Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40247
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ የጎላ ሰፈር ጅብ እየበላው ከምዬ ምኒልክ ጋር አዲሳባን ያቀና ሕዝብ ነው!

Post by Horus » 12 Aug 2024, 00:19

ዛሬም የጉራጌ ህጻናት የሚዘፍኑት አዲሳባ ሄደው ዳገቱ ላይ ፎቅ ስለ መስራት ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 40247
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ የጎላ ሰፈር ጅብ እየበላው ከምዬ ምኒልክ ጋር አዲሳባን ያቀና ሕዝብ ነው!

Post by Horus » 12 Aug 2024, 02:42

ቲያጎ፣
ቢያንስ ስለ ጉራጌ አሰፋፈር ትንሽ ስለምታውቅ ትመሰገናለህ ። እኔ የ7ኛና መሳለሚያ ልጅ ነኝ ። ይህን የምታየው ጉድ ከምጣቱ በፊት እራሱ የአማኑኤል መሳለሚያ ድንጋይ ክምር እስከነ የእንጨት መስቀል ፅ ይለኛል ! ለዚህ ጉራጌዎቹ አዳነችን በነካ እጅሽ ነይና አፍርሺ እያሏት ያሉት! ደሞ አይቀርም !!

ከላይ የጠቀስኩት ታሪክ ግን እውነተኛ ታሪክ ነው ። አጼ ምኒልክ 4 ኪሎን ሲገነቡ ከህንድና አርመኖች ጋራ የሰሩት የጉራጌ አናጺዎችና የጉልበት ሰራተኞች ናቸው ። ግማሾቹ አሁን የፈረሰው የፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ነበር የሚኖሩት ። ሰራተኛ ሰፈር የተ ባለውም ለዚያ ነው ። ግማሾቹ ጎላ ሰፈር ከሴጣን ጀርባ እስከ ተክለ ሃይማኖት ያለው ጫካ ውስጥ ነበር የሚኖሩት ። አዲስ አበባ በጅብ የተሞላ ደን ነበር ። ፊር በር 4 ኪሎ ሲሰሩ ወለው የሆነ ቦታ ከመሸባቸው ጫካ ለጫካ ወደ ጎላ ሰፈር ሲሄዱ በጅብ ይበሉ ነበር። አጼ ምኒልክ ጉራጌዎችን እጅግ ይወድ ስለነበር ፊታራሪ ሃብቴን ምነው ጥቂት ያንተ ሰዎች ከጉራጌ አምጥተህ አዲሳባ ቤት እንዲሰሩ አታደርግም ባሉት መሰረት ነው የዛሬ አሜሪካ ግቢ እስከ ጎላ ሰረ የጉራጌዎች ሰፈር የሆነው። (ምኒልክ የቤቶች ቁጥር በርክቶ እንዲከተም ጉጉት ስለነበረው)። ትግሬና ኤርትራ መጥተው ደቀ መሃሪ የተባለው ሰፈር ተክለ ሃይማኖት እስከ መጡ ድረስ! ሌሴ ገበረ ማሪያም ጋሪ ት/ቤት አሁን ያለበት ቦታ ሁሉ ጎላ ሰፈር ነበር ። ስለዚህ ያዲሳባ ማበብ ለጉራጌ ትልቅ ትርጉም አለው !! አሁን ኮሪደሩን አዲስ ከተማና ቡታጀራ ማድረስ ነው የቀረን!

Odie
Member+
Posts: 6231
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ጉራጌ የጎላ ሰፈር ጅብ እየበላው ከምዬ ምኒልክ ጋር አዲሳባን ያቀና ሕዝብ ነው!

Post by Odie » 12 Aug 2024, 07:21

Horus wrote:
12 Aug 2024, 02:42
ቲያጎ፣
ቢያንስ ስለ ጉራጌ አሰፋፈር ትንሽ ስለምታውቅ ትመሰገናለህ ። እኔ የ7ኛና መሳለሚያ ልጅ ነኝ ። ይህን የምታየው ጉድ ከምጣቱ በፊት እራሱ የአማኑኤል መሳለሚያ ድንጋይ ክምር እስከነ የእንጨት መስቀል ፅ ይለኛል ! ለዚህ ጉራጌዎቹ አዳነችን በነካ እጅሽ ነይና አፍርሺ እያሏት ያሉት! ደሞ አይቀርም !!

