Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Union
Senior Member
Posts: 12062
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Union » 14 Oct 2024, 14:52

Horus የሚባል ሽንትቤት የሆነ ሽማግሌ ሰውዬ :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Selam/ » 14 Oct 2024, 14:55

ጭልፊቱ - በህዝብ ጥያቄ የፈረሰ ሰፈር እኮ የህዝብ ተሳትፎ በሰፊው መኖሩን ያሳያል።

አንተ የምትደግፋቸው አጋስስ ኦሮሙማዎች ግን አይደለም በሳይንሳዊ መንገድ ለነዋሪዎቹ መጠይቅ ሊያቀርቡላቸው ይቅርና፣ ማስጠንቀቂያ እንኳን ሳይሰጡ ነው ቤታቸውን በድንገት በላያቸው ላይ የሚያፈርሱባቸው። የድፍረትህና የብልግናህ ብዛት ደግሞ፣ ቤቱ ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ የወደቁ ሰዎች አንድም አላየሁም ብለህ ቀጠፍክ። እኔ የምለው በሳተላይት ነው እንዴ ፈልገህ ያጣሃቸው ወይንስ ያንን ፓኪስታኑን ጠይቀኸው ነው? አንተ ከርሳም፣ አይደለም ደጅ ላይ መውደቅ፣ በጅብ የተበሉም ሰዎች አሉ እኮ።

የከተማን ዕድገት ማስተካከል የሚቻለው እዚያ የነበሩትን ነዋሪዎች በማፈናቀል ብቻ ነው ብሎ ያስተማረህስ የትኛው የከተማ ልማት ምጡቅ ካድሬ ነው? ድሃዎችን ከመሃል ከተማ ወደ ድንበር አካባቢ በማባረር የፖለቲካ ጥቅም ይገኛል ብሎ ያስተማረህስ የትኛው ጠቢብ ነው? ደርግ የጠፈጠፈው የቁጠባና የማህበር ቤት፣ ወያኔም የደረደረችው የኮንዶሚኒየም ጋጋታ እኮ ከውድቀት አላተረፋቸውም።

Horus wrote:
14 Oct 2024, 14:00
አበረ፣
አንተ አዲስ አበባ ውስጥ ምን ሰፈር እንዳደግ አላውቅም። እኔ አዲስ ከተማ በሚባለው በመርካቶና አማኑኤል መካከል ነው ያደኩት። በእኔ ሕይወት ያዲሳባ ማዘጋጃ ሁለት ግዜ ግዙፍ የቅያስ ፈረሳ አድርጓል ። ያውም በሕዝብ ጥያቄና ድጋፍ ፣የሰዎች ቤት ከሁለት እስከ ሚቁረጥ ድረስ ። ያኔ ያዲሳባ ሕዝብ 350 ሺ ነበር! የደርግ መንግስት ቤት የመንግስት ከደረገ ይህው 50 አመት ሊጠጋ ነው ። ይህ የመንግስት ቤት የተባለ የአይጦች መርቢያ ቆሻሻ በዚህ መልክ ሊቀጥል አይችልም። የቆርቆሮ slum ሲፈርስ ለሕዝብ አዘኔታ መሰል መቆርቆር ማሳየትና ለዚህ ግዙፍ ግዙፍ ችግር መፍትሄ ማቅረብ ፍጹም የተለያዩ ናቸው ። እኔ እስካሁን እንዳየሁት ከዚህ የዛገ የቆርቆሮ ጫካ በፍርሰት ምክንያት የሚወጡት ሰዎች ቤት አልባ የጎዳና ተዳዳሪ ሲሆኑ አላየሁም። ከነበሩበት የራቀ ቦታ ተወስደዋል። አሁን ሚዛናዊ የሆነ ሰው የተሻለ መፍጥሄ ያቅርብ!

ከዚያ በተረፈ ማንኛው የመንግስት ስራ የፖለቲካ አላማ አለው። ይህን የሚክድ የፖለቲካ እንሰሳ ሊሆን አይችልም። ኦሮሞቹ ለምንድን ነው የሚጣደፉት ለሚለው መልሱ ቀላልና ሁለት ነው። አንዱ ስልጣን ያላቸውና ተጽኖ ማድረግ የሚችሉት ከተማዎች ውስጥ ብቻ ስለሆነ የሆነ ለውጥ ማሳየት የሚችሉት ከተማዎች ውስጥ ስለሆነ ነው። ሌላው የሕዝብ ተቃውሞ ለማዳከምና ከሚቀጥለው ምርጫ በፊት በቂ ደጋፊ ለመፍጠር ነው። ይህ የመግስት አላማ ነው። ይህን የራሱ አላማ ለሟሟላት ሲል ግን እጅግ አሳፋሪ የሆነው የ7 ሚሊዮን ሕዝብ መታመሻ የቆርቆሮ slum በከፊልም ቢሆን እየቀረፈ ነው። አይ የኦሮሙማ መንግስት እስካለ ድረስ አዲስ አበባ የቆሻሻ መጣያ ትሁን ማለት ፖለቲካም ሕዝባዊነትም አይደለም።

ፖለቲካ የሪያሊቲ ጨዋታ ነው። ፓርቲዎችና ቡድኖች መንግስት እስከ ሚለዋወጡ ድረስ አገር አትቀጥል አይባልም። የበለጠ ኅይልና የተሻለ መፍትሄ ያለው ፓርቲ ማጆሪቲውን ሕዝብ መርቶ በስራና በሃሳብ ማሸነፍ እንጂ ቅሻሻ አይወገድ፣ መንገድ አይጠረግ፣ ፓርክ አይሰራ ማለት ጸር ለውጥ መሆን ነው! ያ ደሞ ያንድ ተራማጅ ዘመናዊ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን የመልካም አሳቢም ዜጋ አመለካከት አይሆንም።

This is not about me. This is not about what I desire or not. This is not about what hate or disdain. This is about being realistic. This is about trade offs. The direction of development of Ethiopia will be decided by the balance of power of its population and their organizational and political competence. While social forces fight over matters of power and governance, the people have to continue to live on, to exist. Addis Abeba population cannot continue to live in these kinds of shameful squalor and slums.

This is my view. It is entirely healthy that others have a different perspective. Bottom line, the people taken out of these slums are not made homeless street dwellers.

