Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኬርታ አለም አቀፍ ድምጽ

Post by Horus » 24 Oct 2024, 12:22

ዬቦ ኤቦ ኩልሙ! ለኩልምኛ! ኬር ኤቦ!!! ሁሉም ለሁላችን መልካም ይሁን!!!


Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኬርታ አለም አቀፍ ድምጽ

Post by Horus » 24 Oct 2024, 13:07

የክስታኔ ጉራጌኛ ቋንቋ ለማትሰሙ አንድ ሁለት የቃል ትርጉሞች ጀባ ልበላችሁ።

በማሀበረሰባችን ውስጥ እግዚአብሄር ከሚለው ቃል ቀጥሎ ያለው ኬር ይባላል። በክስታኔኛ እግዚአብሄር እዝጌር ይባላል፤ እዝኬር ማለት ነው። ኬር መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን የካልቸራችን ምሰሶ ነው። ኬር እጅግ ብዙ አግባብ ያለው ሲሆን ማንኛውም መልካም፣ ትክክል፣ ሰላማዊ፣ ስርዓታዊ፣ ደህና የሆነ ነገር ሁሉ ኬርነት ነው።

ክኬርነት ቀጥሎ ያለው የማሀረሰባችን ምሰሶ ሴራ ይባላል። ሴራ ስርዓት የሚለው ግዕዝ ነጠላ ቃል ሲሆን እሱም ኦርደር፣ ሕግ፣ መመሪያ፣ መርህ፣ ባህል፣ ከስተም ወዘተ ማለት ነው። በማኛውም ሕይወታችን ውስጥ ኬር እና ሴራ የሌለበት የለም!

ኤቦ ወይም ዬቦ ይሁን ማለት ሲሆን ቃሉ በቀጥታ ቦ የሚለው ግዕዝ ነው ። ቦ ሆነ ማለት ሲሆን ዬቦ ይሁን ማለት ነው! ክስታኔ ዬቦ ኤቦ ካለ አሜን ይሁን ማለቱ ነው!!

ለምሳሌ ኬር ዬቦ ኬር ይሁን ማለት ነው!

በኬር ዋልም! በሰላም ዋሉ!

Post Reply