የካድሬዎች የፖለትካ ቅስቀሳ በተፈጥሮ የተቀራረቡ ማህበረሰቦችን ማራራቅ ነዉ።
ለምሳሌ በኦሮምኛ ቃሉ እና በአማርኛ ቃልቻ መሃል የተፈጥሮ ልዩነት ያለ ኣይመስለኝም።
ቢሆንም ኣንድ ግዜ የኦሮሞ ቃሉ እና የአማራ ቃልቻ የተለያዩ፣ ኣንዱ በጎ፣ ሌላዉ መተተኛ ናቸዉ ዐይነት የካድሬ ክርክር ሰምቼ ወይም ኣንብቤ ታዝቤ ነበር።
የሳቀ እና ሴቄን መመሳሰል ኣስተዉዬ ያቤሎ ምን ይል ይሆን ብዬ ኣንድ ግዜ እዚህ ፎረም ላይ ፅፌ ነበር።
በቅርቡም የሃሳ እና ሂስ፣ ሂሳብ መመሳሰልም ኣስተዉዬ ነበር።
ያቤሎ እነሱ የእኛን ባህል ኣይዘፍኑም የሚል ስሞታ ሲፅፍ የራስን ባህል ባለቤቱ ነዉ የሚዘፍነዉ ወይስ ሌላ እንድዘፍንለት ይፈልጋል ብዬ ብጠይቀዉ ትንሽ ሰንብቶ የአቡሽ ዘለቀን ምርጥ የቦረና ባህል ዘፈን ይዞ ብቅ ኣለ።
እንዳዛ ነዉ እንጂ ያስብላል።
የትግርኛ ሜሎዲ ከኦሮምኛ ኤነርጂ ጋር የተገናኙ የባህል ጭፈራ ስያጋጥም ማህበረሰቦች የሚቀራረቡት እንዲህ ነዉ እንጂ ያስብላል።
ኦሮምኛንም ማስተማር በመናገር እና በመፃፍ ነዉ።
እዚህ ፎረም ላይ ኣልፎ ኣልፎ በኦሮምኛ የሚጽፍ ድፌንድዘትሩዝ ነዉ።
ሆረስ በምያዉቀዉ ፊደል ድፌንድዘትሩዝ ኦሮምኛን ሲጽፍ ሆረስ የምያዉቃቸዉን የጉራግኛ ቃላት እያነበበ ዘለል ዘለል እያለ ኤቦ ላሌ የሚለዉን የጉራግኛ ዘፈኑን ትቶ የወለዳቸዉን ኣምጥተዉ እንዳስቆጠሩት የአርሲ ኣዛዉንት ኩንስ ክያ እያለ ይመስላል።
ኦሮምኛ ሳልስ ይበዛበታል ሲባል ሰምቶ ሳድስ የሌለዉ መስሎት ይሁን የምያዉቀዉን የጉራግኛ ቃል ስርነን ኦሮምኛ ሲርና ኣለዉ ብሎ ይጽፋል። ህን ደንደኡን ሂንደንደኡ ብሎ ይጽፋል። እናርማለን እንጂ ተኮላተፈ ኣንልም።
የአማርኛ ፊደል ወዳድ ኦሮምኛ እንደዛ የቋንቋ ወንዝን ይሻገራል።
አማርኛ ጠል ኦሮምኛ መኪናን ኮንኮላታ ይል ነበር። ኮንኮላታ ማለት ተንከባላይ ማለት ነዉ። የመኪናን መፈጠር ረቂቅ በኣንዴ ይደልዛል። ማሽን መሆኑን ኣዘናግቶ እንደ ድንጋይ የሚንከባል ያስመስለዋል። አማርኛ መኪናን ኣልፈጠረም፣ ቃሉን ተጠቀመ እንጂ።
አማርኛ መኪናን ቀድሞ ስለተጠቀመ ኮንኮላታ እንበለዉ ካልተባለ ኦሮምኛም መኪናን መኪና ብሎ ቢጠቀም ችግር ነበረዉ?
መጽሓፍ ቅዱስ በኦሮምኛም ሆነ በአማርኛ ይዘቱ ተመሳሳይ ነዉ። ስሙ ወደ ኦሮምኛ ሲተረጎም መጫፈ ቁልቁሉ ተባለ።
ይህን ስያሜ ከሰማሁ ግዜ ጀምሮ ሳስታዉስ ሁሌ ይገርመኛል። መጫፈ ምን ማለት ነዉ? የኦሮምኛ ቃል ነዉ? ወይስ ተዉሶ ነዉ? መጽሓፍ በቶሎ ቶሎ መጫፈ ተብሎ ነዉ? መጻፈ ማለት ያስቸግራል ተብሎ ነዉ?
ቁልቁሉ ንጹህ ማለት ነዉ። ስለዚህ መጽሓፍ ቅዱስ በኦሮምኛ ንጹህ መጽሓፍ ተባለ ማለት ነዉ? መጽሓፍ ቅዱስ ንጹህ መጽሓፍ ነዉ ወይስ የሃይማኖት መጽሓፍ ነዉ?
መጻፈ ኤበማ ወይም መጻፈ ኤብፈማ ወይም መጻፈ ኤብፈሜ ተብሎ የነበረ ቢሆን አማርኛ ወዳድ ትርጉም ያደርገዉ ነበር?
ላስተዋለ ኣእምሮ ይህ ታሪክ ምንን ያመለክታል? አማርኛ ጠል ኦሮምኛነትን ኣይዴለም?
አማርኛ ጠል ኦሮምኛነት ከሆነ መነሻዉ ከየት ነዉ? ዉስጣዊ ወይስ የዉጪ ተጽዕኖ ነዉ?
አማርኛ ከመነሻዉ ኦሮምኛ ጠል ነበር? ትግርኛ ጠል ነበር? ቢሆን ኖሮ በትግርኛ እና በኦሮምኛ ቃላት የዳበረ ኣይሆንም ነበር።
ሎሬት ጸጋዬ ቦረና ሄዶ ለካ ኣንተ ነህ ካለ ኣሁን ስልሳ ዓመታት ተቆጥረዋል። በሪሳ መታተም የጀመረዉ ከዛሬ ኣርባ ዓመታት በፊት ነዉ።
ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እዚህ ፎረም ላይ ኦሮምኛ እንደ ወፍዘራሽ ነዉ የምያጋጥመዉ።
በአማርኛ ወዳድ ፊደል ኣለመቀጠሉ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደነበረዉ መገመት ይቻላል?