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Selam/ » 14 Oct 2024, 23:22

ሪዶር ከለስተር እንደተወለደ ቀደም ብሎ ላልተገለጠላቸው ወገኖቼ:

Affable
Member
Posts: 640
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Affable » 15 Oct 2024, 01:41

አዲስ አበባ ነው ተወልጄ ነው ያደኩት። ፉቅር አለኝ ለአዲስ አበባ። ኳስ ተ ጫውችባታለሁ። ። አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እዛው አዲስ አበባ ነው የተማርኩት። የሁለተኛ ደረጃን ከመጨረሴ በፊት ደርግ ከርችሞኛል ለሁለት አመት። አዲስ አበባን ከመሰናበቴ በፊት የ አዲስ አበባ የሳይንስ ፋኩልቲ ተማሪም ነበርኩ። ስለዚህም አዲስ አበባን አውቃታለሁ ብል ማጋነን አይሆንም። ግን ያቺ የምወዳት አዲስ አበባ ዛሬ ድሮ እንደነበረች መቆየት አለባት ብየ አላስብም። እንደዛ ማሰብ ግብዝነትም ስግብግብነትም ነው። ስለ አዲስ አበባ ብዙ ማለት አሁን የሚገባችው የዛሬው ወጣቶች እና ገና ያለተወለዱ ህፃናት ናቸው። እኔን በግዜው አዲስ አበባ በቅጡ አስተናግዳኛለች። አሁን አይጠበቅባትም። እኔ ያደኩባት አዲስ አበባ አንድ ሚሊየን ህዝብ አልነበራትም። ድል አድራጊው — ፒያሳ የነበረው ሻይ ቤት ስትሄድ ሻይ የሚጠጡትን ወጣቶች ስም ባታወቅም መልካቸውን ማወቅህ ጥያቄው ውስጥ አይገባም ያኔ። ያ አዲስ አበባ እኔ ያደኩባት አሁን የለችም። አዲስ አበባ እየተለወጠች ነው። ያ የግድ ነው። አንዳንዶች አዲስ አበባ የድሮ ገፅታዋ መቀየሩ ያስደነግጣቸዋል። ። ለአዲስ አበቤዊች የለመዱትን ማጣት አልለመድ ማለቱ አይገርምም። ያን በመጠኑ እረዳለሁ። ሌሎች አሉ አዲስ አበባን ከስም በስተቀር የማያውቁ ግን ስለ አዲስ አበባ “ ገፅታ” መቀየር ከነዋሪው በባሰ ሲያላዝኑ የሚውሉ። አወ የአዲስ አበባ ለውጥ ኑሮአቸውን የሚያበላሽባቸው ብዙ ደሀ አዲስአበቤዊች አሉ። ችግራቸው ይገባኛል። መንግስትም ሊረዳው ይገባል። ተፈናቃዪችን መርዳት የመንግስት ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው። ግን የአንድ ደሀን ህይወት እስካወከ ድረስ አዲስ አበባን ዘመናዊ ለማድረግ መጣር “ ወንጀል” ነው የሚለው አፈታሪክ ግን አደብ መግዛት አለበት። ልታቆመው የማትችለው የለውጥ ክስተት ላይ ከጨወታው ውጪ ጭራሽ እንዳትሆን ለውጡ ላይ ሚና ለመጫወት መጣር ነው የተሻለ ምርጫ። አዲስ አበባ የመጪውን እንጂ የአሮጊውን ትውልድ ፉላጎት የማንፀባረቅ ግዴታ የለባትም። ያንን መገንዘብ ትርፉ አለው።

Horus
Senior Member+
Posts: 40208
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Horus » 15 Oct 2024, 02:02

Affable wrote:
15 Oct 2024, 01:41

"ሌሎች አሉ አዲስ አበባን ከስም በስተቀር የማያውቁ ግን ስለ አዲስ አበባ “ ገፅታ” መቀየር ከነዋሪው በባሰ ሲያላዝኑ የሚውሉ። "!!!

እጅግ እጅግ በትክክል! አሁንማ አንድ ሰፈር ሊፈርስ ነው ሲባል የslum ነዋሪዎቹ ዋና ጥያቄና ግብ ግብ ስለሚገቡበት አዲስ ቤት ደረጃና መጠናቀቅ እንጂ በቆርቆሮ ውስጥ ነዋሪ ሁሉ አዳነችን በነካ እጅሽ እያሏት ነው። እንዲያውን ኢፍትሃዊነት ከተባለ የኮሪደሩ ጽዳት የሚያዳላ ይመስላል፣ ወደ መሃል፣ ምስራቅና ደቡብ አዲስ አበባ ከምራብና ሰሜን አዲሳባ ሲነጻጸር።

Horus
Senior Member+
Posts: 40208
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Horus » 15 Oct 2024, 02:15

ይህ ጥምባታም ያሜሪካ አምባሳደር ግን ቆሻሻ አጽዱ ብሎ ሊያዘን መቃጣቱን አጥብቄ ነው የምቃወመው! አቢይ አህመድ ይህን ሰው ከኢትዮጵያ ማባረር አለበት!

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Selam/ » 15 Oct 2024, 07:19

አሁን ደግሞ አሽቃባጮች አዲስ አበባን ጠንቅቀን ስለምናውቃት፣ እኛ የምንለው ብቻ ትክክል ነው የሚል ዜማ ይዛችሁ ብቅ አላችሁ። ብቻ ከእረኝነት ከገጠር የመጣችው አዳነችና የበሻሻው አጭቤ እንዳይሰሟችሁ።

የአዲስ አበባ ቆሻሻ መፅዳት የለበትም የሚል ሰው ካለ አዎ የተሳሳተ ነው። እኔ በበኩሌ የምለው በመጀመሪያ የኦሮሙማ ካድሬዎችና ጭልፊቶች የአይምሮ ቆሻሻ ይፅዳ ነው። ፅዳት ያስፈልጋል በሚለው ከተስማማን፣ የሚቀጥለው ጥያቄ ቆሻሻ ወይንም መፍረስ አለበት የሚባለውን ደረጃ የሚያወጣው ማነው እንዴትስ ነው የማፅዳቱ ሂደት የሚከናወነው የሚለው ነው። ከተማ ማሳመር urban renewal ደግሞ ዶለዟ አዳነችና ዕርጉሙ አብዮት የጀመሩት አዲስ ክስተት አይደለም። ብዙ ሃገሮች አልፈውበታል፣ እየሰሩበትም ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ልክ እንደኛው ጉዶች በተሳሳተ መንገድ ሄደው አጨመላልቀውታል፣ ሌሎቹ ደግሞ ማንንም በማይጎዳ መልክ አሳክተውታል። ከተሳሳቱት ከተሞች በዋናኛነት የአሜሪካን segregated cities ሊጠቀሱ ይችላሉ። ዝርዝሩ ውስጥ ግን እዚህ አልገባበትም።

