Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 14836
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Abere » 23 Sep 2024, 11:14

የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ ማለት ነው።

ለብዙዎች ይህ ጉዳይ ሰም መስሎ ሊታያቸው ቢችልም ውስጠ ወይራ የሆነው ወርቅ ግን ሻዕባያ ትልቁ የፍርሃት ምንጩ እና አስጊው ጉዳይ ኢትዮጵያን የሚያፈቅሩ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ናቸው። ይህ ለሻዕብያ ቀይ መስመር ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ ቡድኖች ለምሳሌ ኦነግ እና ወያኔ በምንም አይነት ሁኔታ ከሻዕብያ ጋር ግጭት ቢገቡ የአላማ እና የራዕያ አንድነት ስላላቸው ግጭታቸው ወቅታዊ እና አንጻራዊ ነው። ይህ ጉዳይ የአባት እና የልጅ ጥል ነው። ልጅ አባቱን ራበኝ ቢለው አሳ እንጅ እባብ ይሰጠዋል? ወይስ አኩርፎ ጠፍቶ ከብዙ አመታት በኋላ አባቱ ቤት ቢመጣ አባቱ አትግባ ይለዋል? ይልቅስ አባቱ ለልጁ ያለቀ ልብሱን ይቀይርለታል እራሱን አሻሽቶ የተራበውን ልጁን ያጎርሰዋል እንጅ እንዳለ መጽሀፍ ቅዱስ።

ጉራጌ የተገንጣይ እና አስገንጣይ ቅራቅንቦ ሻዕብያ እና ወያኔ ዘላቂ ጠላት ስለሆነ ይህ ደግሞ ለሻዕብያ ቀይ መስመር በመሆኑ አሁን ግጭቱ በኤርትራ ክፍለ ሀገር ተወላጆች (ሻዕብያዊያን) እና አገር ወደድ ጉራጌዎች መካከል እየጦፈ ነው። ሻዕብያዎች አፋቸውን ከፍተው 24/7 ይለጠፋሉ፤ጉራጌዎች ደግሞ ሱቃቸውን ከፍተው በድህነት እና በግጭት አዙሪት በቆረቆዙት ስደተኛ ሻዕብያዎች ላይ በዋዛ እና ቁም ነገር የሻዕባያን ታኒካ (ቆርቆሮ) እራስ ይጮኹታል። እያየን ያለነው ከቅርብ ጊዜ ወድህ ይህ ነው።

Odie
Member+
Posts: 6196
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Odie » 23 Sep 2024, 11:40

Abere wrote:
23 Sep 2024, 11:14

"የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ ማለት ነው።
ለብዙዎች ይህ ጉዳይ ሰም መስሎ ሊታያቸው ቢችልም ውስጠ ወይራ የሆነው ወርቅ ግን ሻዕባያ ትልቁ የፍርሃት ምንጩ እና አስጊው ጉዳይ ኢትዮጵያን የሚያፈቅሩ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ናቸው። ይህ ለሻዕብያ ቀይ መስመር ነው።"

Good observation. Shabea never been a friend of Ethiopia. You could see abyssiniabeach who often posts a disintegrated Ethiopia, home to 120M people. They insult 120m people for having issue with Oromuma and the drifter in 4Kilo. We hate Oromuma and they say they hate them but they fight with us and 120m Ethiopian, specifically Gurage ethnic which even does not know their conundrum. They call names the whole Gurage bs they don't like the way Horus thinks.

1. They may have grudge with Abiy but why should they attack all of us?

2. They are using disintegrated Somalia to attack Ethiopia by bringing in Egypt and arming all sorts of mercenaries in Somalia

3. They come to Ethiopian forum for insult and misinformation, no Ethiopian goes to their forum. They think they seceded, but they still want to stay infighting with us and when they get advantage, exploit the country.

