Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dama
Member+
Posts: 6451
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Horus: Demera for you

Post by Dama » 11 Sep 2024, 23:08

Woth a cross towring on top

https://vm.tiktok.com/ZMhetURob/

Horus
Senior Member+
Posts: 40221
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Horus: Demera for you

Post by Horus » 12 Sep 2024, 00:23

ዳማ፣
እኔ በምመጣበት ካልቸር የመስክረም ወር በሙሉ የብርሃን ክብር ወይም ክብረ ብርሃን ወር ነው። በሰኔ 12/13 የቡሄ እለት የምጅር ማይ ይባላል ። ምጅር ደመራ ማለት ሲሆን ማይ ማለት ቀን ወይም እለት ማለት ነው ። የደመራ ረጃጅም አጠናዎች ተልጠው የሚተከሉት የዚያ ቀን ነው። ከዚያ በኋላ የምናደርገው ገድራ በሚባል በጣም በሚቃጠል ቁጥቋጦ እናሰባዋለን ። ምጅር ማስባት ይባላል ። ይህ ሁሉ የጎረምሳ ስራ ነው።

ከአክራሚ (ዛሬ አክራሚ ነው) አዲስ አመት መለወጫ ቀን ማለት ነው። ከነገ ጀምሮ ማታ ማታ ጸሃይ ጠልቆ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ልጃገረዶ በደመራው ዙሪያ አበቤ አበቤ የተባለ ዘፈን ይዘፍናሉ ፣ ቆሎ ይዘው መጥተው ይበላሉ እስከ መስቀል ድረስ ለ15 ቀናት ። ጎረምሶች ይጠብቋቸዋል ፣ ቤት ያመጧቸዋል።

የመስቀል ዋዜማ ማታ (እኛ ማታ ነው የምናቃጥለው) አንዳንድ አገር የመስቀል ጠዋት የሚያቃጥሉ አሉ ።

ከነገ ጀምረን ሌላ ስራችን ችቦዎች ለያንዳንዱ ቤት ውስጥ ባለ ሰው ልክ እናስራለን ። ችቦ የሚሰራበት ያ ገድራ የሚባለው ቁጥቋጦ ነው ። እንደ ቤንዚል ነው የሚነደው ። የችቦ ውፍረትና ርዝመት እንደየሰዉ እድሜና ማዕረግ ነው ። እጅግ ግዙፉ ለአያቶች ነው። ቀጥሎ ላባትና እናቶች ነው ። ቀጥሎ ለታላላቅ ወንድሞች እያለ ፣ ለትንሹ ልጅ ትንሽ ይሰራለታ ። ደመራ መሄድ ለማይችሉ ጎረምሳ ይዞላቸው ይወጣል ።

የችቦ እሳት አጀማመር ሴራ አለው ። አንዱ የቤቱ አያት ወይም አያት ከሌላ አባት ትልቁን ችቦ ቤት ውስጥ ከምድጃ ይለኩስና የቤቱን ችባን (እችባ) 3 ግዜ ከወጋው ፣ከባረከው በኋላ ይዞት ደጅ ወጥቶ የቀረው ሰው በሙሉ በእድሜው ተራ ከአያት ወይም ከባት ችቦ ነው የምንለኩሰው እንጂ ሌላ ማምን ሰው ከምድጃ አይለኩስም ። ከዚያ ኤቦ ኤቦ እየተባለ ወደ ደመራው እንሄዳለን ። ደመራው የጋራ ደመራ ከሆነ የሰፈሩ ባሊቅ ፣ ታላቅ ሰው መጀመሪያ ደመራውን በችቦው ሶስቴ አስነክቶ እሳቱን ይጀምራል ። ከዚያም ሁሉም ሰው እንደ እድሜር ቅደም ተከተል ችቦውን ይወረውራል ።

ምጅርና መስቀልን የሚያክል ታላቅ ነገር በጉራጌ የለም ። ጉራጌ የብርሃን ሕዝብ ነው ። ብርሃን ሰላም ነው፣ እውቀት ነው፣ ብርሃን ዊዝደም ነው ። የሕይወት ሁሉ ምንጭ ብርሃን ነው! ይህ ነው የመስቀል ምስጢር ለጉራጌ !

የዛሬ 10 አመት
Last edited by Horus on 12 Sep 2024, 00:50, edited 1 time in total.

Dama
Member+
Posts: 6451
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: Horus: Demera for you

Post by Dama » 12 Sep 2024, 00:34

Addis amet yimech
Amen!

Horus
Senior Member+
Posts: 40221
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Horus: Demera for you

Post by Horus » 12 Sep 2024, 01:00

Dama wrote:
12 Sep 2024, 00:34
Addis amet yimech
Amen!
አንተም ይመችህ
አዲሱ አመት ላንተም ነው!
ክርስቲያንና ሙስሊም ጎረቤት ጉራጌዎች ሁለቱም ነው የሚያከብሩት ! እኛ ጋ በመሃላችን ሙስሊሞች ካሉ ሆን ተብሎ ስጋ ያልሆነ ነገር አይብና ጎመን ክትፎ ተሰርቶላቸው ነው የሚጋበዙት!! መስቀል ማለት አረፋ ነው! በቃ

Post Reply