Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40256
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያዊነት ርዕዮት ምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Aug 2024, 02:48

የኢትዮጵያን ሕብረተ ሰብ ማደራጃ ርዕዮት ኢትዮጵያዊነት ይባላል

የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ አገር፣ መንግስት፣ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ካልቸር ማደራጃው መርህ ምንድን ነው? ማደራጃው ፍልስፍና ፣ ቲኦሪ ፣ ስልት ወይም ተግባር ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ማደርጃው ብቸኛ ሃሳብ ምንድን ነው?

ኢትዮጵያዊነት ነው!

ኢትዮጵያዊነት ማለት ጠንካራ ያገር አንድነት ፣ የተረጋጋ አገርና ትንካራ አገርና መንግስት ማለት ነው ። ኢትዮጵያዊነት ማለት ዴሞክራሳዊት፣ ፍትሃዊት፣ ሕግ ገዝ፣ የነጻ ሕዝብ አገር ኢትዮጵያ ማለት ነው ። ኢትዮጵያዊነት ማለት የበለጸጉ ፣ ከድህነት ነጻ የወጡ ፣ የተማሩ ጤነኛ ፣ በችሎታና ብቃት የበለጸጉ ዜጋዎች አገር ማለት ነው ። ኢትዮጵያዊነት ማለት የተራማጅነትና ፈጣሪነት ካልቸር ፤ የአረንጓዴ ካልቸርና ከተፈጥሮ ጋራ የታረቀ በፈሪሃ ፈጣሪነት የሰክነ ባህል ወይም ካልቸር ማለት ነው።

ኢትዮጵያዊነት እንደ ስልጣኔ የ21ኛው ዘመን የውሃ ስልጣኔ ማለት ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 40256
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያዊነት ርዕዮት ምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Aug 2024, 21:56

ኢትዮጵያዊነት ማለት ማንም ሰራው ማንም ፈየደው አዲሳባ ስታምር ኢትዮጵያ አረንጓዲው ስትሆን እሰይ እልል ማለት ነው! በኢትዮጵያ አንዲት መልካም እርምጃ አይኑ ደም የሚለብስ ተገንጣይ ጸረ ኢትዮጵያ ብቻ ነው!
ዝናብ ጸጋ ነው ! ይዝነብ ምድሯም በውሃ ትሞላ! ውሃ ነጭ ወርቅ ነው!



Post Reply