በዋነኛነት የፕላኒንግ ሂደት ብዙ ባለሞያዎችን የሚያሳትፍና ጊዜ የሚፈጅ ስራ ነው። የማስተር ፕላኒንግ ባለሙያዎች፣ የአሁኑ ከተማ የማፍረስ ዘመቻ ጥናት የጎደለውና የጥድፊያ radical ነው ማለታቸውን በተደጋጋሚ ሰምቻለሁም አውቃለሁም። በመቀጠል፣ ከተማይቷ እትብታቸው የተቀበረባት የነዋሪዎቿ እንጂ በየወቅቱ የሚገለባበጡት ጠጉረ ልውጥ ካድሬዎች ንብረት አይደለችም። ስለዚህ ህዝብን በአሰራሩ ላይ በከፊሉም ቢሆን ማሳተፍ ተገቢ ነው። እኔ የአዲስ አበባ የከተማ ልማት መስሪያ ቤትን በቅርብ አውቀዋለሁ፣ በእርግጥም በጥናት ሂደቱ ነዋሪዎች ይሳተፉ እንደነበር እመሰክራለሁ።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከተማው እንዲያምር ከተፈለገ ድሃው ነዋሪ ከአካባቢው ተነስቶ ሀብታም ብቻ መሰግሰግ አለበት gentrification ብሎ ማሰብ የመጨረሻ ደንቆሮነትና ጨካኝነት ነው። ይኸን የሚሉት ደግሞ ራሳቸው በቆሻሻ መንደር ያደጉና በማንነታቸው የሚሸማቀቁ እራስ-ጠል የሆኑ አናሳ ካድሬዎች ናቸው። ግን ደግሞ እንደገና ተቀጥቅጠህ ካልተፈጠርክ በስተቀር፣ ድሃን ስለጠላህ ብቻ ፣ አይምሮህ ውስጥ የተጣበቀው የድህነትና የበታችነት ቆሻሻ አስተሳሰብ ሊወገድ አይችልም።

ነዋሪዎችን ያሳተፈ የከተማ ዕድሳት urban renewal አሰራር፣ ሰዎቹን ባሉበት ሰፈር እንዲቆዩ ወይንም ወደሌላ ሰፈር እንዲሸጋሸጉ አማራጭ ይሰጣል። ባሉበት ቦታ የኑሮ ውድድሩን የማይፈልጉትና፣ ለኑሯቸው ተመጣጣኝ የሆነ አዲስ ህይወት መጀመር የሚፈልጉት ወደ አዲስ ሰፈር ይሄዳሉ፤ ዕድላችንን እዚሁ እንቀጥላለን የሚሉት ደግሞ የዕድሳቱ አካል ሆነው ባሉበት አካባቢ ይቆያሉ።

ጭልፊቶቹና ካድሬዎቹ ቀድማችሁ ተርገበገባችሁ እንጂ፣ እራሱ ዕርጉሙ ዓብዮት ለገሃርን ለዓረቦች የዛሬ አምስት ዓመት ሲሰጥ፣ እዚህ አሁን ያላችሁት ነዋሪዎች ተሸጋሽጋችሁ ባላችሁበት ሰፈር ትቆያላችሁ እንጂ አትፈናቀሉም ነበር ያለው። እኔም ያኔ ይኸ ሰውዬ የሲንጋፖር፣ የሳንቲያጎ፣ የሲዖል ከተማዎች እንዴት ደሃ ነዋሪዎቻቸውን ሳያፈናቅሉ ከተሞቻቸውን እንደለወጡ ገብቶታል ብዬ ተመስጬ ነበር። የዛሬው አጭቤ አቶ ዓብዮትና የኦሮሙማ ካድሬዎቹ ግን እንኳን መጠይቅ ሊያደርጉ ይቅርና ቤቱቹን ሲደረምሷቸው እንኳን የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አይሰጡም። ቤቱ እራስህ ላይ ይፈርስብህና ዕድለኛ ከሆንክ ከተማው ዳር በጅምር ላይ ያለ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ትወረወራለህ ወይንም ጎዳና ላይ ትጣላለህ።

ለጭልፊቶቹ የማቀርበው ጥያቄ - ለምንድነው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ልክ እንደ ሲንጋፖርና ሳንቲያጎ እዛው እነበሩበት ሰፈር ተሸጋሽገው በኮንዶሚኒየም ውስጥ የመኖር አማራጭ የማይሰጣቸው? ይኸ የፖለቲካ ውሳኔ ነው ሆኖም ግን ማፈናቀሉን እደግፈዋለሁ የምትል ከሆነ አጭበርባሪና ጎጠኛ ካድሬ ወይንም በሁለት ሹካ መብላት የምትፈልግ ከርሳም ነህ። ሌላ ሶስተኛ መንገድ የለም!
Last edited by Selam/ on 15 Oct 2024, 22:58, edited 5 times in total.

