Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6879
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያን እንወቅ፥ የ16ኛዉ ክፍለ ዘመን የቦረና ጄኔራሎች እነማን ነበሩ?

Post by Naga Tuma » 28 Jun 2024, 17:59

ኢትዮጵያ ስም ወይም ስያሜ ነዉ። ከስያሜዉ ጀርባ ዜጎች የሚኖሩባት ሃገር ነች።

የየትኛዉም ሃገር ዜጎች መሠረታዊ የፖለትካ ጥያቄ እኩልነት ነዉ።

የራሳቸዉን አስተዳደር መመስረት የሚችሉ እና አስተዳዳሪያቸዉን መወከል የሚችሉ ዜጎች የፖለትካ ጥያቄ ተፈቶ የልማት እና የእድገት ግስጋሴን ይከተላሉ።

ከጥንት ግዜ ጀምሮ የዛሬ የኢትዮጵያ ዜጎች በባህላቸዉ ዉስጥ ተቀርጾ ለዘላለም የሚኖር ኣንድ ነገር ምንድነዉ ቢባል መለኮት ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጥንት ግዜ ሙሴ ሰማሁኝ ያለዉ መለኮታዊ ግላጼ እና የዚህ ዘመን ቃሉ ወይም ቃልቻ ይገለጽልኛል የሚል መካካል ምን ልዩነት ኣለ ቢባል ማብራራቱ ቀላል ኣይመስለኝም።

ጥንት ግዜ እና እዚህ ዘመን መካካል የተሰየሙት ሁለቱ ምንልኮችም ጽንሰ ሀሳባቸዉ ስለ መለኮት ነዉ። መለኮት ምን ይልክ ይሆን እንደማለት ነዉ። ኣይዴለም?

ስለዚህ ሙሴ፣ ቀዳማዊ ምኒልክ፣ ዳግማዊ ምኒልክ፣ እና ቃሉ ወይም ቃልቻ ማለት ከተቻለ ኢትዮጵያ ተብላ የተሰየመችን ሃገር ማወቅ ከባድ ኣይዴለም።

መለኮት በሳይንስ እንዴት ይዘረዘራል የሚለዉ ሌላ ጥያቄ ነዉ። አሰራሩን እንደ ሙሴ የተገለጠላቸዉን መጠየቅ ነዉ።

ይህ ሁሉ ታዉቆም ሆነ ሳይታወቅ፣ ከዉጪ የገባ ጫና ተጨምሮበት፣ ኢትዮጵያ በእኩልነት ወደፊት ከመገስገስ ለዓመታት ተሽመድምዳ ሰነበተች።

ኢትዮጵያ በእኩልነት ወደፊት እና ከኢትዮጵያ ዉጪ ሌላ ሃገር ባዮች መካካል የነበረዉ ክርክር የመሽመሽመዱ ዋና ምክንያት ነበር ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም።

ከዛ መሽመድመድ ፎቀቅ ስትል በእኩልነት ወደፊት በሚሉ እና በሃገር ዉስጥ ሃገር የማለት ቅዠት ዉስጥ መሽመድመድ የሚታያቸዉን የምትታዘብ ሃገርም ሆናለች።

ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም ዋነኛዉ የ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ታሪክ መሆኑ ይፋ ወይም እፋ ነዉ።

በ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ሰዎች ከሸዋ ወደ ቦረና ተሰደዉ ነበር የሚል አፈታሪክ ቢኖርም በ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ከቦረና ወደ ሸዋ መጥተዉ እስከ ወለጋ መዝለቃቸዉ በሰፊዉ ተመዝግቧል።

ለምሳሌ በልጅነት ሰሰማ ያደኩኝን አፈታሪክ የሚከተለዉ ቪድዮ ከፊሉን ይዘግባል።



በ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ወልሶ አከባቢ የደረሰዉ የቦረና ሰዉ ጎሳ በአከባቢዉ ይኖሩ ከነበሩት ጎሳዎች ጋር ተጋብተዉ ተዋልደዉ እንደ ኣንድ ማህበረሰብ ለዘመናት በሰላም ኖረዋል።

ለኣካዳሚ ስራ ወለጋን ለኣጭር ግዜ ሄጄ ዋና መንገዱን በኣብዛኛዉ ኣይቻለሁ።

ወልሶ እንደደረሰዉ የቦረና ሰዉ ወለጋ ድረስ የዘለቁት የቦረና ሰዎች እነማን እንደነበሩ ባላዉቅም ምስራቅ ወለጋ ዉስጥ ኦሮምኛ የሚናገሩ ጉሙዞች፣ ምዕራብ ወለጋ ዉስጥ ኦሮምኛን የሚናገሩ ኣኙዋዎች በኣጭር ቆይታዬ ዉስጥ ኣጋጥመዉኛል።

