Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 40425
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 23 Feb 2024, 05:23
ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ውስጥ ያዳዲ ማሪያምን ገዳም ታሪክ የሚተርክ ሰው አለ ። ታሪኩ ካሉት ብዙ ስህተቶች እጅግ ግዙፉ 'አዳዲ' ስለ ሚለው ቃል ነው። ተራኪው በአንድ በኩል ገዳሙ በ11ኛው ክፍለ ዘመን ተቆረቆረ ይላል። ገዳሙን የገደሙት አቡነ መንፈስ ቅዱስ በ1414 አረፉ ይላል። በሌላ በኩል የገዳሙ ስም ነጭ ነጭ ልብስ የለበሱ ሰዎች የሚል እዚያ የነበሩ ኦሮሞች ቃል ነው ይላል ። ፍጹም ነጫ ዉሸት ።
አዳዲ፣ አዳዳ፣ አዶት፣ አዶናይ እጅግ ጥንታዊ የሴም ቃል ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ በጉራጌኛ ቋንቋዎች በሰፊው ያለ ቃል ነው ።
አንድ፣
አዶት እናት ማለት ነው (ሰባት ቤት ጉራጌኛ)
ሁለት፡
አዳዳ ታላቅ እናት፣ አያት እናት ፣ እናትን በአክብሮት መጥሪያ ክብርት እናት ማለት ነው (ክስታኔ ጉራጌኛ)
ሶስት
ሌላው ቀርቶ በላቲን አዶናይ ማሪያም ፣ የእግዚአብሄር እናት (Mary, The Mother of God) ማለት ነው ።
ስለዚህ አዳዲ ማሪያም ታላቋ እናታችን፣ ማሪያም የእግዚአብሄር እናት ማለት ነው
ፈጠራና ዉሸት ቀስ በቀስ መጋለጡ ስለ ማይቀር የሌለን ታሪክ አንፍጠር !
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12910
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 23 Feb 2024, 05:41
አደዳ = አክስት፣
አዶዬ = የሴት ልጅ የቅርብ ጓደኛ (አብሮ ኣደግ)
አዴሱ = ማንጣት (ነጭ ማድረግ)፣
አዲ = ነጭ፣
አደኣ = የቦታ ስም
አዳሚ = የእንጨት ስም
አዱ = ፀሓይ
ጉራግኛ ከአፋን ኦሮሞ ጋር ፍክክሩን በጊዜ ብያቆም አይሻለዉም? ይህ የፕሪሜየር ሊግ ክለብ ነዉ በሉት።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 40425
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 23 Feb 2024, 11:33
[quote=DefendTheTruth
[/quote]
ዲዲቲ፡
ይህ ውይይት ተስማምቶኛል። እንድትገፋበት እፈልጋለሁ ። በጉዳዮ ላይ ለብዙ የቋንቋ ተማሪዎችና ሊቃውንት ግ ብ አ ት የሚሆን ነው።
አንድ፤
ኦሮሞ በስንት ዘመን ነው በሸዋ የተከሰተው? አዳዲ ማሪያም መቼ ነው የቆመኦሮሞችው? ኦሮሞ በ1550 ዓም እንኳ በጉራጌ ምድር አልደረሱም ። አዳዲ ማሪያም ቢያንስ ከመቶ እስከ ሶስት አመት አመት በፊት መላ ክስታኔን ለዘመናት አስተምረው እዚያ በክስታኔ ክቡር ምድር በምድረ ከብድ የተቀበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተመሰረተ ገዳም ነው ።