Odie
Member+
Posts: 6200
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Odie » 15 Oct 2024, 07:44

Affable wrote:
15 Oct 2024, 01:41
አዲስ አበባ ነው ተወልጄ ነው ያደኩት። ፉቅር አለኝ ለአዲስ አበባ። ኳስ ተ ጫውችባታለሁ። ። አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እዛው አዲስ አበባ ነው የተማርኩት። የሁለተኛ ደረጃን ከመጨረሴ በፊት ደርግ ከርችሞኛል ለሁለት አመት። አዲስ አበባን ከመሰናበቴ በፊት የ አዲስ አበባ የሳይንስ ፋኩልቲ ተማሪም ነበርኩ። ስለዚህም አዲስ አበባን አውቃታለሁ ብል ማጋነን አይሆንም። ግን ያቺ የምወዳት አዲስ አበባ ዛሬ ድሮ እንደነበረች መቆየት አለባት ብየ አላስብም። እንደዛ ማሰብ ግብዝነትም ስግብግብነትም ነው። ስለ አዲስ አበባ ብዙ ማለት አሁን የሚገባችው የዛሬው ወጣቶች እና ገና ያለተወለዱ ህፃናት ናቸው። እኔን በግዜው አዲስ አበባ በቅጡ አስተናግዳኛለች። አሁን አይጠበቅባትም። እኔ ያደኩባት አዲስ አበባ አንድ ሚሊየን ህዝብ አልነበራትም። ድል አድራጊው — ፒያሳ የነበረው ሻይ ቤት ስትሄድ ሻይ የሚጠጡትን ወጣቶች ስም ባታወቅም መልካቸውን ማወቅህ ጥያቄው ውስጥ አይገባም ያኔ። ያ አዲስ አበባ እኔ ያደኩባት አሁን የለችም። አዲስ አበባ እየተለወጠች ነው። ያ የግድ ነው። አንዳንዶች አዲስ አበባ የድሮ ገፅታዋ መቀየሩ ያስደነግጣቸዋል። ። ለአዲስ አበቤዊች የለመዱትን ማጣት አልለመድ ማለቱ አይገርምም። ያን በመጠኑ እረዳለሁ። ሌሎች አሉ አዲስ አበባን ከስም በስተቀር የማያውቁ ግን ስለ አዲስ አበባ “ ገፅታ” መቀየር ከነዋሪው በባሰ ሲያላዝኑ የሚውሉ። አወ የአዲስ አበባ ለውጥ ኑሮአቸውን የሚያበላሽባቸው ብዙ ደሀ አዲስአበቤዊች አሉ። ችግራቸው ይገባኛል። መንግስትም ሊረዳው ይገባል። ተፈናቃዪችን መርዳት የመንግስት ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው። ግን የአንድ ደሀን ህይወት እስካወከ ድረስ አዲስ አበባን ዘመናዊ ለማድረግ መጣር “ ወንጀል” ነው የሚለው አፈታሪክ ግን አደብ መግዛት አለበት። ልታቆመው የማትችለው የለውጥ ክስተት ላይ ከጨወታው ውጪ ጭራሽ እንዳትሆን ለውጡ ላይ ሚና ለመጫወት መጣር ነው የተሻለ ምርጫ። አዲስ አበባ የመጪውን እንጂ የአሮጊውን ትውልድ ፉላጎት የማንፀባረቅ ግዴታ የለባትም። ያንን መገንዘብ ትርፉ አለው።
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
Now I get your Identity.
Boti-Gama :lol: == DDT==affable==abetokichaw==noble Amhara
Who said addis should not change? This is not the way forward :lol:
Why don't you go read what gentrification means?
Addis has a master plan. This is a random destruction and glittering. It is demographic change
Did you remember the flood, it is glittering without a drain.
You don't destroy old cities. London has not been destroyed. It is a very old city with very narrow lanes.
I can count 10000 things. But you are either and idiot to know the reason why many complain about, or you are a profiter or you are dumb Oromo simply supporting your kins :lol:

Stupid cadre :lol:

Affable
Member
Posts: 640
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Affable » 15 Oct 2024, 08:47

Odie, ካድሬው አንተ ነህ። እኔ አይደለሁም። እዚህ ሚሊዪን ስም እየለወጣችሁ ብትመጡ የምትቀይሩት ነገር የለም። አንዲት ቅንጣት። ለራሳችሁ ነው የምታወሩት። ለአዲስ አበባ ህዝብ አትመጥኑም። የ አዲስ አበባ መቀየር እንቅልፉ ከነሳህ መጥፎ በሽታ ላይ ነው ያለሀው። የማይድን ምክንያቱም የ አዲስ አበባን መለወጥን የሚያቆም ምንም ሀይል አይመጣም። እዚህ ላይ የትራይባል ፓለቲካህ ርባና እንደሌለው ልነግርህ እወዳለሁ። ይህ ለውጥ የመጣው ህወአት ስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ ቢሆን ኖሮ — ማን ነበር አጎትህ የሚለው — የ ምርጡ ዘር ተአምር እየሰራ ነው እያላችሁ እንቅልፉ አንተኛም ነበር በጩሀታችሁ።

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10461
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by ethiopianunity » 15 Oct 2024, 09:17

Abere wrote:
14 Oct 2024, 10:07
Horus,

Honestly, your praise of the extinction of Addis Ababa is so baffling. This is not even demolition when one truly analyses the degree, intensity and the coverage of extinction - particularly all these occurred in synchronized fashion all over the city in just a single year. This neither an urban gentrification or renewal, it is extinction and genocide of citizens.

All these extinction projects of Orommuma for sure is an over night scheme of cleansing non-Oromo residents ( dispossessing them) - not based on the National Urban Planning Institute's master plan survey that dates back 10 or more years of studies.

If it were a good intention, this would not be an overall destruction of the city ( especially when the country is without money or needs money to feed its people). You have not questioned why all this rush taking place? Why is this an emergency project of Orommuma and all it Qeerroo are on a fire-fighting mission of displacing people en masse? Orommuma affected people in may ways - their neighborhood, Edir, Equib, livelihood, health, education, etc.

