በትግራይ ክልል Selam/ ቢሰፍንም ጽኑ ረሃብ ህፃናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው

ዋሽንግተን ዲሲ —
በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት አብቅቶ አሁን ሰላም ቢሰፍንም፣ ጦርነቱ ትቶት የሄደው ጠባሳ ከድርቅ እና የርዳታ አያያዝ ጉድለት ጋራ ተደማምሮ፣ በአንድ ወቅት ለምለም የነበረውን ሜዳ አሁን ምድረበዳ አድርጎታል። ፊታቸው በጭንቀት የተሞላ እናቶችም ልጆቻቸው በምግብ እጦት ሲዳከሙ እርዳታ በማጣት ይመለከታሉ። በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቅ ውስጥ የሚገኘው እና 13ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ፊናርዋ ከተማ፣ ረሃብ ከፀናባቸው አካባቢዎች አንዱ ሲሆን፣ በአካባቢው በሚኖሩ እናቶች እና ህፃናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።
https://amharic.voanews.com/a/7526402.html