ግጥም ጥልቅ ሊሆን ይችላል፣ እንደገጣሚዉ።
ግጥምን እንደሜካንካል መገጣጠም ከባድ ነዉ። ብዙዎችን ያስቸግራል።
ፖኤትሪ ዉብ ነዉ፣ በጥልቁ ከተጻፈ።
የኣማርኛ ሙዚቃ ግጥምን ያቀነቅናል።
የእንግሊዘኛ ሙዚቃ እንደፖኤትሪ ነዉ፣ የገቡኝ።
ወጣት ሆኜ የንዋይ ደበበ ዘፈኖች ይወደዱ እና ቶሎ ያልፍባቸዋል ሲባል ሰምቼ ነበር። መጽሓፍ የምያነብ ይመስላል ተብሎ። ስለግጥሙ ጥልቀት ይሆን?
ስለዚህ ግጥምን እና ፖኤትሪን እንዴት ማጣጣም ይቻላል?
ከጸሃይ ባታች፣ ከምድር በላይ
ስንቱን ዉሽቅ፣ ስንቱን ዉልቅ?
ሰማይን ሰተሽ፣ ምድርን ሰተሽ
የት ኣላ ጎረቤት፧ ግቢ ወደ ድሮሽ ቤት
ተገዳላይ ቢል ቆረጣ
ልጁ ይላል ደፈጣ
ኣለ ወይ ታሪካቸዉ ወይ ጉዳቸዉ
ለዓመታት ኣይቶ የታዘባቸዉ
የትኛዉ ነው ግጥም?
የትኛዉ ነዉ ፖኤትሪ?
ካልገጠመ እንደ ሜካንካል
ዳር ዳር ለምን፣ ማንባብ እንደማይቻል
ዳር ዳር ለምን፣ ማንበብ እንዳይቻል
የትኛዉ ነዉ ፖኤትሪ?
የትኛው ነዉ ግጥም?
ፖኤትሪ ከግጥም ሲጋጠም
የትኛዉ ቢጠብቅ ነዉ?
የትኛዉ ቢላላ
ሁለቱንም የማንበብ መላ?
Re: ግጥም እና ፖኤትሪ
ናጋ ቱማ፣
ጥያቄህ የተሳሳተ ነው ። ግጥምና ፖይትሪ ሁለቱም አንድ ስረ ቃል ነው ያላቸው፤ አንዱ ግዕዝ ነው ሌላው ግሪክ ነው ። ግሪክኛው የጥንት ግብጽ ቃል ሲሆን ሆነ ፣ተሰራ ማለት ነው ። የግሪኩ ፖዬሲስ ኮምፖዝ ማድረግ፣ ማጋጠም ፣ መስራት ማለት ሲሆን በግዕዝም ባማርኛው ገጠመ ፣ ኮምፖዝ አደረገ፣ አጋጠመ ፣ አስተካከለ ማለት ነው ። ግጥ/ቅጥ እኩል ትክክል ማለት ነው ።
ስለዚህ ግጥምና ፖይትሪ የተለያዩ ማስመሰል የቃሎቹ ትርጉም አለማወቅ ነው ።
ግጥም የተለያዩ ቤቶች (ዣንራ) አሉት ። ቤት የማይመታ የግጥም ቤት የሆያ ሆዬ ቤት ወይም የግጥም አይነት ይባላል ። በቅኔ ዘረፋ እጅግ የታወቀ የግጥም አይነት ነው ። ለምሳሌ፣
አፋፍ ላፋስ ስሄድ አገኘሁ ሚዳቋ
ጅራቷን ብይዛት አይኗ ፍጥጥ አለ ።
ይህ የሆያ ሆዬ ቤት ግጥም ነው!
ከዚያ በተረፈ ባብዛኛው የግጥም አይነት የሚወሰነው በስንኝ ቁጥር ልክ ነው ። አንድ ስንኝ አምስት ቃላት፣ ሌላው ስንኝ ስምንት ቃላት ሊኖሩት አይገባም። ስለዚህ ግጥም ማለት ሃ በሃ ማሳካት ብቻ አይደለም ፤ ስንኝ በስንኝ ማጋጠም ነው ።
ዘፈን ግጥም አይደለም !
ግን የዘፈን ግጥም (ሉራ/ሊሪክ) ለመዘመር የሚቻል ግጥም ማለት ነው ። ሊራ ማለት በገና ወይም በገና መሰል የክር መሳሪያ ነው ። ሊሪክ ለበገና ወይም ለሊራ የተጻፈ ግጥም ማለት ነው ። ሙዚቃም ግጥምም የተሰሩት በድምጻና በቃል ነው ። የሙዚቃ ግጥም ይዘመራል፤ የግጥም የፖይትሪ ግጥም ይነበባል ።
ስለዚህ
ንዋይ ደበበ
እንደ ገና ወጥቶ
ግጥም አነበበ
የሚለው ክስ ትክክል ነው ። ሙዚቀኛ ግጥምን ይዘምረዋል እንጂ አያብበውም!
በዚህና በመሳሰሉ ምክኛት ያንተም ጥያቄ ስህተት ነው ! ስለ ቅኔ፣ ስለ ግጥም ፍቅር ካለህ ማጥናት ስትችል ማለት ነው።