Please also note, since Orommuam projects are random ill-designed ( out of the national urban plan repeated surveys) they too will be demolished for failure to meeting standard or obstruct sustainable urban development. The cost of destruction will be too heavy.
Abere,

That is my dilemma. Abiy deceptively put prominent Ethiopians who struggle and speak for Ethiopia paralyzed them in less than 3 years of his leadership in order to trick them and the population, by appointing them near him (put your enemy closer), and saying Ethiopia! Ethiopia! His book says so, “show the cow where the grassland, where you digged a pit under it..”. We have no grasped the fact that the project of Liberation Fronts lead by Isayas lives on, Abiy is raised by Tplf under Simon Berket who answers to Shabia and Isayas. Of course from snake you don’t find pigeon egg,except snake egg. Therefore all those who scream Aby cadres are impotent as he has control of key Ethiopians : Dakon Daniel Kibret, Dawit Core, Seyoum the journalist,diaspora activists, etc whom l respected sacrificed so many for Ethiopia are now being deceived by Aby . I don’t think they understand being member of Illuminati as religion, as Tplf, Olf, Shabia are. So many sorcery is used to fulfill this project i countries. The Lieration Fronts plan is to fulfill this dream. As Aby had become a member of Illuminati, he accepted the Moble Peace price award from the hand of lgbtq…l have suspicion, as he is student of Bereket Simon, He has been deceiving Ethiopians as descendant of previous kings.. they probably think once Tplf is gone(which is a lie), everything will be ok. No amount of ok will explain why in the midst of war and absence of peace, you displace Addis Abebans in the name ketema limat. That is one question. Why you are targeting Amara who has been targeted by liberation fronts for 30 years and who supported you voted for you, etc indeed the world is unstable, that affect Ethiopia too. But pp has ample oortunity no matter what to control Tplf and Olf throughout the nation if nothing else. Why the rush spending on borrowed money unnecessary so you are now under the orders of Arabs when you can mobilize the most Ethiopians you deceived to elect you, to work especially in agriculture if nothing else to produce food and export to Arabs for currency? Why you allowed Olf inside Ethiopia that turned against Ethiopians and weaponized against Ethiopia? How can you let in Olf who does not believe in Ethiopia in the first place and create more problems for Ethiopians? I was thinking is this not be more problem for Aby to counter Tplf and Olf by welcoming Olf and radicalizing our Oromo youth? He must be part of Liberation Front himself when he welcomed Olf. Bereket Simon and Sebhat Nega we’re released by Aby, are in comfort in U.S organizing the break up of Ethiopia while the Ethiopian soldier that rescued Sebhat Nega had Aby killed in another Weyane war. There is no Ethiopian military currently that protects citizens, as someone in ER mentioned, the army currently is to protect the government pp and Aby while pp and Aby with Liberation Fronts is implementing the destruction of Ethiopia, they know they need protection against Ethiopians who will rightfully resist this destruction whose forefathers kept them free from colonization. The near future of Addis will be home of Liberation Fronts (all of them) becoming oligarchs and foreigners. That is why the rush to change Addis as anti Ethiopians eating way of citizens. By coordinating with foreigners, the plan is to turn Addis into Babylon which is under way. Why the need to look like West from corrupted African leaders? We know Westerners are regretting allowing oligarchs to grow within their nation as the citizens of West are being eaten away slowly. PP named itself exactly this Prosperity for reason so that it is going to create Oligarchs who are going to eat away Ethiopians

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Selam/ » 15 Oct 2024, 09:25

ካድሬው - አዎ፣ ምንም አልተሳሳትክም፣ ሰካራም የሚሾፍረው ባቡር ማንም ሊያቆመው አይችልም። በጎጠኝነት ያበደ አካልም ጭፍጨፋውንና ማፈናቀሉን ማንም እንደማያቆመው ደጋግሞ ነግሮናል።

እኔንም አሰራሩ ትክክል ያልሆነና በግፍ የታጀለ ነው ከማለት የሚያስቆመኝ ማንም ሃይል የለም። የእኔ ሃሳቤ ምንም ፋይዳ የማያመጣ ቢሆን ኖሮማ፣ እናንተ ጭንጋፍ ካድሬዎች የ24 ሰዓት የወሬ ማመላለሱ ስራ ይቀርባችሁ ነበር። ተባይ!

Affable wrote:
15 Oct 2024, 08:47

Right
Member
Posts: 4305
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Right » 15 Oct 2024, 10:15

ይህ ጥምባታም ያሜሪካ አምባሳደር ግን ቆሻሻ አጽዱ ብሎ ሊያዘን መቃጣቱን አጥብቄ ነው የምቃወመው! አቢይ አህመድ ይህን ሰው ከኢትዮጵያ ማባረር አለበት!
Really. Pretending to be patriotic and calling on “patriotic Abiye” to do something is a typical cadre work.
Try something else.

As I have said one of the 3 things is forcing you to behave super stupid: MONEY -TRIBALISM - MENTAL BREAKDOWN.

And on corridor development: putting lipstick on a pig. The recent floods in Addis that brought faeces and dirt out on the surface confirms it is a waste of borrowed money.
Mega palace, beautifying Addis and other fancy projects in a country where civil wars are igniting on all corners is not and should not be a priority to the government.

Not that it is relevant but my bet is Horus’s Mindset, tribalism and all he does is consistent to non residents to AA Abiye, Adanech, Takele Uma etc. he may gone to school in AA but that is it. For him to come up with this argument of knowing the city to justify Corridor Destruction is utterly stupid.

Abere
Senior Member
Posts: 14851
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Abere » 15 Oct 2024, 10:31

ሆረስ፤

አዲስ አበባ ከተማ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ( ተወልደው ያዳጉበት ይሁን፤ ከሁሉም የአገሪቱ ምንጭ መጥተው ውበት እና ሙቀቷን ለተቋደሱት) ከፍተኛ የማይጠፋ የትውስታ ማህተም በሁሉም አእምሮ የረገጠች ናት። አብይ አህመድ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ፤ 4ኪሎ፤ ለገሀር ወዘተ ቢያፈርስ እነኝህ ቦታዎች ከህዝብ አእምሮ አይጠፉም። ኦሮሙማ የእነኝህን አሻራዎች ለማጥፋት የሚጠቀምበት የፓለቲካ እና የፕሮፓጋንዳ መልካም አጋጣሚ ፍለጋ ነው - ያረጀ ሰፈር፤ የጭቃ ግድግዳ፤ የቀበሌ ቤት ወዘተ። (opportunistic reason or pretext - urban slum :mrgreen: ) ለመሆኑ ከቀዘቀዘ የሃብታም የቦሌ ቪላ ቤት ደሳሳዎቹ የቀበሌ ቤቶችም የፍቅር ሃብት እንደሆኑ ደግሞ መረዳት እንደት ይሳናል።የሙስና አይጦች እና ቀበኞች የሚደበቁት በታላላቅ ቪላዎች ነው - የህዝብ ገንዘብ የዘረፉ አገር የሚዘርፉ:: ይህ ስል ድህነት ይሞቃል ወይም በድህነት ይኑሩ አይደለም። እነዚህ ወገኖቻችን የሰው ልጅ ክብር ይገባቸዋል - ቤታቸው ለምን እንደሚፈርስ እንኳን ሳያውቁ ስራ ውለው ማታ ቤታቸው ሲመለሱ ቤታቸው ፈርሶ ነው የሚያገኙት። ቤታችን ካልፈረሰ ማታ እንገናኛለን ሁኗል የአድስ አበባ ሰው ጠዋት ሲሰነባበት:: Is this common where you live?