ይህም ማለት ጋላ ወይም ኦሮሞ የተባሉ ሕዝቦች መላ የጉራጌን ምድር ከግቤ እስከ አዋሽ፣ ካዋሽ እስከ ዝዋይ ያለውን ከመውረራቸ ከመቶ እስከ ሶስት መቶ አመት በፊት ማለት ነው።
ለዚህም ነው ግራኝ መሃመድ አዳዲ ማሪያምን በ1525 ዓም ያቃጠለው በግልጽ በታሪክ ተመዝግቦ ያለ ነገር። ግራኝ መሃመድ የመላ ጉራጌ ገዳማትን ሲያውድም ከዝዋይ፣ ባደቄ እስከ ጋፋቶች እንደ ገብጣን ድረስ አንድም ጋላ የሚባል ሕዝብ እንዳልተዋጋና እንዳላሰለመ በታሪክ የተመዘገበ ነው ።
በ1525 ጋሎች በጉራጌ ምድር አልደረሱም ። ስለዚህ የግዜ ታይምላይን ክርክርክን ይሽረዋል
ሁለት
ዛሬ አድአ ሆነ አዳዲ የሚኖሩት ኦሮሞ የተባሉት ሕዝብ ኦሮሞኛ ቋንቋ የተጫናቸው የጥንት ጉራጌዎች እነ ያኔ እነ ገላን ፣ እነ ላቄ ወዘተ ናቸው ። ዛሬ ቁንቋው ሆነ ካልቸራቸው፣ ስነልቡናቸው ከግንዳቸው የወረሱትን ያሳብቃል። ለምሳሌ ከላይ የጠቀስካቸው ቃላት እንመልከት፡
ቃላቶች እነፈለጋቸው አንድ ድምጽ ይዘው እንደ ፈለጋቸው በትርጉም የሚለዋወጡ ከሆነ በድንቁርና የተወሰዱ ተውሶዎች ናቸው ማለት ነው ።
ጉራጌ አዳዳ (እናት)፤ እንዶቶ (አክስት)፣ በሰባት ቤት አዶት = እናት ብሎ አጎት እያለ ይሄዳል ። እውነተኛ ቃል ስሩን ሳይለቅ ተቀራራቢ ነገሮችን ይጠራል። ሌላው ነገር ሰዎች በካልቸር ለውጥ ማንነታቸው ቢለወጥም የእናት አባት የመሳሰሉት ቃላት አይለወጡም ።
አዶዬ (ሴት ጓደኛሞች) ትርጉሙ ውዴ እነደ እናት ማቆላመጫ ማለት ነው። ሌላው ዬጎስቴ ይባባላሉ (ንግስቴ) እንዲሁ። እነዚህ ኦሮማይዘድ ቱባ ክስታኔዎች ናቸው ።
አዴሱ = ማንጣት (ነጭ ማድረግ) ነው ብለሃል። ይህ አዲስ ከሚለው ቃል ተውሶ ነው ።
አዲ = ነጭ፣ ነው ብለሃል ። አዴሱና አዴ ሁለቱም ከላይ አዲስ ከሚለው የተወሰዱ ናቸው
አዳሚ እንጨትና አዱ ጸሃይ አንድ ስረ ቃል የላቸውም ። ጸአዳ ንጹህ ነጭ ማለት ነው ። ግ ን ኦሮሞኛ ሳይሆን ግዕዝ ነው ። ግዕዝ ተናጋሪ ክስታኔዎች ናቸው ።
ይህ ለመጀመር ያክል ነው ።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 40425
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 23 Feb 2024, 16:29
ዲዲቲ
ዝምታህ ለምነው? መስማማት ወይስ መቃወም ። አዶዬ የሚለውን ልዩ የሆነ ክስታኔኛ ቃል ማወቅህ የሚነግረኝ አንተ አጠገቤህ ያለህ የግላን ፣ ያያ፣ ወይም የጨቦ ኦርሞ ነህ ፣ አያቶችህ ክስታኔዎች ናቸው ። አዶዬ ዛሬ ላይ የእብራይስጥ ቃል ነው ። ሲጀመር ግን የአረሜይክ አባት የሆነው የዩጋርቴና ኢብላይቴ እጅግ አሮጌ የሴም ቃል ነው ። ልጃገረዶቻችን ዬጎስቴ (ንግስቴ) እና አዶዬ (እሜቴ) እየተባባሉ የሚሞካሹበት ጥንታዊ ቃል ነው የያዝከው። ጊስት/ ጊስቴ ማለት በጉራጌኛ ንግስት/ንግስቴ ማለት ነው ። እኛ ወንዶቹም እጅግ የቅርብ ጓደኛችን መሪ ነው የምንባባለው። እጅግ አዛውንቱ አያታችን ወንዱ አጋ ይባላል (ጌታ) ማለት ነው ፣ ሴቷ አዳዳ እንላታለን። ልብ በል አጋ እና አዳ እንዴት አንድ እንደ ሆኑ ! ማሪያም እናት ነች!