Shabia has never been a friend of Ethiopians from inception and never will be until it is uprooted. It is an opportunist terrorist group :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Horus » 23 Sep 2024, 14:52

አበረ፣
የተማረ ይግደለኝ ይባል የለ! በቃ ጉዳዩ ያ ነው ። ይህ በጉራጌ ላይ ያለው ዘመቻ ዛሬ አልተጀመረም ። ወያኔ ትግሬ አዲሳባ ከገባች ጀምሮ ትግሬ ዋና ጠላታችን አማራ ነው ቢልም ፣ሌላው ጠላት ጉራጌ ተገርጎ አንድም በቁጥር እንዲመነምን ከፋፍለውት፣ ሌላም የጉራጌ ድብልቅ ሆነው በጉራጌነት ለዘላለም ከኛ ጋር መርካቶ ሚነግዱት ዛሬ ሶዶ ጂዳ የተባሉት የነግር ማብሩ ና ሌሎች ቁልፍ ያቢይ አማካሪዎች ሁሉ በትግሬ ተንኮል ከጉራጌ ተገንጥለው ኦሮሞ የተባሉት ናቸው ። ይህ ሁሉ የሆነው ጉራጌ ትግሬን ምንም ስላደረገው አይደለም ፤ በጽኑ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። በጸረ ጣሊያኑም ያርበኘት ዘመን የሆነው ይህው ነው ። እነ ደስታ ዳምጠውን ለሶላቶ የሰጡት የትግሬ ባንዳዎች ናቸው ።

ልክ እንዳልከው ዛሬ ትግሬ ከ4 ኪሎ ከተባረረና አማራም በውስጡ አሁን ያለው ነገር ውስጥ ከገባ በኋላ ፣ ትግሬም በራሱ ጉዳይ ከተጠመደ በኋላ ስራዬ ብለው በጉራጌ ላይ የሚዘምቱት የኤርትራ ተገንጣዮች ናቸው ። እንደ ምታውቀው ጉራጌ ምንም ያደረጋቸው ነገር የለም ። ችግራቸው የጉራጌ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ።

እኔ የጉራጌ ግለሰቦች ምን ያክል በአቢይ መንግስት ውስጥ እንዳሉና ምን ያክል ኢንፍሉወንስ እንዳላቸው ምንም የማውቀው ነገር የለም ። አንድ ነገር ግን አለ ምንም ጥርጥር መናገር የምችለው ነገር አለ ። ጉራጌ በንጉስ ካሌብ፣ ሆነ በንጉስ ሳህለ ስላሴ ፣ በምኒልክ ሆነ በኃይለ ስላሴ ፣ በመንግስቱ ሆነ በአቢይ አህመድ መንግስት ውስጥ በማንኛውም የስልጣን ደረጃ ቢሰሩ አንዲት ቅንጣት ጸረ ኢትዮጵያም ሆነ በሌላ ሕዝብ ላይ ክህደት የሚፈጽሙ፣ ግፍ የሚሰሩ፣ ሌላውን የሚጨቁኑ ሕዝብና ባህል አይደሉም።

እኔ አፌን ሞልቼ የምናገረው ነገር አለ። ዛሬ እንኳን ኦሮሞ በሚዘውረው መንግስት ውስጥ የሚያገለግሉ ጉራጌዎች ካሉ አቢይን ወደ ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ይገፉት እንደ ሆነ እንጂ ለኦሮሞ ተገንጣይነት መሳሪያ እንደ ማይሆኑ ፍጹም እምነቴ ነው። ስለዚህ ኤርትራዊያን እኛ ማናውቀው የጉራጌ ሚና ካለ ያው የጽኑ ኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ተጽኖ ቢሆን ነው። እሳት በሌለበት ጪስ አይኖርም እንደ ሚባለው ነገሩን በትክክል አስተውለሃዋል ።

ኢትዮጵያ የጎሳውን ድራማ ዝቅጠት ጨርሳ አሁን ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ እያዘገመች ነው! ይህ ነው የተገንጣዮች ጥብቅ ፍርሃት ።

sesame
Member+
Posts: 7958
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by sesame » 23 Sep 2024, 16:32

