Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7321
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የኢትዮጵያ ኣዝማሪ ተማር፣ የኢትቶጵያ ኣዝማሪ ተማሪ

Post by Naga Tuma » 27 Jan 2024, 04:48

በኣዝማሪ እና ኣርቲስት ወይም የጥበብ ባለሙያ መካከል ልዩነት ኣለ? ኣዎ።

ኣዝማሪ ከሰዉ የሰማዉን ሰምቶ በቃጭል ድምጹ የምያሰማ ነዉ።

ኣርቲስት የራሱን ሀሳብ እና አስተሳሰብ በጥበብ መግለጽ የሚችል ነዉ።

በኣዝማሪ እና በኣርቲስት መካከል ያን ያህል ልዩነት ካለ ብዙዎች ኣዝማሪ ወይም ኣርቲስት መሆናቸዉን በቀላሉ መለየት ይችላሉ።

ኣርት ኣንዴ በጥልቅ ጥበብ ከተሰራ ዘላለማዊ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነዉ ተማር፣ ተማሪ ያልኩኝ።

ሃገር ቤት ናት፣
ሕዝቧ ቤተሰብ ነዉ፣

ይህ ቀላል አባባል ነዉ። ቢሆንም ለሌላ ጥልቅ አስተሳሰብ ያንደረድራል።

ቤተሰብ ወገን ነዉ እንጂ እርስ በርሱ ወገን እና ባዕዳ ኣይሆንም።

ብይ አከ መናት።
ሰብን እሳ አከ ማቲት።

ማቲን ወገነ መሌ ኦርማ ፊ ወገነ ምት።

ከነቱ ነጋ ቡሳ፣
ከነቱ ነጋ ፉላሰ።

ከነቱ መሪ ባሰ፣
ከነቱ መሪአቺሰ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17691
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የኢትዮጵያ ኣዝማሪ ተማር፣ የኢትቶጵያ ኣዝማሪ ተማሪ

Post by Selam/ » 27 Jan 2024, 05:01

ይኸን የወል ስም ‘አርቲስት’ እስኪ ወደ አማሪኛ ተርጉመው።

ደግሞ ማነው አዝማሪ ከሰው ሰምቶ ይደግማል ብሎ የነገረህ? የከተማ ጠጅ ቤት አውደልዳይ አዝማሪ ብቻ አይተህ ይሆናል እንቺ፣ አዝማሪ በታሪክ ፈጣሪና ቅኔ አዋቂ ነው፣ ዜማ ፈልሳፊ ነው፣ ክራርና ማሲንቆ ተጫዋች ነው። ሲፈልግ ይመርቅሃል፣ ሲፈልግ እንዳይገባህ አድርጎ ይሰድብሃል፣ ሰውን ያስጨፍራል፣ ያስለቅሳል፣ ለጦር ይቀሰቅሳል፣ ያዝናናል ወዘተ!







Naga Tuma wrote:
27 Jan 2024, 04:48
በኣዝማሪ እና ኣርቲስት ወይም የጥበብ ባለሙያ መካከል ልዩነት ኣለ? ኣዎ።

ኣዝማሪ ከሰዉ የሰማዉን ሰምቶ በቃጭል ድምጹ የምያሰማ ነዉ።

ኣርቲስት የራሱን ሀሳብ እና አስተሳሰብ በጥበብ መግለጽ የሚችል ነዉ።

በኣዝማሪ እና በኣርቲስት መካከል ያን ያህል ልዩነት ካለ ብዙዎች ኣዝማሪ ወይም ኣርቲስት መሆናቸዉን በቀላሉ መለየት ይችላሉ።

ኣርት ኣንዴ በጥልቅ ጥበብ ከተሰራ ዘላለማዊ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነዉ ተማር፣ ተማሪ ያልኩኝ።

