ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ” የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን
ቢቢሲ- የትግራይ ኃይሎች እና የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አዛዦች ትጥቅ መፍታት፣ ማሰናበት እና መልሶ ማቋቋምን በተመለከተ የናይሮቢ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሆኗቸዋል። እነዚህን መዘግየቶች ያስከተሉት ነገር ምንድን ናቸው?
አሁን የፌደራል መንግሥት ሁሉንም ባይሆንም አራት ዙር በራሱ [በጀት] ለማሰናበት ተነሳሽነት ኣሳይቷል። የትግራይ መንግሥት እና የትግራይ ሠራዊት አመራሮችም ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው። የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽኑ ቦርድም አቅጣጫ አስቀምጦ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ግብዓት ማሰባሰብ ችሏል።
በተጨማሪም መንግሥት የገቢ ማሰባሰብ ሥራዎችን እንዲያከናውን እና ሀብትን እንዲያንቀሳቅስ ከዚያም የአገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን ሠራዊቱ መቋቋሚያ ተሰጥቶት ወደ ማኅበረሰቡ እንዲመለስ ለማድረግ ሀሳብ ቀርቧል።
ቢቢሲ፡ ፕሮግራሙን ለመሸፈን ቃል የገቡት አገሮች እነማን ናቸው?
አቶ ተስፋዓለም፡ ቃል የገቡ በርካታ አገሮች አሉ ከነዚህም መካከል አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ጀርመን እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ቢቢሲ፡ ይህንን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ በአጠቃላይ ምን ያህል በጀት ያስፈልጋል?
አቶ ተስፋዓለም፡ የሚፈለገው ብዙ ነው። አስፈላጊው በጀት ተዘጋጅቷል። ነገር ግን ሲፀድቅ እና ይፋ ሲሆን ሌላ ግዜ እገልጻለሁ። የካናዳው ግን ራሳቸው ይፋ አድርገውታል። ሌሎችም ይኖራሉ። የሙከራ ፕሮጀክትም እየጀመርን ስለሆነ አንድ ነገር ሲፈቀድ እና ሲወሰን እንናገረዋለን።
This is another grand scam by TPLF and OPDO. They beg in the name of demobilization, but in reality they will use the funds to mobilize the TPLF militia to once again fight and die in the lands far away from home. No amount of foreign funding will save the OPDO regime. Tigray youth will only be paying unnecessary sacrifice to sustain the dying regime. No one can stop the Amhara Fano movement!!
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pypp0jp8wo
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40