Gurages were originally Eritreans from GuraE! በኤርትራውያንና ጉራጌዎች መሃከል ቅራኔ ሊኖር ኣይችልም። ጉራጌዎች ከጉራዕ፡ ኤርትራ፡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ የፈለሱ የነኛ ሰዎች ናቸው። Gurages are "our people in Ethiopia." በደርግ ግዜ፡ "ኤርትራ ኣትሸጥም: ኣትለውጥም" ሲባል የሰማ ኣንድ ኣራዳ ጉራጌ፤ "ለምን ኣትሸጥም፡ ትርፍ ካላት ትሂድ እንጂ" ኣለ ይባላል። That is how Guraghes supported our independence struggle. :lol: :lol: :lol:

Abere
Senior Member
Posts: 14836
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Abere » 23 Sep 2024, 17:11

Sesame street,

ያኔ ጉርዐ ጉርዐ በሚባልበት ዘመን የእናንተ አገር ማን ይባል ወይም እናንተ ማን ትባሉ ነበር? :lol:

sesame
Member+
Posts: 7958
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by sesame » 23 Sep 2024, 17:33

Abere wrote:
23 Sep 2024, 17:11
Sesame street,

ያኔ ጉርዐ ጉርዐ በሚባልበት ዘመን የእናንተ አገር ማን ይባል ወይም እናንተ ማን ትባሉ ነበር? :lol:
"ምድሪ ባሕሪ" ስንባል ነበር። ከድሮም ባሕሩ የኛ ነበር። :lol: :lol: :lol:

Dama
Member+
Posts: 6433
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Dama » 23 Sep 2024, 18:17

Horus wrote:
23 Sep 2024, 14:52
አበረ፣
የተማረ ይግደለኝ ይባል የለ! በቃ ጉዳዩ ያ ነው ። ይህ በጉራጌ ላይ ያለው ዘመቻ ዛሬ አልተጀመረም ። ወያኔ ትግሬ አዲሳባ ከገባች ጀምሮ ትግሬ ዋና ጠላታችን አማራ ነው ቢልም ፣ሌላው ጠላት ጉራጌ ተገርጎ አንድም በቁጥር እንዲመነምን ከፋፍለውት፣ ሌላም የጉራጌ ድብልቅ ሆነው በጉራጌነት ለዘላለም ከኛ ጋር መርካቶ ሚነግዱት ዛሬ ሶዶ ጂዳ የተባሉት የነግር ማብሩ ና ሌሎች ቁልፍ ያቢይ አማካሪዎች ሁሉ በትግሬ ተንኮል ከጉራጌ ተገንጥለው ኦሮሞ የተባሉት ናቸው ። ይህ ሁሉ የሆነው ጉራጌ ትግሬን ምንም ስላደረገው አይደለም ፤ በጽኑ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። በጸረ ጣሊያኑም ያርበኘት ዘመን የሆነው ይህው ነው ። እነ ደስታ ዳምጠውን ለሶላቶ የሰጡት የትግሬ ባንዳዎች ናቸው ።

ልክ እንዳልከው ዛሬ ትግሬ ከ4 ኪሎ ከተባረረና አማራም በውስጡ አሁን ያለው ነገር ውስጥ ከገባ በኋላ ፣ ትግሬም በራሱ ጉዳይ ከተጠመደ በኋላ ስራዬ ብለው በጉራጌ ላይ የሚዘምቱት የኤርትራ ተገንጣዮች ናቸው ። እንደ ምታውቀው ጉራጌ ምንም ያደረጋቸው ነገር የለም ። ችግራቸው የጉራጌ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ።

እኔ የጉራጌ ግለሰቦች ምን ያክል በአቢይ መንግስት ውስጥ እንዳሉና ምን ያክል ኢንፍሉወንስ እንዳላቸው ምንም የማውቀው ነገር የለም ። አንድ ነገር ግን አለ ምንም ጥርጥር መናገር የምችለው ነገር አለ ። ጉራጌ በንጉስ ካሌብ፣ ሆነ በንጉስ ሳህለ ስላሴ ፣ በምኒልክ ሆነ በኃይለ ስላሴ ፣ በመንግስቱ ሆነ በአቢይ አህመድ መንግስት ውስጥ በማንኛውም የስልጣን ደረጃ ቢሰሩ አንዲት ቅንጣት ጸረ ኢትዮጵያም ሆነ በሌላ ሕዝብ ላይ ክህደት የሚፈጽሙ፣ ግፍ የሚሰሩ፣ ሌላውን የሚጨቁኑ ሕዝብና ባህል አይደሉም።