ሃገር ቤት ናት፣
ሕዝቧ ቤተሰብ ነዉ፣

ይህ ቀላል አባባል ነዉ። ቢሆንም ለሌላ ጥልቅ አስተሳሰብ ያንደረድራል።

ቤተሰብ ወገን ነዉ እንጂ እርስ በርሱ ወገን እና ባዕዳ ኣይሆንም።

ብይ አከ መናት።
ሰብን እሳ አከ ማቲት።

ማቲን ወገነ መሌ ኦርማ ፊ ወገነ ምት።

ከነቱ ነጋ ቡሳ፣
ከነቱ ነጋ ፉላሰ።

ከነቱ መሪ ባሰ፣
ከነቱ መሪአቺሰ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7321
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የኢትዮጵያ ኣዝማሪ ተማር፣ የኢትቶጵያ ኣዝማሪ ተማሪ

Post by Naga Tuma » 28 Jan 2024, 04:08

ማለት የፈለኩኝ ገብቶህ ከሆነ ኣላዉቅም። ምናልባት ቸኩለህ መልስ ሰጥትህ ይሆናል። ሀሳቤ ላይ ለመጨመር መጥቼ ነዉ መልስህን ያነበብኩኝ።

ስለዚህ ተጨማሪዉንም ሀሳቤን እስቲ ኣንብብ።

በኣጭሩ ማለት የፈለኩኝ በራስ ኣዕምሮ ማሰብ እና ከሌላ ሰዉ ኣዕምሮ የሰሙትን ማስተጋባት መካከል ልዩነት ኣለ ነዉ።

በራስ የማሰብን እና ከሌላ የሰሙትን ማስተጋባትን ልዩነት ግልጽ የምያደርጉ ቃላትን ብታሰጠኝ ካሳመኑኝ እጠቀማቸዋለሁ።

በተጨማሪም የወገን እና ባዕድ ልዩነትን እና የወገነ እና ኦርመ ልዩነትን በደንብ ታዉቃለህ? የምትፈልገዉን ኣታዉቅም የምትባል ካልሆንክ። ወገን የምትለዉ ኦርመ ካላለህ።
Selam/ wrote:
27 Jan 2024, 05:01
ይኸን የወል ስም ‘አርቲስት’ እስኪ ወደ አማሪኛ ተርጉመው።

ደግሞ ማነው አዝማሪ ከሰው ሰምቶ ይደግማል ብሎ የነገረህ? የከተማ ጠጅ ቤት አውደልዳይ አዝማሪ ብቻ አይተህ ይሆናል እንቺ፣ አዝማሪ በታሪክ ፈጣሪና ቅኔ አዋቂ ነው፣ ዜማ ፈልሳፊ ነው፣ ክራርና ማሲንቆ ተጫዋች ነው። ሲፈልግ ይመርቅሃል፣ ሲፈልግ እንዳይገባህ አድርጎ ይሰድብሃል፣ ሰውን ያስጨፍራል፣ ያስለቅሳል፣ ለጦር ይቀሰቅሳል፣ ያዝናናል ወዘተ!







Naga Tuma wrote:
27 Jan 2024, 04:48
በኣዝማሪ እና ኣርቲስት ወይም የጥበብ ባለሙያ መካከል ልዩነት ኣለ? ኣዎ።

ኣዝማሪ ከሰዉ የሰማዉን ሰምቶ በቃጭል ድምጹ የምያሰማ ነዉ።

ኣርቲስት የራሱን ሀሳብ እና አስተሳሰብ በጥበብ መግለጽ የሚችል ነዉ።

በኣዝማሪ እና በኣርቲስት መካከል ያን ያህል ልዩነት ካለ ብዙዎች ኣዝማሪ ወይም ኣርቲስት መሆናቸዉን በቀላሉ መለየት ይችላሉ።

ኣርት ኣንዴ በጥልቅ ጥበብ ከተሰራ ዘላለማዊ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነዉ ተማር፣ ተማሪ ያልኩኝ።

ሃገር ቤት ናት፣
ሕዝቧ ቤተሰብ ነዉ፣

ይህ ቀላል አባባል ነዉ። ቢሆንም ለሌላ ጥልቅ አስተሳሰብ ያንደረድራል።

ቤተሰብ ወገን ነዉ እንጂ እርስ በርሱ ወገን እና ባዕዳ ኣይሆንም።

ብይ አከ መናት።
ሰብን እሳ አከ ማቲት።

ማቲን ወገነ መሌ ኦርማ ፊ ወገነ ምት።

ከነቱ ነጋ ቡሳ፣
ከነቱ ነጋ ፉላሰ።

ከነቱ መሪ ባሰ፣
ከነቱ መሪአቺሰ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7321
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የኢትዮጵያ ኣዝማሪ ተማር፣ የኢትቶጵያ ኣዝማሪ ተማሪ

