Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40425
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አበረ ፤ ይህን ረፖርት በጥልቀት መርምረው!

Post by Horus » 25 Feb 2024, 12:59

እጅግ እጅግ ያስገርማል! ማን ከማን ጋር እንደ ቆመ!

Horus
Senior Member+
Posts: 40425
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አበረ ፤ ይህን ረፖርት በጥልቀት መርምረው!

Post by Horus » 25 Feb 2024, 13:44

አበረ፣
ይህ ፓኪስታናዊ የሚለው ምን መሰለህ፤ ግብጽ የኢትዮ ሱማሌላንድ ስምምነት የምትቃወመው የራሱን ወደብ ለኢሚራቲ ለመሸጥ ነው ይላል። ይህ ማለት ደሞ አቢይ ከሱማሌላንድ ጋር የሚያደርገው ስምምነት በመሰረቱ የኢሚራቲው ጉዳይ ነው ማለቱ ነው ። ባንድ ቃል ግብጽ ቢ ዛይድ የሱማሌላንድ ወደብ ትቶ የነሱን እንዲገዛ ስለሚፈልጉ ነው ሱማሌን የደገፉ የሚመስሉት ነው ያሚለው ። ሁሉም እንደ ሚያውቀው አቢይ ወደቡን ለማልማት ገንዘብ የለውም፣ ገንዘብ ያለው ኢሚሬቱ ጋ ነው ።

ሌላው ደም ቱርክና ግብጽም በሰፊው የተሳሰሩ ናቸው ። ቱርክ ሱማሌ ምትገባው ቢ ዛይድን ለማስወጣ ነው ። ስለዚህ ሱማሌ ውስጥ አረቦቹ ጥቅማቸው ተመሳሳይ አይደለም ። የነገሪ ጂኦ ኢኮንሚክስ ውስብስብ ነው

Abere
Senior Member
Posts: 14917
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አበረ ፤ ይህን ረፖርት በጥልቀት መርምረው!

Post by Abere » 25 Feb 2024, 15:04

ሆረስ፤

መቸም አባቶችን ነገሮችን በምሳሌ በማስረዳት ሰፊ ክስተትን በአጭሩ ይገልጹታል። የአረቦች ነገር "ባል እና ሚስቱ ሊተዋወቁ ምን ነው ሰርገኛ ልቡን ማውለቁ" ማለት ነው ለ HoAዎች ። ዐብይ አህመድ ገንዘብ እንደሌለው እሙን ነው። እርሱም ለፕሮፓጋንዳ ሲል ያለወቅቱ ያነሳው ጥያቄ መሆኑ ግልጽ ነው። ያለ ወቅቱ ቢመጣም ከተነሳ ዘንድ መቀጠል አለበት ምክንያቱም ነጥብ አገሪቱ ነጥብ ጥላ መሄድ ስለሌለባት ብቻ። በጣም የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን ዐረቦች ፈረንጆች የአፍሪካ ቀንድ የሚሉትን አካባቢ እንደ መሲና ላም መዳሪያ ቦታ ማድረጋቸው ነው። ይህ አካባቢ የደናቁርቶች መዳሪያ በመሆኑ አንዳች ፍሬ ሳይጸንስ አገር ምድሩ በፍራስራሽ ከተማ እና በተራቆቱ ሰው ዐልባ አውራ ጎዳናዎች ተሞልቷል። በዚህ ሁኔታ ገና ብዙ ንትርክ እና የፓለቲካ ድሪያ አረቦች ያደርጋሉ። አረቦች እጅግ የሚያማልላቸው የኢትዮጵያ ለምለም የእርሻ መሬት እና ንጹህ ውሃ ምንጭነት ነው -ለዚህ ደግሞ የተለያየ ዘደ እየተጠቀሙ ትርምሱን ይቀጥሉበታል።

Horus wrote:
25 Feb 2024, 13:44

Post Reply