እኔ አፌን ሞልቼ የምናገረው ነገር አለ። ዛሬ እንኳን ኦሮሞ በሚዘውረው መንግስት ውስጥ የሚያገለግሉ ጉራጌዎች ካሉ አቢይን ወደ ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ይገፉት እንደ ሆነ እንጂ ለኦሮሞ ተገንጣይነት መሳሪያ እንደ ማይሆኑ ፍጹም እምነቴ ነው። ስለዚህ ኤርትራዊያን እኛ ማናውቀው የጉራጌ ሚና ካለ ያው የጽኑ ኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ተጽኖ ቢሆን ነው። እሳት በሌለበት ጪስ አይኖርም እንደ ሚባለው ነገሩን በትክክል አስተውለሃዋል ።

ኢትዮጵያ የጎሳውን ድራማ ዝቅጠት ጨርሳ አሁን ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ እያዘገመች ነው! ይህ ነው የተገንጣዮች ጥብቅ ፍርሃት ።
Believe in the supremacy of your thoughts. But you should not be a coward to change your views when millions of people in Oromo support OLF, Tigray TPLF, Eritrea EPLF. There is nothing wrong with them; it's rather you who is wrong.

Abere
Senior Member
Posts: 14836
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Abere » 23 Sep 2024, 20:19

አሁን ወደ መስመር እየመጣሽ ነው - ጥሩ መልስ ነው። ባህር-ምድር/ ባህር-ነጋሽ ያሚለውን ስያሜ የሰጠው ማን ነው። የማን ባህር-ምድር? የመሬት ግዛቱን አንዱን መናገሻ ሌላውን የባህር በር ያደረገ አንድ መንግስት ነበር ማለት ነው። ብርሃን ሳይኖር ጨለማ ማወቅ አይቻልም። አንድ መንግስት ይህ ባህር-ምድር ያደገሞ የሰብል፤የመንግስት መናኻሪያየ ነው ያለ እንዳለ ያስረዳል።

በጣም ጥሩ ነው። ኤርትራ የሚባል ነገር እንደሌለ መገንዘብሽ ትልቅ ለውጥ ነው። ወደ ቀደመው ጉዳይ ስንመለስ ጉራጌዎች ከጉርዐ ናቸው ካልሽ በባህር-ምድር ወይም ባህር-ነጋሽ አንጻር ከሆነ መልካም ነው። ጉራጌ ግን የአስካሪ-ላንድ ግዛት ዘመን ጎሳ አይደለም። ኤርትራ የሚባል ነገር ጉራጌ አያውቅም። ስለዚህ እርምት ማድረግ ይጠበቅብሻል። ለጉራጌ ኤርትራዊ ወይም አስካሪ-ላንድ ነህ ማለት ትልቅ ስድብ ነው። This is just my opinion.
sesame wrote:
23 Sep 2024, 17:33
Abere wrote:
23 Sep 2024, 17:11
Sesame street,

ያኔ ጉርዐ ጉርዐ በሚባልበት ዘመን የእናንተ አገር ማን ይባል ወይም እናንተ ማን ትባሉ ነበር? :lol:
"ምድሪ ባሕሪ" ስንባል ነበር። ከድሮም ባሕሩ የኛ ነበር። :lol: :lol: :lol:

kebena05
Member
Posts: 3122
Joined: 10 Nov 2019, 14:58

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by kebena05 » 23 Sep 2024, 20:41

Great Response!

