የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕረዜዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በመግለጫቸው ፥ ” በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ላይ መሰረት ያደረገ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከፌደራል መንግስት ጋር የሁለት ቀን ውይይት በማድረግ የአፈፃፀም ስምምነት ላይ ተደርሷል ” ብለዋል።
” በውይይቱ የማጠቃለያ ስምምነት መሰረት የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም እንዲተገበርና እንዲፈፀም ስምምነት ተደርሷል ” ሲሉ ተናግረዋል።
https://mereja.com/amharic/v2/946600