Post by Naga Tuma » 28 Jan 2024, 04:18

ኢትዮጵያ እያለሁ ዘሪሁን ወዳጆ ኣንድ የዘፈን ካሴት ኣዘጋጀ።

አንዱ ዘፈኑ ዉስጥ ለፈ ሴንቱ ነን ሁረ፣ መከ ያበቱ ነን ሙረ ብሎ ዛተ።

ምድር ዉስጥ ብትገባ እበሰዋለሁ፣ ዘፍ ላይ ብትወጣ እቆርጠዋለሁ ብሎ እንደመዛት ነዉ።

ዘፈኑ ለብቻዉ ጥበብ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። የምያነሳሳ ግጥም ነዉ።

ቀጥሎ ያለዉ ወይም እዛዉ ካሴት ዉስጥ ያለ ዘፈኑ ያ ረቢ ኑ ብልሶምስ ይላል። ረቢ ሆይ ነፃ ኣዉጣን እንደማለት ነዉ። የምያጸልይ መልዕክት ነዉ።

የሁለቱን ዘፈኖች ኣለመጣጣም ያስተዋለ ኣንድ ሰዉ ሳቀበት። በወቅቱ ታዝቤ የነበረዉ የምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ መነቃቀፍ ነዉ እንዳልል እኔም ሳስበዉ የሁለቱ ዘፈኖች ኣለመጣጣም ገርሞኝ ዝም ኣልኩኝ።

ሌላ ቢቀር ኣድዋ ኢትዮጵያዊያኖችን ኣንድ ወገን ኣድርጎዋቸዋል። ኣይዴለም?

በክፉ ግዜ ክፋት ስር የወደቁት ኤርትራዊያን የኢትዮጵያዊያን ታሪካዊ ወገን ናቸዉ።

በዚህ የማይስማማ ካለ የድሮ ቀኝ ገዢዎች ጣልያን እና እንግሊዝ አጨብጫቢዎች እና ኣጫፋሪዎች ናቸዉ።

ቀነኒሳ በቀለ እና ሀይሌ ገብረስላሴ የኣንድ ሃገር ወገን ብቻ ሳይሆኑ የእስፖርት ሜዳ ዉሎ ወገንም ሆኖ ኣሳይተዉ ጥበበኛዉ ቴዎድሮስ ካሳሁን በፍጥነት ቀንጭቦ የብዙዎችን ዐይኖች ኣረጥቧል። ያ የጥበብ ስራዉ መቼም ኣያልፍበትም።

ታድያ በየትኛዉም ቋንቋ ቢሆን ቀነኒሳ በቀለ እና ሀይሌ ገብረስላሴ ወገን ወይም ወገነ ማለት እንጂ ኣንዱ ለሌላዉ ባዕድ ወይም ኦርመ ማለት የወገን እና ባዕድ ወይም ወገነ እና ኦርመ ትርጉሞችን ኣለማስተዋል ወይም ኣለማወቅ ኣይዴለም?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7321
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የኢትዮጵያ ኣዝማሪ ተማር፣ የኢትቶጵያ ኣዝማሪ ተማሪ

Post by Naga Tuma » 01 Feb 2024, 16:39

እኔ የሙዚቃ ትምህርትም ሆነ ዕዉቀት ዬለኝም።

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የታወቀ የተባለ የሙዚቃ ኣስተማሪ ኣንድ ሰሚስተር ስለሙዚቃ ስያስተምር ለሕሳብ ተማሪ የሙዚቃ ቋንቋ ለምን ያስፈልጋል ብዬ በጥልቅ ኣልተከታተልኩትም። ዶ ሬ ሚ ፋ ሶል ላ ሲዶ ሲል እንደ ቀልድ ነበር የምናስታውሰዉ። ሕሳብ ሲጫን ሙዚቃ ያዝናናል ብሎ ያኔ ማን መከረኝ?