እቺን የፒፒ ገረድ ከንባታ ከረበትካት lol

sesame wrote:
23 Sep 2024, 17:33
Abere wrote:
23 Sep 2024, 17:11
Sesame street,

ያኔ ጉርዐ ጉርዐ በሚባልበት ዘመን የእናንተ አገር ማን ይባል ወይም እናንተ ማን ትባሉ ነበር? :lol:
"ምድሪ ባሕሪ" ስንባል ነበር። ከድሮም ባሕሩ የኛ ነበር። :lol: :lol: :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Selam/ » 23 Sep 2024, 20:56

ይኸንን ርዕስ በጣም እወደዋለሁ።

አንደኛ ፡ የጉራጌ ህዝብ ከግራና ከቀኝ በጎጠኞችና ጅቦች ቢቦጫጨቅም፣ ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ አይልም።

ሁለተኛ፥ አንድን ጎሳ ጠቅልሎ የሚሳደብና የሚያጠቃ ወራዳ ብቻ ሳይሆን ዕርጉም ነው።

ሶስተኛ፥ ካድሬነት ጎጥ አይወስነውም። የኦሮሞ፣ የትግሬና የአማራ ካድሬ እንዳለ ሁሉ፣ የጉራጌ ካድሬም ግጥም አድርጎ አለ። የተማሩ ካድሬዎችና የመንግስት ተላላኪዎች ለምን ከገዳይ ፖለቲከኞች ጋር ትሰራላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም መልሳቸው አንድ ዓይነት ነው፥ “ሃገሬን ለማገልገል ነው!” That’s a bullsh!t!

የጨቦ ጉራጌን ያስጨረሰው አቶ ገስግስ ገብረ መስቀልም፣ ከርሳሙ ብርሃኑ ነጋም፣ ውሻው ዳንኤል ክብረትም፣ ከአንዱ መንግስት ወደ ሌላው የሚገለባበጠው ስንዝሮው ታየ አፅቀ ስላሴም፣ ከደርግ ጀምሮ የሚልከሰከሰው የወባ ዶክተሩ ተቀዳ ዓለሙም፣ የመለስ ዜናዊ ቡችላ ዶር ፈቃዱ ገዳሙም፣ አቶ እርስቱ ይርዳውም፣ አቶ ስዩም ተሾመም ቢጠየቁ መልሳቸው ከዚህ የተለየ አይሆንም። መንግስት ለምን ሰዎችን ያፈናቅላል፣ ያስራል፣ ለምንስ ይገድላል ስትላቸው ግን መልስ የላቸውም።

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Selam/ » 23 Sep 2024, 21:21

ቀቤ ባሬንቱ - እኔ የምጠየፈው ነቀዝ ሻዕቢያ ያረከሰውን ርዕስ ብቻ ነው።
kebena05 wrote:
23 Sep 2024, 21:10
Selam/ wrote:
23 Sep 2024, 20:56
ይኸንን ርዕስ በጣም እወደዋለሁ።

እምዬ ቁጭ ይበሉ
አንቺ የምትጠዩው ርዕስ አለ? :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Horus » 23 Sep 2024, 21:54

Abere wrote:
23 Sep 2024, 20:19
አሁን ወደ መስመር እየመጣሽ ነው - ጥሩ መልስ ነው። ባህር-ምድር/ ባህር-ነጋሽ ያሚለውን ስያሜ የሰጠው ማን ነው። የማን ባህር-ምድር? የመሬት ግዛቱን አንዱን መናገሻ ሌላውን የባህር በር ያደረገ አንድ መንግስት ነበር ማለት ነው። ብርሃን ሳይኖር ጨለማ ማወቅ አይቻልም። አንድ መንግስት ይህ ባህር-ምድር ያደገሞ የሰብል፤የመንግስት መናኻሪያየ ነው ያለ እንዳለ ያስረዳል።

በጣም ጥሩ ነው። ኤርትራ የሚባል ነገር እንደሌለ መገንዘብሽ ትልቅ ለውጥ ነው። ወደ ቀደመው ጉዳይ ስንመለስ ጉራጌዎች ከጉርዐ ናቸው ካልሽ በባህር-ምድር ወይም ባህር-ነጋሽ አንጻር ከሆነ መልካም ነው። ጉራጌ ግን የአስካሪ-ላንድ ግዛት ዘመን ጎሳ አይደለም። ኤርትራ የሚባል ነገር ጉራጌ አያውቅም። ስለዚህ እርምት ማድረግ ይጠበቅብሻል። ለጉራጌ ኤርትራዊ ወይም አስካሪ-ላንድ ነህ ማለት ትልቅ ስድብ ነው። This is just my opinion.
sesame wrote:
23 Sep 2024, 17:33
Abere wrote:
23 Sep 2024, 17:11
Sesame street,