ደግሞስ ይህ አይነት ከተማ የማደስ ስራ በኢትዮጵያ ብቻ ነው እንደ የተጀመረው? ሁሉም የአለም አገራት ይህን ያደርጋሉ - ግን በጥናት፤ በጋራ ስምምነት፤ በበቂ ዝግጁነት ነው። በዘመቻ ሙሉ የአዲስ አበባን ቤት ከማዕበል (hurricane) በላይ በሆነ ውድመት የመታ አገር አላየንም። የኦሮሙማው ማዕበል ብቻ ነው። የፈረሱትን ቤቶች እና ሰፈር እኮ እናውቃለን። አንዳንዶቹ ከሚሰሩት በላይ የተሻሉ ምርጥ ቪላዎች፤ፎቆች ፈርሰዋል - ባለቤቶቹ የኦሮሙማ ቤተሰብ አይደላችሁም - ልትሆኑም አትችሉም ተብለው። ኦሮሙማዎች እያደረጉ ያሉት ገሃዱ ነገር አጋጣሚውን slum በሚል በመሸፋፈን ህዝብ ማፈናቀል ማስደድ ነው። ይህ ምጡቅ አእምሮ አያስፈልገውም። እሳት በባዶ በእጁ የጨበጠ ሰው አያቃጥልህም ያዘው እንደማለት ነው።
I am pretty much certain Abiy Ahmed is building another giant slum as well.

Just a note: no body opposes urban renewal. but the OLF 's context is totally opposite of the practice of developing decent urban community. It is a hideous tactic of ethnic cleansing. It is all about how to remove non-Oromo Ethiopians out of Addis Ababa, from their legal land, home and possession. It is an illegal confiscation by Orommuma. This act of banditry is not even political and cannot be regarded as for the purpose political activism.

ለእኔ ግን እጅግ የሚደንቀኝ አንድ ነገር ብቻ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ መብቱን ማስከበር የማይችል ደካማ ብቻ ሳይሆን ሲበዛ ፈሪ ነው። ቤት በተፈሰ ቁጥር እየወጣ መልቀስ እንጅ ለተቃውሞ እንኳን ሰልፍ አይወጣም። ሰልፍ እየወጣ ያለው በቄሮ መንገድ ላይ የተወረወረው የቤት እቃው እና ቁሳቁሱ ብቻ ነው።

የፍርሃት ቆፈን ከሚገድለው ፍርሃቱን በማባራ ተቃውሞ ቢገልጽ አንድ ሰፈር አይደለም አንድ ቤት አይፈርስም። ባለቤቱ ካልጮኸ ማንም አይደርስለትም እንድሉ። ይህ ህጋዊ እና ሞራላዊ መብቱን በፍርሃቱ ምክንያት ተነጥቆ ሞራል አልባ ኦሮሙማ ይጫዎትበታል።

Horus wrote:
14 Oct 2024, 14:00
አበረ፣
አንተ አዲስ አበባ ውስጥ ምን ሰፈር እንዳደግ አላውቅም። እኔ አዲስ ከተማ በሚባለው በመርካቶና አማኑኤል መካከል ነው ያደኩት። በእኔ ሕይወት ያዲሳባ ማዘጋጃ ሁለት ግዜ ግዙፍ የቅያስ ፈረሳ አድርጓል ። ያውም በሕዝብ ጥያቄና ድጋፍ ፣የሰዎች ቤት ከሁለት እስከ ሚቁረጥ ድረስ ። ያኔ ያዲሳባ ሕዝብ 350 ሺ ነበር! የደርግ መንግስት ቤት የመንግስት ከደረገ ይህው 50 አመት ሊጠጋ ነው ። ይህ የመንግስት ቤት የተባለ የአይጦች መርቢያ ቆሻሻ በዚህ መልክ ሊቀጥል አይችልም። የቆርቆሮ slum ሲፈርስ ለሕዝብ አዘኔታ መሰል መቆርቆር ማሳየትና ለዚህ ግዙፍ ግዙፍ ችግር መፍትሄ ማቅረብ ፍጹም የተለያዩ ናቸው ። እኔ እስካሁን እንዳየሁት ከዚህ የዛገ የቆርቆሮ ጫካ በፍርሰት ምክንያት የሚወጡት ሰዎች ቤት አልባ የጎዳና ተዳዳሪ ሲሆኑ አላየሁም። ከነበሩበት የራቀ ቦታ ተወስደዋል። አሁን ሚዛናዊ የሆነ ሰው የተሻለ መፍጥሄ ያቅርብ!

ከዚያ በተረፈ ማንኛው የመንግስት ስራ የፖለቲካ አላማ አለው። ይህን የሚክድ የፖለቲካ እንሰሳ ሊሆን አይችልም። ኦሮሞቹ ለምንድን ነው የሚጣደፉት ለሚለው መልሱ ቀላልና ሁለት ነው። አንዱ ስልጣን ያላቸውና ተጽኖ ማድረግ የሚችሉት ከተማዎች ውስጥ ብቻ ስለሆነ የሆነ ለውጥ ማሳየት የሚችሉት ከተማዎች ውስጥ ስለሆነ ነው። ሌላው የሕዝብ ተቃውሞ ለማዳከምና ከሚቀጥለው ምርጫ በፊት በቂ ደጋፊ ለመፍጠር ነው። ይህ የመግስት አላማ ነው። ይህን የራሱ አላማ ለሟሟላት ሲል ግን እጅግ አሳፋሪ የሆነው የ7 ሚሊዮን ሕዝብ መታመሻ የቆርቆሮ slum በከፊልም ቢሆን እየቀረፈ ነው። አይ የኦሮሙማ መንግስት እስካለ ድረስ አዲስ አበባ የቆሻሻ መጣያ ትሁን ማለት ፖለቲካም ሕዝባዊነትም አይደለም።

