Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Abere
Senior Member
Posts: 14874
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: PP በሻዕብያና በኤሜሬትስ ጉልበት የተቆጣጠራቸው የትግራይ ግዛቶች የማስረከብያ ጊዜው ኣልረፈደም? የሻዕብያ ከለላ expiry date ኣለው!

Post by Abere » 15 Jun 2024, 08:05

ወያኔ ኤርምያስ ለገሰ እና ለወያኔ ቤተሰቦቹ በዚህ የጎንደር ዘፈን ትንሽ ፈታ ይበሉ - including TPLF sarcasm :lol:

ሁመራ ናልኝ በጎንደር አርግና


https://www.youtube.com/watch?v=PA9kH01CzDU

sarcasm
Senior Member
Posts: 11385
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: PP በሻዕብያና በኤሜሬትስ ጉልበት የተቆጣጠራቸው የትግራይ ግዛቶች የማስረከብያ ጊዜው ኣልረፈደም? የሻዕብያ ከለላ expiry date ኣለው!

Post by sarcasm » 15 Jun 2024, 09:00

Abere wrote:
15 Jun 2024, 08:05
ወያኔ ኤርምያስ ለገሰ እና ለወያኔ ቤተሰቦቹ በዚህ የጎንደር ዘፈን ትንሽ ፈታ ይበሉ - including TPLF sarcasm :lol:


Brother Abere,

Thanks for the lovely song. Enjoy Almaz's another famous song. I am sure you will get up and dance two or three rounds :lol

https://www.youtube.com/watch?v=GnpmrWaxtrQ&t=1


Abere
Senior Member
Posts: 14874
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: PP በሻዕብያና በኤሜሬትስ ጉልበት የተቆጣጠራቸው የትግራይ ግዛቶች የማስረከብያ ጊዜው ኣልረፈደም? የሻዕብያ ከለላ expiry date ኣለው!

Post by Abere » 16 Jun 2024, 10:19

ወ/ሮ ማርያማዊት በእውነቱ ያቀረበችው ትንታኔ የተቻቸው ሰዎች ትክክለኛነት እንጅ እርሷ እንደምትለው ወይም እንደምታስበው አይደለም።

ወልቃይት ሁመራ እና ራያን በተመለከተ ማንኛውንም አማራ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቢጠየቅ ምንም አይነት አንቂ ሳይፈልግ እነ ዶ/ር ዳኛቸው ያሉትን ሀሳብ ነው የሚያንጸባርቀው። የወልቃይት፤ራያ እና ሁመራ ጉዳይ በአማራ ህዝብ ዘንድ የወል አቋም ነው።

እውነት መነጋገር ከተፈለገ የትግራይ ህዝብ ወልቃይት ራያ እና ሁመራን ሰርቃችሁ አምጡልኝ ብሎ ያዘዘው ወያኔ የለም። ወያኔ እራሱ የፈጠረው እና ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፈው በሽታ ነው። ከዚህ በሽታ ነው የትግራይ ህዝብ መላቀቅ ያለበት።

ማርያማዊት ታጭበረብራለች። እንደት?

1ኛ) የወያኔ ትልቁ ህልም ትግራይን መገንጠል ነው። ዐባይ ትግራይ ሪፓብሊክ መመስረት። ለዚህ ደግሞ በውሸትም ይሁን በጉልበት የአማራን መሬት ሰርቆ መሄድ። ወያኔ አንቀጽ 39 በደደቢት ህገ-መንግስቱ ለምን አስቀመጠች? ግልጽ ነው። ከዚያ ነበር መጀመር ያለባት። የትግራይ ህዝብ እኮ እራሱ ወያኔ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የሚለውን እንኳን ይዞ የማይወጣ ነው። በልቡ እና በህሌና ከኢትዮጵያ የተገነጠለ ነው። እኔ የትግራይ ህዝብ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዞ ተበደልኩ ቢል አዳምጥ ነበር። ስለዚህ አንቀጽ 39 የጻፈውን በመርሳት አማራን ለማታለል ሌሎች እውነት ስለተናገሩ አናዷታል።

2) የወልቃይት፤ራያ እና ሁመራ ጉዳይ ቅድመ ዐብይ አህመድ የነበረ እንጅ ልክ አሁን ብቻ እንደ ተጀመረ አድርጎ ማየትም ስህተት ነው።የእነዚህ አካባቢ ህዝብ ጥያቄ ታፍኖ የቆየ በመዋቅር የተዳፈነ የጭቁን ህዝቦች ድምጽ ነበር። የአብይ አህመድ ትልቁ ጥፋት የእዚህ አካባቢ አማራ ህዝብ በመስዋዕትነት ያስመለሰውን እርስቱን ከወራሪ ወያኔ ጋር መደራደሪያ አድርጎ በበደል ላይ በደለ መጨመሩ ነው። አሁን አብይ አህመድ ማማረር ያለበት የአማራ ህዝብ እንጅ በዚህ ጉዳይ የትግራይ ህዝብን መጠቀሚያ አድርጎ ስለትግራይ ህዝብ በወያኔኛ አፍ ማውራት አይደለም።

አንድ የሚደንቀኝ ነገር ደግሞ አንዳንድ ትግሬዎች እና ወያኔዎች አይደለንም ወያኔን እንቃወማለን ይላሉ። እንደት ነው የሚቃወሙት? ወያኔ የሚፈልገውን እና ወያኔ የሚያወራውን ጉዳይ እያወሩ ምን እንድባሉ ይፈልጋሉ። ለምሳሌ ማርያማዊት በዚህ ቪድዮ ላይ ሙልጭ ያለች አክራሪ ወያኔ ነች። ምናልባት ሳልሳይ ወያኔ የሚባለው ከወያኔ በላይ ወያኔ አባል ሳትሆን አትቀርም።

--- ዋናው ጉዳይ ግን የትግራይ ህዝብ ስለ ሁመራ፤ወልቃይት እና ራያ ያለውን ቅዠት ከጭንቅላቱ ማውጣት አለበት። ምንም አይነት መፍትሄ የለውም - ከመርሳት ውጭ። እንደ እኔ መፍትሄ የምለው አጠቃላይ የጎሳ ክልል ማፍረስ እና ሁሉም እኩል አንድት አገር ኢትዮጵያ አለችኝ ማለት ሲችል ነው። የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት መድሃኒት ክኒኑን ሲውጥ ያኔ ይሻለዋል። ራያ ወልቃይ ሁመራን ሪፈረንደም ( ሰው እና መሬት በስታትስቲክስ :lol: :lol: :lol: )፤በማጭበርበር ወዘተ አይሰራም። Any sane Tigre had better stop dreaming off these territories for a sustained peace.



sarcasm wrote:
16 Jun 2024, 06:39
Prosperity Party must end occupation of Tigray territories.


Post Reply