ግን አንድ ልዩነት በግልፅ ይታየኛል፣ በሁለቱ አከባበር ላይ።
መስቀል ልሙጥነትን ወይም ደግሞ አንድ አይነትነትን ያገዝፋል፣ በአንድ ማዕከል ይመራል፣ በአንድ ዶክትርን ማለት ይቻል ይሆናል፣ በላሙያዉ ስላልሆንኩኝ ግን ብዙም መፍረድ አልፈልግም።
ኢሬቻ ደግሞ በብዝሃትነት ነዉ የተመሰረተዉ፣ አንድ አይነትነትን የለዉም፣ የተለየዩ ቀለማት አንድ ላይ መጥቶ ያደምቁታል፣ ድምቀቱ ከብዝሃት ነዉ የምመነጨዉ፣ በተመሳሳይነት ላይ አይደለም የተመሰረተዉ፣ አንድ ማዕከል የለዉም፣ መሪዎቹ ከተለያዩ ቦታ ና ከተለያዩ አመለካከቶች ነዉ የምመነጨዉ፣ ሁሉም እንደመሰለዉ ያከብረዋል፣ እንድህ ሁን የምለዉ ማዕከለዊ ስልጣን የለዉም፣ መመሪያዉ የኦሮሞ የቆየ ና እግዚያብሔርን የማመስገን ተልዕኮ ብቻ ነው ያለዉ። ሁሉም እንደመሰለዉ ፈጣሪዉን ማመስገን ና መማፀን ይችላል፣ በዚህ ሆነህ፣ እንደዚህ አድርገህ የምለዉ የለም።
ብዝሃነት የፈጠረዉ የብዝሃነት መገለጫ፣ ኢሬቻ፣ መደሰቻ!