ፖለቲካ የሪያሊቲ ጨዋታ ነው። ፓርቲዎችና ቡድኖች መንግስት እስከ ሚለዋወጡ ድረስ አገር አትቀጥል አይባልም። የበለጠ ኅይልና የተሻለ መፍትሄ ያለው ፓርቲ ማጆሪቲውን ሕዝብ መርቶ በስራና በሃሳብ ማሸነፍ እንጂ ቅሻሻ አይወገድ፣ መንገድ አይጠረግ፣ ፓርክ አይሰራ ማለት ጸር ለውጥ መሆን ነው! ያ ደሞ ያንድ ተራማጅ ዘመናዊ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን የመልካም አሳቢም ዜጋ አመለካከት አይሆንም።

This is not about me. This is not about what I desire or not. This is not about what hate or disdain. This is about being realistic. This is about trade offs. The direction of development of Ethiopia will be decided by the balance of power of its population and their organizational and political competence. While social forces fight over matters of power and governance, the people have to continue to live on, to exist. Addis Abeba population cannot continue to live in these kinds of shameful squalor and slums.

This is my view. It is entirely healthy that others have a different perspective. Bottom line, the people taken out of these slums are not made homeless street dwellers.

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Selam/ » 15 Oct 2024, 13:27

ቆሻሻ የድህነት ምልክት ነው። ቆርቆሮ ቤት ውስጥም አኖርከው ፎቅ ላይ ሰቀልከው አይጠፋም።

ደንቆሮ ካድሬዎች ግን ከመሬት ከፍ ያለ ነገር ሁሉ የስልጣኔ ምልክት ይመስላቸዋል። እነ ፖላንድና ሶቪየት ኅብረት የዛሬ ስልሳ ዓመት ድሃውን ሁሉ በአንድ ቅርፅ በተገነቡ የኮንክሪት አፖርትመንቶች prefabricated concrete apartment ውስጥ ለማጨቅ ሞክረው ነበር። ሰው ታዲያ የለመደውን አኗኗር በአንድ ጊዜ መለወጥ ስላልቻለ፣ ዶሮና አሳማውን ይዞ ፎቅ ቤት ውስጥ ገብቶ ተግማማ። ይኸ ለዚያውም ነፃ የመብራት፣ የውኃና ፍሳሽ አቅርቦትን ጨምሮ ነው። ዛሬ እነዚያ አስፀያፊ ፎቆች ፈርሰዋል፣ ባዷቸውን ቆመዋል ወይንም ተለውጠዋል።

ምስኪኑን የአዲስ አበባ ነዋሪንም፣ በመጀመሪያ ኑሮውን ሳታሻሽል ፎቅ ላይ ብትሰቅለው በሉክ ወረቀት እየተፀዳዳ ፍሳሽ መውረጃውን ይደፍነዋል። ይኸንን ደግሞ በአይኔ በብረቱ መገናኛ ኮንዶሚኒየሞች ውስጥ አይቻለሁ። የምግቡን ተወውና፣ ጎረቤትህ ከላይኛው ፎቆ ሆኖ ሻወር ሲወስድ፣ አንተ ምን አይነት ሳሙና እንደሚጠቀም መናገር ትችላህ፣ እንጥፍጣፊው ስለሚደርስህ። በሌላ አነጋገር የመሬቱ የቆርቆሮ ቤት slum ፣ ፎቅ ላይ ወጥቶ ነው ያገኘሁት። In essence, it’s a mere upgrade to a high-rise slum.

ሰዎች አኗኗራቸው ባለበት ቆሞ ይቅር ማለት ስህተት ነው፣ ሆኖም በአንድ ለሊት በጅምላ አፈናቅለህ ሜዳ ላይ መበተን ወንጀል ነው፣ የታሸገ ምግብ እየበላህ ፎቅ ላይ ተንጠልጠልም ማለት ኃጥያት ነው።

Abere wrote:
15 Oct 2024, 10:31
ሆረስ፤
I am pretty much certain Abiy Ahmed is building another giant slum as well.
Last edited by Selam/ on 15 Oct 2024, 22:53, edited 1 time in total.

Tiago
Member
Posts: 2952
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Tiago » 15 Oct 2024, 14:15

ይህ ጥምባታም ያሜሪካ አምባሳደር ግን ቆሻሻ አጽዱ ብሎ ሊያዘን መቃጣቱን አጥብቄ ነው የምቃወመው! አቢይ አህመድ ይህን ሰው ከኢትዮጵያ ማባረር አለበት!
horus :lol: :lol:

ገረድ ማባረር መሰለህ :lol: :lol:

Affable
Member
Posts: 640
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Affable » 15 Oct 2024, 14:52

ከህወአት ካድሬዎች ሽልማት የሚገባሽ በማስመሰል ሰላም አንቺ ነሽ። ግን በሰላም የምትኖሪ አይመስለኝም። ያልሆንሽውን ለመሆን የምታደርጊው መገለባበጥ ሰላም ሰጪ አይደለም። ተቆጣሽ ምንም አትፈይጂም በማለቴ። ሀቁ ያ ነው። DDT እና sun , አንድ ሰሙ የጠፋኝ አሮሞ , ሰሞኑን በሽታ እየሰጣችሁ ያለውን ጉራጌ ሆረስ Revelations የሚሉትን አማራ ቀንሺ ቀሪው በሙሉ የህወአት ካድሪዎች ናችሁ። መንግስት በዚህ ስብስብ ምክንያት እንቅልፉ እያጣ ነው ብለሽ ከገመትሽ ደንቆሮ ነሽ። ሰሞኑን Tik Tok ላይ የሰማሁት በደንብ ይገልፃችሁል።
You can’t fix stupid, and stupid is forever.