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12910
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 23 Feb 2024, 16:53
ሆረስ፣
አንተ አሁን እኮ ኦሮሞን እያጣጠልክ ሳይሆን እያሞከሽክ ነዉ፣ ወደህ ሳይሆን በድርግትህ።
ኦሮሞ ወደ ክልላችን የመጠዉ ከመቶዎች አመታት በፊት ነዉ፣ እኛ በቦታዉ የነበርነዉ ለሺዎች አመታት ነዉ፣ የምትለዉ። እዚህ ላይ ልብ በል። የሆነ ችግር ብኖር ነዉ እንጂ ሰዎች ለሺዎች አመታት በኖሩበት ቄያቸዉ አይገብሩም፣ ነገር ብኖር ነዉ መጤዎቹ ነባሮቹን በልጠዉ መግዛት የቻሉት። ይህ ሳይንስ ነዉ።
ኦሮሞ አቃፊ ነዉ የምባለዉ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ አይደለም። ሰዉን በእኩልነት ማየት መቻል ትልቅ የሕዝብ ብልህነት ወይም አሴት ና እዉቀት ነዉ። እንደአንተዉ ሰዎች አግላዮች አይደሉም ማለት ነዉ።
ዛሬም የኦሮሞ አገዛዝ መጣ ና የአፍሪካ ቀንድን አንድ አድርገን በጋራ እንልማ ብሎ እየለመነ ይገኛል፣ የአንተዉ ዘመዶች ግን ለዘመናት እሽቅድድም ተያይዞ ቀጠናዉን ለችግር ዳራጉት፣ ኋላ ቀር አድርጎ አስቀሩት።
ሶማሊያላንዶች እናመሰግናለን እይሉን ነዉ፣ አልሰማህም? ታዲያ ምነዉ አንተም ለምዶብህ እናመሰግናለን ብትል? ምስጋና ለፈጣሪ ነዉ፣ አይደለም እንዴ?
በተረፈ ቃላቶቹን አትጨመድዳቸዉ፣ ራስህን ታስታዝባለህ እንጂ ምንም አታተርፍም። አዱ፣ አዴሱ፣ አዲ ምን ጊዜም ከኦሮምኛ መዝገበ ቃላት ማዉጣት አትችልም ና። ተመከር!
እኔ የስነ ቋንቋ ምሁር አይደለሁም፣ ነገር ግን ይህ የአንተ ሞከራ ከተፈጥሮም ጋር የተጋጨ ነገር ነዉ የሆነብኝ።
ኦሮሞን መጥላት ትችላለህ፣ ተፈጥሮን መቀየር ግን አትችልም፣ ምን ጊዜም!
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12910
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 23 Feb 2024, 17:04
What exactly do you mean, when you scribble something like this?
"አዴሱ = ማንጣት (ነጭ ማድረግ) ነው ብለሃል። ይህ አዲስ ከሚለው ቃል ተውሶ ነው ።
አዲ = ነጭ፣ ነው ብለሃል ። አዴሱና አዴ ሁለቱም ከላይ አዲስ ከሚለው የተወሰዱ ናቸው"
Do you mean there is no new black or in any other color?
