Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6852
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ሁለት ጥልቅ ጥያቄዎች ለአበረ፥ ስለ ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

Post by Naga Tuma » 05 Oct 2024, 12:33

አበረ፥

ስለ ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ታሪክ በጥልቀት የምታዉቅ ይመስለኛል።

ለሁለት ጥልቅ ጥያቄዎች መልስ ይኖርህ ይሆናል።

ኣንደኛ) የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንደ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በየዘመኑ የምያሳትመዉ እንሲይክሊካል ዐይነት መሪህ ኣለዉ?

ሁለተኛ) የሌለዉ ከሆነ የሁለቱን ቤተክርስትያኖች እንደዚህ ዐይነት መሪህ ማሳተም እና ኣለማሳተም ወይም አካሄድ ልዩነትን ማብራራት ይቻላል?

Abere
Senior Member
Posts: 14851
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሁለት ጥልቅ ጥያቄዎች ለአበረ፥ ስለ ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

Post by Abere » 06 Oct 2024, 10:57

Naga Tuma,

ያነሳኻቸው ጥያቄዎች አስተምሮ ይኖራቸዋል ባይነኝ። ብዙ ጊዜ አሳታፊ እና አስተማሪ ሁኔታዎች ቢነሱ እንደት ጥሩ ነበር። የሚሰነዘሩትም ሃሳቦች ጎጅ የጎንዮሽ ትርጓሜ ባይሰጣቸው ወይም ተፈልጎባቸው ባይጠየቁ ሰው እና ትውልድ ገንቢ ይሆኑ ነበር።

በመቀጠል እኔ የቤተ-ክህነት ትምህርት በእውነቱ የለኝም ። This is just a note of disclosure. ይህን ጥያቄ በአጋጣሚ ያነበበ ጥልቅ የቤተ-ክህነት ትምህርት ያለው ቢመልሰው ሁላችንም እንማርበታለን።

እንደ ተራ ምዕምን የግል ግምቴ የሆነውን ለመጥቀስ ያህል። ከኦርቶዶክስ ካቶሊክ ተወለድ: ከካቶሊክ ደግሞ የማርቲን ሉተር ፕሮቴስታንት ተወለደ - ብዙ አይነት ፕሮቴስታንት እምነቶችም ተወለዱ - ለምሳሌ ፕሮስፐርቲ ጎስፕል ወዘተ።

ኦርቶዶክስ ቀዳማዊ ሃይማኖት ነች። በየዘመናቱ በርካታ ጉባዔዎች እና መለያየቶች ከተነሱ በኋላ በመጨረሻ የተለዩት ካቶሊክ ሆነው እንደ ወጡ ይታወቃል። በመሰረቱ በኦርቶዶክስ ይሁን በካቶሊክ ትልቁ ተግባር የሀዋርያነት ስራ ነው። ይህም ሀዋርያት ወንጌልን ለህዝብ መዳረስ የጠፋውን መንጋ የህይወት ምግብ ( የክርስቶስ ወንጌል) መመገብ። ይህ ማለት የሲኖዶስ ይሁን ሌላ ቅርጽ የሀዋርያቶችን አቀነጃጀት እና የስልጣን ሰንሰለት መከተል ነው።