ያኔ ጉርዐ ጉርዐ በሚባልበት ዘመን የእናንተ አገር ማን ይባል ወይም እናንተ ማን ትባሉ ነበር? :lol:
"ምድሪ ባሕሪ" ስንባል ነበር። ከድሮም ባሕሩ የኛ ነበር። :lol: :lol: :lol:
አበረ፣
አንድ ሃቅ ልንገርህ! በመላ ጉራጌ፣ በድፍን ታሪኩ ጉራጌ ሴት ልጁን ሳባ ብሎ ጠርቶ አያውቅም ፤ አዜብ ብሎ ጠርቶ አያውቅም! በፍጹም! በመላ ጉራጌ በድፍን ታሪኩ ወንድ ልጁን ሃጎስ ብሎ ጠርቶ አያውቅም ። ጉራጌ አይደለም ትላንት ጣሊያን ከፈጠረው ኤርትራ፤ ከዚያ ቀደም እንኳን ቅንጣት የባህል የዝርያ ት ስ ስ ር የለውም። አንድ ቦታ ብቻ በቲኒሿ የአለቃ ታየ 'የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ' በሚለው መጽሃፋቸው ከግማሽ ፓራግራፍ ያነሰ ጉራጌ ከጉር 'አ መጣ ብለው በወረወሩት በሰረተ ቢስ መላምት ላይ ነው ይህ ሁሉ ድራማ!

መሰረተቢስ ያልኩበት ምክኛት አለኝ ። ለምሳሌ ጋፋት የመጣው ገፋት ከሚለው ነው፤ ከንጉሱ (ከንግስቷ) ጎን ሲሄዱ ገፋትና ጋፋት ተባሉ ይላሉ ። ፍጹም ተረት ማለት ነው። ከሸዋ በኦሮሞ ወረራ ወደ ደጋ ዳሞት ጎጃም የፈለሱት እዚያ ዛሬ ጎጃሜ ሆነዋል ። እነዚህ ሰዎች አፈር ቀቅለው የብረት አር አይረን ኦር መስራት ጥበብ ነበራቸውና አጼ ቴዎድሮስ ጎጃም ሰው አስልከው የጦር መሳሪያ መድፍ እንዲሰሩለት የተወሰኑ ጥበበኞች ወደ ቋራ ያስመጣል ። እነሱም ዝነኛውን ጋፋት የተባለው የቴዎድሮስ መድፍ ሰሩለት ። በዚያ ሳቢያ ትንሽ የጋፋት ጎሳ ቋራ ላይ አድገው ነበር። ይህቺን የሰሙ አለቃ ታየ አለም ምንም የታሪክ ጥናት ጋፋት ገፋት ማለት ብለው የተረት ታሪክ አስቀሩ ማለት ነው ። ስለጉራጌም የወረወሩት መላምት ተመሳሳይ ነው ። አለቃ ታየ የጉራጌ ምድርን ረግጠው አያውቁም ፣ ምን ቋንቋ እንደ ምንናገር እንኳ የሚያውቁት ነገር የለም ።

ጉራጌ እንደ ሚባለው ከአካለ ጉዛይ የግንድ ትስስር ቢኖረው በብዙ የባህልና የቋንቋ ምልክቶች ይገናኝ ነበር ። በአንድ ቃል ሁሉም ዉሸት ነው።

Dama
Member+
Posts: 6433
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Dama » 23 Sep 2024, 22:08

Selam/ wrote:
23 Sep 2024, 20:56
ይኸንን ርዕስ በጣም እወደዋለሁ።

አንደኛ ፡ የጉራጌ ህዝብ ከግራና ከቀኝ በጎጠኞችና ጅቦች ቢቦጫጨቅም፣ ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ አይልም።