It must be the funniest of all.
new = ሃራ፣
white = አዲ
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 40425
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 23 Feb 2024, 17:10
DefendTheTruth wrote: ↑23 Feb 2024, 16:53
ሆረስ፣
አንተ አሁን እኮ ኦሮሞን እያጣጠልክ ሳይሆን እያሞከሽክ ነዉ፣ ወደህ ሳይሆን በድርግትህ።
ኦሮሞ ወደ ክልላችን የመጠዉ ከመቶዎች አመታት በፊት ነዉ፣ እኛ በቦታዉ የነበርነዉ ለሺዎች አመታት ነዉ፣ የምትለዉ። እዚህ ላይ ልብ በል። የሆነ ችግር ብኖር ነዉ እንጂ ሰዎች ለሺዎች አመታት በኖሩበት ቄያቸዉ አይገብሩም፣ ነገር ብኖር ነዉ መጤዎቹ ነባሮቹን በልጠዉ መግዛት የቻሉት። ይህ ሳይንስ ነዉ።
ኦሮሞ አቃፊ ነዉ የምባለዉ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ አይደለም። ሰዉን በእኩልነት ማየት መቻል ትልቅ የሕዝብ ብልህነት ወይም አሴት ና እዉቀት ነዉ። እንደአንተዉ ሰዎች አግላዮች አይደሉም ማለት ነዉ።
ዛሬም የኦሮሞ አገዛዝ መጣ ና የአፍሪካ ቀንድን አንድ አድርገን በጋራ እንልማ ብሎ እየለመነ ይገኛል፣ የአንተዉ ዘመዶች ግን ለዘመናት እሽቅድድም ተያይዞ ቀጠናዉን ለችግር ዳራጉት፣ ኋላ ቀር አድርጎ አስቀሩት።
ሶማሊያላንዶች እናመሰግናለን እይሉን ነዉ፣ አልሰማህም? ታዲያ ምነዉ አንተም ለምዶብህ እናመሰግናለን ብትል? ምስጋና ለፈጣሪ ነዉ፣ አይደለም እንዴ?
በተረፈ ቃላቶቹን አትጨመድዳቸዉ፣ ራስህን ታስታዝባለህ እንጂ ምንም አታተርፍም። አዱ፣ አዴሱ፣ አዲ ምን ጊዜም ከኦሮምኛ መዝገበ ቃላት ማዉጣት አትችልም ና። ተመከር!
እኔ የስነ ቋንቋ ምሁር አይደለሁም፣ ነገር ግን ይህ የአንተ ሞከራ ከተፈጥሮም ጋር የተጋጨ ነገር ነዉ የሆነብኝ።
ኦሮሞን መጥላት ትችላለህ፣ ተፈጥሮን መቀየር ግን አትችልም፣ ምን ጊዜም!
እኔ ያንተን ቃላት አልጨመደድኩም ፣ በዉሸት አለ ጥቅስ የሚወሰዱት የራሴ ቃላት ላይ ነው ሙግቴ ።
በተረፈ አው መሬትክ ነጥቂያለሁ ምን ታመጣለህ ያልከውን መልስ ነው የወደድኩ ፣ እውነቱን ስለ ተናገርክ !
ወራሪ ነኝ፣ ዘራፊ ማለቱን ፈርተህ 'አቃፊ' የሚባለው የጋላ ትርክትን ወዲያ በለው !
በወራሪ፣ ዘራፊና አራጅ ካልቸር ያደጉት ናቸውኮ የዝቋላን መነኩሴዎች ወስደው ያረዱት !
አንተና ናጋ ቱማ ምትባሉ ግን እዚህ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ስትሞናመኑ የናንተ ዘር በመላ ኢትዮጵያ ስላሰፈነው የመከራ ዘመን ቃል አትተነፍሱም!
ታሪክ ግን ይህን ሁሉ እየመዘገበ ነው ! ልክ እንደዚህ ነው የኢትዮጵያን ስልጣኔና ካልቸር ለዘመናት ያቆረቆዛችሁት!