እስከዛሬ ድረስ መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች በኣብዛኛዉ የኣኙዋ ወይም የቦረና ጎሳዎች መሆናቸዉን ነዉ።

ከየትኛዉ ጎሳዎች ይሁን ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ ነባሩ እና ከቦረና የመጡት ጎሳዎች ለዘመናት ተጋብተዉ ተዋልደዉ በሰላም የኖሩ ከሆነ፣ ምስራቅ ወለጋ ዉስጥ ነባሩ እና ከቦረና የመጡት ጎሳዎች ለዘመናት ተጋብተዉ ተዋልደዉ በሰላም የኖሩ ከሆነ፣ ምዕራብ ወለጋ ዉስጥም ነባሩ እና ከቦረና የመጡት ተጋብተዉ ተዋልደዉ በሰላም የኖሩ ከሆነ ሁሉም አስተዳደሮቻቸዉን ኣስተካክለዉ ወደ ልማት እና ዕድገት መገስገስ ይችላሉ ብሎ ማሰብ ኣይከብድም።

ሌሎች አከባቢዎችንም እንደዚሁ ማሰብ የሚቻል ይመስለኛል።

እንደዚህ ማሰብ ሲቻል ነዉ ሃገሩ በእንደዚህ ዓይነት ስብስብ ተሽመድምዳ የነበረችዉ። እንደዚህ ዓይነት ስብስብ ለብቻዉ ቢተዉ እርስ በእርሱ የሚፋጅ ጥርቅም የሚሆን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነዉ። በኣጭር ግዜ ኣንድ ላይ ኣሰባስቧቸዉ የነበረዉ ኣንዱ ምክንያት ሕወሃትን መቃወም ነበር።

እንደዚህ ዓይነት ስብስብን ኢትዮጵያ ከእርስ በእርስ ፍጅት ማትረፏ ባለዉለታዉ ነች።

ለዚህ የእርስ በእርስ ፍጅት ስብስቡ መንገድ ላይ እንደነበረ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ። ንፁህ የሆነ ኦሮሞ እና ንፁህ ያልሆነ ኦሮሞ በማለት። በዚህ መስፈርት ኦቦ ዮሓንስ ለታ እና ፕሮፌሰር መረራ ጉድና ለመሪነት ብቃታቸዉ ዉድቅ ይሆናል። ይህ መላምት ሳይሆን ከዓመታት በፊት ሰምቼ ታዝቤ ያለፍኩኝ ነዉ።

እነዚህ ሁለት የኢትዮጵያ ዜጎች የዜግነት ሙሉ መብታቸዉ ወደሚነፈግበት መንግድ ሲነጉዱ የነበረ ግዜ ምን እያሰቡ እንደነበረ ማወቅ ያዳግተኛል።

ወለጋ ዉስጥ ንፁህ ኦሮሞ የሚባልን ለመድሃኒት ፈልጎ ማግኘት ይቻላል ቢባል መመለስ ያዳግተኛል። ብያንስ ከቦረና ርቆ ያለ መሆኑ ለመልስ ያስቸግራል።

ይባስ ብለዉ ሌላን መዉቀስ ካራስ ድክመት ማስቀደም የማይከብዳቸዉ ከቦረና መጥቶ የተቀላቀለዉ የራሱን ጎሳ ወገን ነባሩን ጎሳዎች ባዕድ ብሎ መጥራታቸዉ ነዉ። ሃገር ማለት ኣንድም ሁሉም ዜጎችዋ ኣንድ ወገን መሆን ነዉ።

ይህን ኣለማስተዋል በቀላሉ ማወቅ የሚቻለዉ የ16ኛዉ ክፍለ ዘመን የቦረና ጄኔራሎች እነማን እንደነበሩ በማወቅ ነዉ። ማንነቱን የረሳ ከእራሱ ጋር የሚጣላ ይሆናል።

ይህን በማወቅ ከዛ ግዜ ጀምሮ በሰላም ኣብረዉ የኖሩት ማህበረሰቦች ኣብረዉ በሰላም ወደ ልማት እና እድገት የሚገሰግሱ ይሆናሉ። ይህ ስህተት ነዉ?