ከላይ የጠቀስኩት ታሪክ ግን እውነተኛ ታሪክ ነው ። አጼ ምኒልክ 4 ኪሎን ሲገነቡ ከህንድና አርመኖች ጋራ የሰሩት የጉራጌ አናጺዎችና የጉልበት ሰራተኞች ናቸው ። ግማሾቹ አሁን የፈረሰው የፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ነበር የሚኖሩት ። ሰራተኛ ሰፈር የተ ባለውም ለዚያ ነው ። ግማሾቹ ጎላ ሰፈር ከሴጣን ጀርባ እስከ ተክለ ሃይማኖት ያለው ጫካ ውስጥ ነበር የሚኖሩት ። አዲስ አበባ በጅብ የተሞላ ደን ነበር ። ፊር በር 4 ኪሎ ሲሰሩ ወለው የሆነ ቦታ ከመሸባቸው ጫካ ለጫካ ወደ ጎላ ሰፈር ሲሄዱ በጅብ ይበሉ ነበር። አጼ ምኒልክ ጉራጌዎችን እጅግ ይወድ ስለነበር ፊታራሪ ሃብቴን ምነው ጥቂት ያንተ ሰዎች ከጉራጌ አምጥተህ አዲሳባ ቤት እንዲሰሩ አታደርግም ባሉት መሰረት ነው የዛሬ አሜሪካ ግቢ እስከ ጎላ ሰረ የጉራጌዎች ሰፈር የሆነው። (ምኒልክ የቤቶች ቁጥር በርክቶ እንዲከተም ጉጉት ስለነበረው)። ትግሬና ኤርትራ መጥተው ደቀ መሃሪ የተባለው ሰፈር ተክለ ሃይማኖት እስከ መጡ ድረስ! ሌሴ ገበረ ማሪያም ጋሪ ት/ቤት አሁን ያለበት ቦታ ሁሉ ጎላ ሰፈር ነበር ። ስለዚህ ያዲሳባ ማበብ ለጉራጌ ትልቅ ትርጉም አለው !! አሁን ኮሪደሩን አዲስ ከተማና ቡታጀራ ማድረስ ነው የቀረን!
>>>>>>>>>>>>>
ስለ አጭር ታሪካዊ ትውስታው እናመስግናለን ሆረስ!
ጉራጌ የአዲስ አበባን ጫካ ሲመነጥር ኦሮሙማ ያኔ የት ነበር ነው ጥያቄው? ማን ከለከለው? ዴሞግራፊ ደባ ተስራብኝ ሲል የነበረው? ዛሬ ከመሽ መጥተው ሁሉንም ኬኛ የሚሉት!!
ጉራጌ ስም እየተጠራም ቢሆን ይህችን አንካሳ አርገው እንዳትንቀሳቀስ ያደረጉዋት አገር ውስጥ ያደረገው አስተዋፅኦ በቁጥር እንበዛለን ከሚሉት ቢበልጥ አንጂ አያንስም:: ወያኔ መሬት እስጣለሁ ብር አምጡ ተመዝገቡ አለና ጉራጌዎችን ለቅሞ ብርጭቆ ይሁን ጠርሙስ ፋብሪካ ነው አስኮ ስብስቦ ወረወረ:: የተናደዱ ይሄ ዘረኝነት ነው ብላው ጥለውለት ከአገር ወጡ:: አብይ አህመድ ግራኝ ጉራጌን ክልል ላለማድረግ የፈፀመው ግፍ ታስታውሳለህ:: ዛሬም ኮሪደር እያለ በዘር ተዋፅኦ ቢስራ የሚገረም የለም:: በፊውዳል ዘመን ስራተኛ ብሎ ስው ላለመጥራት በዘሩ ነበር የሚጠራው:: ምድሪቱ ላይ የነበረው ድንቁርናና ጥጋብ አሃዝ የሚገልፀው አልነበረም:: ሌላውን የሚያንቋሽሹ ብዙ የፖለቲ ምላስ ረጅሞች ነበሩ:: ዛሬም አሉ:: አብዛኛው ያለመስልጠናችን ያለማወቃችን ጥልቀት ማሳያ ነው!!
ኢትዮዽያ በቅርብ ግዜ ሙሉ በሙሉ ልትለወጥ አትችልም:: ምናልባት ደንቆሮ ዘረኞች ጨርስው ካላፈረሱዋት incremental change ታመጣ ይሆናል:: አንድ dictator ከላይ ሳይወርድ ሌላው ዲክቴተር መስላሉን መውጣት የሚጀምርበት አፍሪካ/አገር ነው ያለነው:: ያ ስልጣን የያዘው ደንቆሮ በጉልበት አገር ለማልማት እየሞከረ ንፍጥ ይለቀልቃል:: ያላዋቂ ሳሚ ማለት ነው:: አገር በጉልበትና በመንግስት አይለማም በፖሊሲ በህዝብ ተሳትፎና ኢንቨስትመንት እንጂ!!
ቸር ይሁን!

Post Reply