ሁለተኛ፥ አንድን ጎሳ ጠቅልሎ የሚሳደብና የሚያጠቃ ወራዳ ብቻ ሳይሆን ዕርጉም ነው።

ሶስተኛ፥ ካድሬነት ጎጥ አይወስነውም። የኦሮሞ፣ የትግሬና የአማራ ካድሬ እንዳለ ሁሉ፣ የጉራጌ ካድሬም ግጥም አድርጎ አለ። የተማሩ ካድሬዎችና የመንግስት ተላላኪዎች ለምን ከገዳይ ፖለቲከኞች ጋር ትሰራላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም መልሳቸው አንድ ዓይነት ነው፥ “ሃገሬን ለማገልገል ነው!” That’s a bullsh!t!

የጨቦ ጉራጌን ያስጨረሰው አቶ ገስግስ ገብረ መስቀልም፣ ከርሳሙ ብርሃኑ ነጋም፣ ውሻው ዳንኤል ክብረትም፣ ከአንዱ መንግስት ወደ ሌላው የሚገለባበጠው ስንዝሮው ታየ አፅቀ ስላሴም፣ ከደርግ ጀምሮ የሚልከሰከሰው የወባ ዶክተሩ ተቀዳ ዓለሙም፣ የመለስ ዜናዊ ቡችላ ዶር ፈቃዱ ገዳሙም፣ አቶ እርስቱ ይርዳውም፣ አቶ ስዩም ተሾመም ቢጠየቁ መልሳቸው ከዚህ የተለየ አይሆንም። መንግስት ለምን ሰዎችን ያፈናቅላል፣ ያስራል፣ ለምንስ ይገድላል ስትላቸው ግን መልስ የላቸውም።
You love a pacifist, disarmed, weakened and docile Gurage.
You love it when Gurage refuses to adapt to changing political philosophies to conform to polutical realities in Ethiopia.
What kind of love is Amara love of Gurage?

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Selam/ » 23 Sep 2024, 23:32

ፕስስስስ!

የላፕ ቶፕ አርበኛው - ቀበቶ ከታጠቀህ፣ ለዘብተኛ የምትላቸውን ህዝቦች ምድር ላይ ወርደህ ማነቃቃት ነው፣ እዚህ ፎረም ላይ አየር በአየር እንደ በቆሎ ከምትንጣጣ!

Dama wrote:
23 Sep 2024, 22:08
Selam/ wrote:
23 Sep 2024, 20:56
ይኸንን ርዕስ በጣም እወደዋለሁ።

አንደኛ ፡ የጉራጌ ህዝብ ከግራና ከቀኝ በጎጠኞችና ጅቦች ቢቦጫጨቅም፣ ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ አይልም።

ሁለተኛ፥ አንድን ጎሳ ጠቅልሎ የሚሳደብና የሚያጠቃ ወራዳ ብቻ ሳይሆን ዕርጉም ነው።

ሶስተኛ፥ ካድሬነት ጎጥ አይወስነውም። የኦሮሞ፣ የትግሬና የአማራ ካድሬ እንዳለ ሁሉ፣ የጉራጌ ካድሬም ግጥም አድርጎ አለ። የተማሩ ካድሬዎችና የመንግስት ተላላኪዎች ለምን ከገዳይ ፖለቲከኞች ጋር ትሰራላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም መልሳቸው አንድ ዓይነት ነው፥ “ሃገሬን ለማገልገል ነው!” That’s a bullsh!t!

የጨቦ ጉራጌን ያስጨረሰው አቶ ገስግስ ገብረ መስቀልም፣ ከርሳሙ ብርሃኑ ነጋም፣ ውሻው ዳንኤል ክብረትም፣ ከአንዱ መንግስት ወደ ሌላው የሚገለባበጠው ስንዝሮው ታየ አፅቀ ስላሴም፣ ከደርግ ጀምሮ የሚልከሰከሰው የወባ ዶክተሩ ተቀዳ ዓለሙም፣ የመለስ ዜናዊ ቡችላ ዶር ፈቃዱ ገዳሙም፣ አቶ እርስቱ ይርዳውም፣ አቶ ስዩም ተሾመም ቢጠየቁ መልሳቸው ከዚህ የተለየ አይሆንም። መንግስት ለምን ሰዎችን ያፈናቅላል፣ ያስራል፣ ለምንስ ይገድላል ስትላቸው ግን መልስ የላቸውም።
You love a pacifist, disarmed, weakened and docile Gurage.
You love it when Gurage refuses to adapt to changing political philosophies to conform to polutical realities in Ethiopia.
What kind of love is Amara love of Gurage?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6848
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Naga Tuma » 23 Sep 2024, 23:33