Odie
Member+
Posts: 6200
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Odie » 15 Oct 2024, 15:06

Affable wrote:
15 Oct 2024, 08:47
Odie, ካድሬው አንተ ነህ። እኔ አይደለሁም። እዚህ ሚሊዪን ስም እየለወጣችሁ ብትመጡ የምትቀይሩት ነገር የለም። አንዲት ቅንጣት። ለራሳችሁ ነው የምታወሩት። ለአዲስ አበባ ህዝብ አትመጥኑም። የ አዲስ አበባ መቀየር እንቅልፉ ከነሳህ መጥፎ በሽታ ላይ ነው ያለሀው። የማይድን ምክንያቱም የ አዲስ አበባን መለወጥን የሚያቆም ምንም ሀይል አይመጣም። እዚህ ላይ የትራይባል ፓለቲካህ ርባና እንደሌለው ልነግርህ እወዳለሁ። ይህ ለውጥ የመጣው ህወአት ስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ ቢሆን ኖሮ — ማን ነበር አጎትህ የሚለው — የ ምርጡ ዘር ተአምር እየሰራ ነው እያላችሁ እንቅልፉ አንተኛም ነበር በጩሀታችሁ።

>>>>>>>>>
በሳምባህ ብቻ ተንፍስ!
የሆንክ አገው ሽንጎ ተከፋይ
የእቂል ኦሮሞ ካድሬ
በፌስታል እያስታቀፉች ጋዜጣ የሚያካክል ፅሁፍ ትተይባለህ
ወይ ደግሞ ኮንዶምንየምህን እያጣጣምክ ነው!
ጥቅመኛ!
በደረስባቸው ግፍ የሚያለቅሱት ምነው ቤተስብህ ባረገልኝ?

ጥቅምህን እያፈስክ ድሃ ላይ ታቅራራለህ!

Horus
Senior Member+
Posts: 40208
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Horus » 15 Oct 2024, 15:17

አበረ፣
ለጥያቄህ መልስ አንተው እየሰጠህ መሰልኝ ። እኔ the wisdom of the crowd በሚባል መርህ አምናለሁ። የአንድ ሕዝብ ችግርና ትክክለኛ መፍትሄ ከራሱ ከሕዝቡ ይበልጥ ሌላ ሰው አያውቅም ። ደሞም ስታጽቲካል ሳይንስ ትክክል ነው ብለን ካመንን የሕዝቡ አመለካከትና መልስ ከማንኛው የኤሊት መፍትሄ የላቀ ነው ። እኔና አንተ በአዲስ አበባ ውስጥ አንኖርም። ባዲስ አበባ ብንኖር እንኳን እዚያ የበሰበሰ ቆርቆሮ ውስጥ መኖር አንፈቅድም። ስለዚህ እራስክን እነዚያ ሰዎች ቦታ አድርገህ አለምን ብታይ ሌላ አመለካከት እንደ ሚኖርህ ጥርጥር የለውም ። በምራብ ጽዱ አለም ላይ ሆነን ስለ አዲሳባ እስለም መፍረስ ላይ ያለን ቅዋሜ በመሰረቱ የሎጂክ ስህተት አለበት ። የራሳችን ሳብጀክቲቭ ስሜት ስለሆነ።

ይህን ሳብጀክቲቭ ስሜታንን የሚያረጋግጥ እርምጃ አዲስ አበቤዎች ስላልወሰዱ በጥቅል ፈሪ ሕዝብ ብለን ሕዝብ መዝለፍ ስህተት ነው፤ ያውም በምዕራብ ምቾት ላይ እየኖርን። ትህትናና ህውሚሊቲ ያሻናል። ይህ እኛ የምናደርገው ክርክር ማድረግ ያለባቸው እዚያ ያሉት ነዋሪዎች ናቸው። ለምን ዝም እንዳሉ ጥናት ያደረገ ሰው ይንገረን እንጂ የኛን ፖለቲካዊ ምርጫ በቆሻሻ ውስጥ በሚኖሩ ዜጋዎች ላይ የመጫን የሞራል ትክክለኛነት ሊኖረን አይችልም።

ሕዝቦች ሁልግዜም በጥቅል የሚወስኑት ነገር በታሪክ ትክክል መሆኑ ነው የሚታወቀው ፤ ያ ነው wisdom of the crowd የሚባለው።

Abere
Senior Member
Posts: 14851
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ይድረስ ቆሻሻ አይፍረስ ለምትሉ ጸረ ኮሪደሮች!

Post by Abere » 15 Oct 2024, 15:35

ሆረስ፤

አሁን የአዲስ አበባ ህዝብ በመጀመሪያ መጠለያ አልባ ነው። ያች የሚወዳት የቆሮቆሮ ክዳን ቤት እንኳን የለውም። እንዳው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ ሁሉ አይኖረም። ፎቅ እና ተራ የጭቃ ቤት ምርጫ መካከል ያለ አይደለም። የመባረር እና ተቀምቶ ከአካባቢው ደብዛ የመጥፋት ዕድል ነው። እኔ አድስ አበባ በቅርብ አይቻታለሁ። ከናጠጡ ሃብታም ቤት እንድሁም ከምስኪን ቆርቆሮ ቤት ነዋሪዎች ከፍትፍታቸው ፊታቸው የሚጋብዝ። ለእኔ ወገን እንጅ የህንጻ ክምር መለኪያየ አይደለም።

ለሰው ሰው እንጅ ቦታ ዘመድ አይሆንም። ሰዎች በሰዎች እየተበሉ ነው። ልክ በእንግሊዝ የሱፍ በግ እርባታ ለፋብሪካ ግብዐት ሲባለ ሰዎች ከመሬታቸው ሲያፈናቅሏቸው " በጎች ሰዎች እየበሉ ነው" እንደተባለው። ኦሮሙማ ኢትዮጵያዊያኖችን ከኖሩበት ከከበዱበት ቦታቸው ላይ እየበላቸው ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ የመሳተፍ፤የመጠየቅ መብት የተቀማ ነው። ህጋዊ ሰውነት ቢኖረውም በኦሮሙማ ዘንድ ህጋዊ ሰውነት ብቃት የሌለው የተሰለበ ነው። በዚህ ድረጃ የምናገረው ህዝቡ እንድህ እንድሆን የታፈነ፤ የተሸማቀቀ፤ እስረኛ ስለሆነ ብቻ ህዝብ ተስማምቶበታል የሚል ፈሊጥ አይሰራምም፡

አዲስ አበባ ታላቅ የኦሮሙማ የኦሽዊዝ ማካመቻ (Auschwitz concentration) ማስቃያ ቦታ ነው - በከተማ ደረጃ። People are living and doing under duress of Orommuma. Their silence is taken advantage as if they agreed.

Horus wrote:
15 Oct 2024, 15:17

Post Reply