አስተማሪዉ በሙያዉ ከኣጼ ሀይለስላሴ ጋር ይጓዝ ነበር የሚል ወሬ ሰምቼ ነበር። እዉነት ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም።

ጎልማሳ ሆኜ ሙዚቃ የራሱ የሆነ ቋንቋ ያለዉ መሆኑ የበለጠ ገብቶኝ ማህበረሰብ ዉስጥ ልጆች ስለ ዶ ሬ ሚ ፋ ሶል ላ ሲዶ ከልጅነት ጀምሮ እንዲያዉቁ ሆነ ብዬ መጽሃፉን ፈልጌ ገዛሁ።

ብዙም ሳልቆይ መንፈሳዊ መዝሙር እንጂ አለማዊ ሙዚቃ ኣያስፈልግም የሚል ሰበካ እንደነበረ ገባኝ።

ኣንድ ግዜ ከኢትዮጵያ መጥታ የአፋን ኦሮሞ እስካስታዋን ኣይቼ ያደነኳት ወጣት መንፈሳዊ እንጂ ተብላ ተወች ሲባል ሰምቼ ኣዘንኩኝ። ከሰባኪዎች ተይ ማለት በላይ የቤተሰቧ ያንን የልጅነት ችሎታ ኣይቶ ተይዉን እሺ ማለታቸዉ ገርሞኝ ዝም ኣልኩኝ።

የኣማርኛ እስክስታ ትከሾችን ይወዘውዛል። የአፋን ኦሮሞ እስክስታ ያልኩኝ አንገትን የሚወዘውዘዉን ነዉ።

መንፈሳዊ ተብሎም አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ፕሮቴስታኖችን ከኣማርኛ ተናጋሪ ፕሮቴስታኖች ለመለየት ትልቅ ትግል እንደነበረም ሰምቼ ነበር።

ሰንብቶም በወጣትነቴ በሙዚቃዉ በጣም የታወቀዉ አብተዉ ከበደ መንፈሳዊን እንጂ ሙዚቃን ትቻለሁ ብሎ አደባባይ ወጣ።

ሌላ በአካል የማላዉቀዉ ሰዉ ሕዝቡ በዛ ዉስጥ ማለፍ ኣለበት የሚል ጽሑፉን ኣንብቤ ደንግጬ ያ ሕዝብን ወደ ጨለማ እየነዱ በጨለማ ዉስጥ ማለፍ ኣለበት እንደማለት ነዉ ብዬ መከርኩት። የኣዉሮፓን የጨለማ ዘመን ኣስታዉሼዉ። እሱ መታለሉ ብቻ ሳይሆን ያታለለዉ ሰዉ መኖሩን ገምቼ።

የእኔ የኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎ መነሳት እነዚህን መሠረታዊ ስህተቶችን ከማስተዋል ጭምር ነዉ። ከሕዝቡ ባህል መራቅ እና ማራቅ ሳይሆን ወደ ሕዝቡ ባህል መቅረብ እና ማቅረብ ያስፈልጋል ማለት ነዉ። በኣጭሩ።

ለዚህም ታግያለሁ ብል ስህተት ኣይመስለኝም።

ትግሉ እና ትግሎቹ ከተለያዩ ኣቅጣጫዎች ቢመጡም የሕዝቡን ባህል የማንሳት ዉጤት እየታየ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ብዙ ባህላዊ ሙዚቃዎች ባለፉት በርካታ ዓመታት መዉጣታቸዉ ኣመልካች ዉጤት ነዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም።

ኣሁን ያለኝ ጥያቄ ስለ ባህላዊ ሙዚቃ ብዛት ሳይሆን ጥራት ነዉ። በተለይ በአፋን ኦሮሞ ከሚወጡት። ምናልባት ኣማርኛዉ በአቀራረቡ የተሻለ ልምድ ያለዉ ነዉ።

