Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

PRESIDENT OF SOMALILAND REPUBLIC ON THE CERTAINTY OF THE MOU!

Post by Horus » 30 Oct 2024, 12:44


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: PRESIDENT OF SOMALILAND REPUBLIC ON THE CERTAINTY OF THE MOU!

Post by Za-Ilmaknun » 30 Oct 2024, 12:49

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች;

ከሶማሊላንድ ጋር በተፈረመ የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር ቁርሾ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ አሊ መሐመድ አደን የተባሉ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

በኢትዮጵያ ኤምባሲ በአማካሪነት እያገለገሉ ያሉት አሊ መሐመድ አደን “ከዲፕሎማሲ ሚናቸው ጋር በማይሄዱ ተግባራት ላይ እየተሳተፉ ነው” ሲል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አትቷል።

በሞቃዲሾ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉት አሊ መሐመድ አዳን ይህ ማስታወቂያ በደረሳቸው በ72 ሰዓታት ውስጥ ከአገር ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል።

የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ አሊ ከዲፕሎማሲ ተልዕኳቸው ውጪ ስለተሳተፉበት ተግባር ዝርዝር ባይሰጥም ድርጊታቸው “በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የተደረሰውን የቪየና ስምምነትን የሚጥስ ነው” ብሏል።

ሚኒስቴሩ በቪየና የተደነገገውን ዲፕሎማቶች የሚሰማሩባቸውን አገራት ሕግ እንዲያከብሩ እና በውስጥ ጉዳዮች ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚደነግጉ አንቀጾችን ጥሰዋል ሲል ከሷቸዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲፕሎማቱ መባረር ላይ እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።

ሶማሊያ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ተቀማጭ የነበሩትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ይታወሳል።

የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ወሰድኩት ባለችው እርምጃ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከአገር ከማባረር በተጨማሪ አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯን ጠርታለች።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cvgk96nr4zxo

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: PRESIDENT OF SOMALILAND REPUBLIC ON THE CERTAINTY OF THE MOU!

Post by Za-Ilmaknun » 30 Oct 2024, 12:53

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ተግባራዊነት ስለመዘግየቱ ምን ይላሉ?

ከየትኛውም አገር ይፋዊ ዕውቅናን ያላገኘችው ነገር ግን አንድ አገር ሊኖረው የሚገባውን መስፈርት እንደምታሟላ የሚነገርላት ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ስምምነቱን ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

በአንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ከምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተጠየቁት ቢሂ፣ “ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ ነው። በመግባባት ደረጃ ላይ ነው ያለው። ሁሉም ወገን የተግባራዊነት ሰነዱ መቼ እንሚፈረም እየተጠባበቀ ነው” በማለት አስር ወራትን ያስቆጠረው ስምምነት እንዳለ መሆኑን ገልጸዋል።
“እኛ ከኢትዮጵያ ጋር ነው የተስማማነው። የእኛ ነው ወደሚለው [ፕሬዝዳንት ሐሰን] መሬት መሄድም ሆነ መቆጣጠር እንደማይችል ያውቀዋል። ለ34 ዓመታት ሁለት የተለያየን ነጻ አገራት ነን፤ ሁለት መንግሥታት ነን፤ ሁሉም ያውቀዋል” ብለዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c62976eyz9do

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: PRESIDENT OF SOMALILAND REPUBLIC ON THE CERTAINTY OF THE MOU!

Post by Horus » 30 Oct 2024, 13:26

በእኔ ግምት በኢትዮጵያ በኩል የተደረገው መዘግየት ትክክል ይመስለኛል ምክኛቱም ኢትዮጵያና ሱማሌላንድ ጦርነት በከፈትባቸው ራሳቸው ለመከላከል የዝግጅት ግዜ ብቻ ሳሆን የሱማሌላንድ ምርጫ ፕሬዚዳንት ቢሂን በሚደግፍ አይነት ኢትዮጵጵያ ጣልቃ መግባቷ የሱማሌላንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ስለሚያስቆጣ ኢትዮጵያ የምታደርገው ውል ከመላ ሱማሌላንድ አገርና ፓርቲዎች ስምምነት ጋር እንዲሆን መደረጉ በጣም ዘላቂ ውጤት አለው ። ኢትዮጵያ የምትዋዋለው ከሱማሌላንድ አገር ጋር እንጂ ከአንድ ፓርቲ ጋር መሆን የለበትም። ምክን ያቱም ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ከ50 አመት በኋላስ ኢትዮጵያ ምንድን ነው የምትፈልገው ብለው የባህር ኃይሉ ከዚያ በኋላ ምን ይሆናል የሚለ ከባድ ጥያቄ ሁሉ አንስተዋል ። ማለትም ኢትዮጵያ እግሯን ሱማሌላንድ ካስገባች በኋላ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት የለባትም። ከወዲሁ ሊነሱ የሚችሉ የረጅም ዘመን ችግሮች ላይ ከሁሉም ጋር ተስማምታ መሆን አለበት ስምምነቱ መፈረም የሚኖርበት ። ለምሳሌ ከ2 ሳምንት በኋላ ተቃዋሚው ፓርቲ ካሸነፈ የሚፈራረመው ፓርቲ ያ እንጂ የሙሴ ቢሂ ፓርቲ አይሆንም። ይህ ሁሉ መጣራቱ በጣም ጥሩ ነው ። ይህ ማለት ደሞ ለነሱማሌና ግብጽ ቅዋሜ ግዜ የሚሰጣቸው ነው። ይህ ምንም ማድረግ የሚቻል ችግር አይደለም! የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ጦርነት ባህሪው ስለሆነ።



Somaliman
Member+
Posts: 7167
Joined: 09 Nov 2007, 20:12
Location: Heaven

Re: PRESIDENT OF SOMALILAND REPUBLIC ON THE CERTAINTY OF THE MOU!

Post by Somaliman » 30 Oct 2024, 14:16


Post Reply