እንደምናየው ካቶሊክ መንበር መቀመጫው አንድ ቦታ ሁኖ ዕዙ በርካታ የአለም አገራት እና አህጉራት ይሸፍናል - ስለዚህ የግደታ የቢሮክራሲ ስራ ለአንድ ወጥነት ይታገላል ማለት ነው። በሌላ መልኩ የአለም ኦርቶዶክስ ግን ከሮማው በአደረጃጀት አንድ ወጥ ትዕዛዝ ከአንድ ርዕሰ አባት ሳይሆን አንድ ወጥ ዶግም እና አቋም አለው። የግብጽ፤ የሩሲያ፤የኢትዮጵያ የራሳቸው ፓትሪያርክ አላቸው። እንደ ሮማው ፖፕ የኢትዮጵያው ፓትሪያርክ የግብጽ ወይም የሩሲያን ምዕም ወይም ጳጳስ መገዘት የሚችል አይመስለኝም - በእኔ ግምት። ስለዚህ ምስጢረ-ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ ስንመልሰው የኢትዮጱያው ፓትሪያሪክ ልክ የሮማው ፓፕ በተለያዩ አገራት በአሜሪካ፤ ካናዳ፤ጀርመን፤ ደቡብ አፍሪካ፤ወዘተ ተዋረድ ቢሾፕ ላይ የትዕዛዝ የበላይነት እንዳለው የኢትዮጵያው ፓትሪያርክ በአሩሲው፤በባሌው፤በትግሬው፤ በጎጃሙ ወዘተ ጳጳሳት ላይ ስልጣን እና የበላይ ትዕዛዝ ተፈጻሚ ነው።

ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ ሀዋርያቶች የበላይ ሰብሳቢ እንደነበራቸው እንድሁ ሁሉ ማለት ነው። የፓትሪያርክ ይሁን የ Pope አመራረጥ በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን የሚመረጥ መሆን እንዳለበት በቤተ-እምነቶቹ የቆዩ መዛግብት እና ቀኖና ይኖራል። አሁን ችግር እየሆነ የመጣው ፓትሪያርክ ከምዕምን እየለየ ያለው በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን በባለስጣን እየተመረጡ መሆኑ ነው። Pope ቢሆንም የሚያስተላልፉት የአክቲቪስት መልዕከት ነው ባይነኝ - አንዳንዶቹ ጆሮዬ ሲገቡ።

በመሰረቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከተራው ምዕምን እጅ የማይገቡ እና ያልገቡ በዝህ ዙሪያ የተሰነዱ ጥንታዊ መዛግብት አሉ። በአንድ ወቅት በተነሳው የሲኖዶስ ግርግር አንዳንዶች ያንን ህግ እያጣቀሱ ሲተቹ አድምጫለሁ።

ቀደም ብየ እንደጠቀስኩት ቀዳማዊ እና ጥንታዊ መሰረተ ክርስቶስ የሆነችው ኦርቶዶክስ በየጊዜ በዙሪያዋ የሚያቆጠቁጡ አረም ይፈትናታል። ዛሬም እንድሁ በኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተጠልለው የተሃዲሶ ርዕዮት አቀንቃኝ ወይም መናፍቃን እያስቸገሩ ነው። ከካቶሊክ አንድ ልማድ ከፕሮቴስታን ሌላ ልማድ በመምዘዝ ኦሮቶዶክስን ለመተቸት ሲታገሉ እናያለን።

በእኔ ግምት ሃይማኖት ውስብስ ድርጅታዊ ቢሮክራሲ ይዘት ውስጥ ከገባ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ክርስቶስ ከፈተና ላውጣችሁ አለ እንጅ ፈተናን ወደ ሆነ የቢሮክራሲ ሰንሰለት ግቡ አላለም። ከቤተ-ክርስቲያን አስተምሮ እና ቀኖና ውጭ የሆነ ተቀጻል አደረጃጀትም ለክርስቶሳዊ ትምህርት መስፋፋት ማነቆ ነው።



Naga Tuma wrote:
05 Oct 2024, 12:33
አበረ፥

ስለ ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ታሪክ በጥልቀት የምታዉቅ ይመስለኛል።

ለሁለት ጥልቅ ጥያቄዎች መልስ ይኖርህ ይሆናል።

ኣንደኛ) የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንደ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በየዘመኑ የምያሳትመዉ እንሲይክሊካል ዐይነት መሪህ ኣለዉ?

ሁለተኛ) የሌለዉ ከሆነ የሁለቱን ቤተክርስትያኖች እንደዚህ ዐይነት መሪህ ማሳተም እና ኣለማሳተም ወይም አካሄድ ልዩነትን ማብራራት ይቻላል?

Post Reply