ትግርኛን ኣልችልም። ቢሆንም ዝም ብዬ ሳዳምጠዉ ሰከን ያለ ይመስለኛል። በአፋን ኦሮሞ የሚወጡትን ማዳመጥ እፈልጋለሁ። እንደ ኣንድ ኣዳማጭ በርካታዎቹን ወጥ ናቸዉ ማለት ያስቸግረኛል።

ወጥ የሆኑ የአሊ ብራ ዘፈኖች ኣሉ። ወጥ የሆኑ የአብተዉ ከበደ ዘፈኖች ኣሉ። ኣብተዉ በዛዉ ቢቀጥል የት በደረሰ እላለሁ።

ኣንድ የ አቡሽ ዘለቀ የቦረና ባህል ሙዚቃ የላቀ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ስለ ቦረና ጥልቅ ባህል ማስተርፒስ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ስለቦረና ጥልቅ ባህል የምያዉቁት የተለያየ ሁኔታ ዉስጥ የተለያየ ቃላትን መርጦ መናገርን ያስተምራል ይላሉ።

እንደሁኔታዉ ቃላትን መርጦ መናገር በላይ ፊደልን መርጦ መጻፍ በቀላሉ የተገኙ የሕዝብ እሴቶች ኣይመስሉኝም። ለምሳሌ ሠ እና ሰን ለይቶ መጠቀም መቻል በቀላሉ የተፈጠረ ኣይመስለኝም። በዚህ ግዜ ሳይሆን ጥንት ግዜ።

ኣንድ ግዜ ሰዎች ስያወሩ የሰማሁኝ ማይክል ጃካሰን ቢት እት የሚለዉን ታዋቂ ዘፈኑን እንዲዘፍን ቀርቦለት የነበረዉ ኪል እት የሚል ነበር ኣሉ።

እሱ ነዉ እንዲዘፍን የቀረበለትን ኪል እት ወደ ቢት እት ቀይሩ ብሎ ዘፍኖ የታወቀበት። ጥበብ ነዉ ያደረገዉ።

የእኔ ሀሳብ በእንደዚህ አይነት ጥበብ ሙዚቃ ዉስጥ የሚገቡ ቃላት የምያዝነኑ እንጂ የማያስከፉ እንዳይሆኑ ማድረግ ይክብዳል ወይ ነዉ።

ይህን ሀሳብ ሳነሳ ወጥ የሆኑ በርካታ ኣልተሰሙም ለማለት ኣይዴለም።

ወጥ ያልሆኑት ጥልቅ የሆነ ባህልን የምያደፈርሱ ኣይሁኑ ለማለት ነዉ። ኣንዳንዴ ከዓመታት በፊት የሰማሁትን ክርክር ያስታዉሰኛል። ኢትዮጵያ እያለሁ ኣንድ ግዜ የሕዝብ ትግል ዉስጥ ካልደፈረሰ ኣይጠራም የሚል አስተሳስብ ሰምቼ ኣያስፈልግም ብያለሁ።

ሌላ ግዜ በኢትዮጵያ ጎሳዎች ፉክክር ዉስጥ ኣንዱ ዜይ ዱ ዘ ሮንግ ቲንግስ፣ ዊ ኣር ኖት ዱይንግ እት ላይክ ዜም ሲል ሰምቼ ወድያዉ ዊ ዶንት ኒድ ቱ ዱ ዘ ሮንግ ቲንግስ፣ ዊ ጀስት ኒድ ቱ ዱ ዘ ራይት ቲንግስ ብዬ ስመልስ ዝም ኣለ።

ለዓመታት የተለያየ አስተሳሰቦችን ሰምቼ ኣንዳንዶቹ እኔ ከልጅነት ጀምሮ ያስተዋልኩኝ መሠረታዊ የኢትዮጵያ ባህል ዉጪ የሚመስሉኝን ሰምቻለሁ።

ወይ የእኔ ማስተዋል ስህተት ነዉ። ወይም ሌላ ምንጭ ኣለዉ።

ከሳምንታት በፊት ኣንድ ሙዚቃ የተባለን ማዳመጥ ጀምሬ ግማሹን ሳላዳምጥ በደመነፍስ ገተተ ብዬ ድርግም ያደረኩበት ከዚህ ዉጪ ሊሆን የሚችል ኣይመስለኝም።

Post Reply