በደቡብ ምሥራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ የፓርቲው አባላት “ጉባኤው በዚህ ጊዜ እንዳይካሄድ” የሚል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፣ በስብሰባው የ24 ቀበሌዎች ተወካዮች መገኘታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል
የእንደርታ ወረዳ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ስላስ ሃፍቱ ሕዝቡ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ባለበት እና በፓርቲው ውስጥ አንድነት በሌለበት ሁኔታ ጉባኤ መካሄድ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንዳልሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር እና ምክትላቸው አንድ ባልሆኑበት፣ የቁጥጥር ኮሚሽኑ ሊቀመንበሩን ጨምሮ አባላቱ በሌሉበት ጉባኤ ማካሄድ ተገቢ አይደለም” ብለዋል።
ወይዘሮ ስላስ ተሰብሳቢዎቹ ፓርቲው በአባላቱ የቀረበውን ሀሳብ እንዲያዳምጥ መማጸናቸውንም አስታውሰዋል።
“ከዚህ በፊት የአባላቱን ድምጽ የሚሰማ ድርጅት ነበር፤ ፓርቲው ወደ ቀድሞው ባህሪው ሊመለስ ይገባል። ከዚህ ውጪ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ አይደለም።”
በክልሉ ውስጥ “ከፌዴራል መንግሥት እና ከምርጫ ቦርድ እውቅና ሳይሰጠው የህወሓት ጉባኤ መካሄድ ለሕዝብ አጥፊ እና የማይጠቅም ነው” የሚል አቋም የያዙ ሰዎች እንደነበሩ ተናግረዋል።
“የቁጥጥር ኮሚሽኑ አባላት በሌሉበት፣ ሁለት ሰዎች ከአዘጋጅ ኮሚቴው በቀሩበት፣ በአጠቃላይ በፌዴራል መንግሥት ላይ እምነት በሌለበት ሁኔታ እና ብዙ ሰዎች ከአዘጋጅ ኮሚቴው ራሳቸውን ባገለሉበት ሁኔታ ውስጥ ጉባኤ ማካሄድ አደጋ ሊያመጣ እንደሚችል መረጃዎች አሉ፤ እኔም ይህንን ተገንዝቤ ነው ራሴን ያገለልኩት” ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpdll7v6jvpo