sesame wrote:
23 Sep 2024, 16:32
Gurages were originally Eritreans from GuraE! በኤርትራውያንና ጉራጌዎች መሃከል ቅራኔ ሊኖር ኣይችልም። ጉራጌዎች ከጉራዕ፡ ኤርትራ፡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ የፈለሱ የነኛ ሰዎች ናቸው። Gurages are "our people in Ethiopia." በደርግ ግዜ፡ "ኤርትራ ኣትሸጥም: ኣትለውጥም" ሲባል የሰማ ኣንድ ኣራዳ ጉራጌ፤ "ለምን ኣትሸጥም፡ ትርፍ ካላት ትሂድ እንጂ" ኣለ ይባላል። That is how Guraghes supported our independence struggle. :lol: :lol: :lol:
እንደ ዛሬ በኣንድ ኣፍታ ብዙ ስቄ ኣላዉቅም።

ለካስ ኤ ኤም ሲ ኢ ነህ። ናቅፋ ከመሸጉት ኣንዱ ትመስለኝ ነበር።

እንዳይገነጠሉ ኣማላጅ ትሆናለህ ብትባል ስንጋፖር ያደርሱኛል ብለህ ኣብረህ ተገነጠልክ።

ኣሁን የድሮ ባህራችን ላይ በኣንድ በኩል ኔቪ፣ በሌላ በኩል እሬቸ ሲባል ሰምተህ ስንጋፖር ህን ጅሩ፣ ፅዋን ጅረ ብለህ እስከነወደቡ ለመደራደር የጉራጌን ቀልድ ኣመጣህ?

ያሳቀኝ ድሮ ኤ ኤም ሲ ኢ ሆነህ ከጉራጌ የገዛሀዉን ኮትህን ገልበጥ ስታደርግ ጥበበኛዉ ጉራጌ ዉስጡ የሰፋዉ ተነቦ ኤ ኤም ሲ ኢ መሆንህ ተለየ። ከሌላ ኤ ኤም ሲ ኢ ያልተዋስክ ካልሆነ።

ኣማላጅነትህን ዘንግተህ ቀድሞ ተሰላፊ ለመሆን ጠጋ ጠጋ ማለት ዬለም። የዘንድሮ ጉራጌ ትርፍ ካመጣች ትመለሳ የሚል ኣይሆንም? ካልሆነ የሶሎሎ እና እዲ ሎላ ዐይን ቀለሞች መሃል ምን ልዩነት ኣለ የሚለዉን ቦረና ለሌላ ኣማላጅነት መላክ ነዉ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17010
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የወትሮው ቅራኔው በሻዕብያ-ኤርትራ እና ወያኔ መካከል መሆኑ ቀርቶ አሁን በሻዕብያ-ኤርትራ እና ጉራጌ መካከል ሁኗል። ለምን? ሻዕብያን ያስፈራው ትልቅ ውርጅብኝ ዶፍ ያዘለ ደመና አለ።

Post by Selam/ » 24 Sep 2024, 00:15

ሴሰኛው - ተረት ተረት ስለምትወድ ፣ እኔም ደግሞ አንዲት ታሪክ ላጫውትሃ።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ሰንጋ ተራ አካባቢ የሚያውደለድሉትን ጓደኞቻቸውን ለምንድነው ለመገንጠል የመረጣችሁት ብለው ሲጠይቋቸው፣ “በቃ የውጭ አገር እንሆናለን!” አሉ፣ ከውጭ ሃገራታም መካከል በአንደኝነት ሲንጋፖርን መረጡ።

Post Reply