ወደባችው ቆሞ ቀረ-ውይ አልን! የመለስ ዜናዊ ግመላቸው ያጠጡበት ያለው እርግማን ነው ብለን
ግን ግመል ባህር ይጠጣል?
ባህር ያህልስ የሚጠጣ የግመል ቁጥር ይኖራቸው ይሆን አልን?
መለስ ዜናዊ ያረገመው መለስ ዜናዊንም ያልረገመ ማን አለ?
እንደውም በጋዜጠኛ እርግማን አይደል ሞተ የሚባለው!
>>>>>>>>>>>>
ያ ሌባ ማራገቢያ/መሽረፈጥ ለማጨናበር ለሻቢያ ቀለበት አርጎላቸው ሲያበቃ እስይ አልን
ወደእኛ ሲመጡ ደስም አለን
ከኢትዮጵያ ጋር ሲታረቁ አጠፋሪስ እንደወስደ ያረጋቸዋል
ከኢትዮጵያ ጋር ሲጣሉ እንደ ክፉ ለማኝ ሁላችንንም እየስደቡ drug ወይም አልኮል withdrawal የያዛቸው ይመስላሉ!
ድባቴ ይይዛቸዋል
ግብፅ ጉያ ይገባሉ
የሱማሌ የበላይ ጠባቂ ይሆናሉ
ማደርያቸው እየፈረስች ሃያላን አገራት አልስሙንም ብለው UN ውስጥ ይሳደባሉ
ኢትዮጵያን የሚያክል የመሬት ስፋትና ህዝብ ቢኖራቸው ሶስተኛው የአለም ጦርነት ሻእብያ አይቀስቅስም ብላችሁ ነው?
ቢያንስ በምኞት ደረጃ አሁንም የሚተው አይደሉም
ቀበተተኝ ላናፋ ብላ ጅብ የዘረጠጣት አህያ አይነት ነገር!!
..........
ደግነት ከቤት ነው የምጀምረው:: እነዚህ እስረው የሚቀቅሉዋቸውን ቢያንስ ፈተው ካገር ቢያባርዋችው እንኩዋን ስብአዊነት ነበር እኮ:: ቢያንስ ሬሚታንስ ያመጡ ነበር!
…………………..
በነገራችን ላይ ስውየው ኮከባቸው ችስታነት ነው? ኢሳያስ::
ሽበጣቸው የዛኔ የኔ ሽበጥ ይመስላል:: ከወያኔ ትንሽ ሻል ግን ይላል:: የወያኔው ያሳር ነው!! ያኔ በጦርነቱ ዘመን ደብረ ሲኦል ትዛላችሁ? በእርግጥ ሲኦል ወርዶ የመጣ ዞምቢ መስሎ ነበር!
ኢሱ ግን አንዳንዴ ከመሬት በላይ ያለ ዞምቢ ይመስላሉ:: ቢሆንም ከወያኔ ዞምቢ ይሻላሉ!!
---------
ስውየው ኮከባቸው ችስታነት ነው ብዬ ነበር! የምር ሁሉ ነገር እየፈራረስ በትእቢት ሁልህንም ንቀው የሚንገዋለሉት ነገር ይገርማል:: የኤርትራው ሊጋባው በየነ እየተጀነነ(ተደብቄ ነው የማወራው...ቂቂቂቂቂ) :: ሃብታም ቢኖር ይጨፈልቁታል::ልባቸው የሌላ ፕላኔት ነው የሚመስለው:: ቢደን..ጥረምፕን...የሚበልጥ!! ችግሩ ልባቸው የሌላ ፕላኔት ስለሆነ ይመስላል ቀሳውስትን የሚያስቃዩት:: ልክ ነዋ alien ምን ቄስ ያውቃል? alien ማን ደፍሮ ይመክራል! ሃሃ! at your own risk
የብልፅግናውና የኛውን ጉድ ተውት! ስውን ሳይሆን መንገድ ፓርክና ኮሬ ነጌኛን ብቻ እያበለፀገ ያለው? ሳልረሳ:: ገበሬው በልፅጎ አቦካዶ ሶስት ጊዜ እየበላ ነው አሉ:: መጠጣት ገና አለመደም:: ደስ አይልም ዘመነ ግልብጥብጥ:: አቦካዶ በቆጮ:: አቦካዶ በንጀራ...ዶሮ በዳቦ ትበላታለህ ወደህ ነው? አብይ ይመስገን እያልክ ነዋ! ኤጭ ምን ምስጋና ይገባዋል? ላቦካዶ!
ግን ሁለቱም አገሮች አይገርሙም ሁለት ጥግ ነክ ስርአት እኮ ነው ያላቸው!!
………..
ግን ኢትዮጵያና ኤርትራ በልፅገው አብረው በጉርብትና የሚኖሩ ይመስላችሁዋል? ኖ ሃብታም ቢሆኑ ኑክሊያር ይስራሉ ለመጠፋፋት:: በተለይ ወንድም ሻእብያ እያለ?
አንዱ ሃብታም አንዱ ደሃ ቢሆንም በምቀኝነት ይተላለቃሉ!
አጥር ይስራ ይሆን? አይመስለንም እየተናጩ መቀጠል ነው እንደፎረሙ!!