Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7334
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያን የበለጠ ማወቅ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ነዉ

Post by Naga Tuma » 21 Dec 2023, 04:12

በቅርቡ ኣዕምሮ ዉሽትን ሲጀምር እየተሳቀቀ ነዉ የሚል አስተሳሰብ እዚህ ፎረም ላይ ኣንብቤ ጥልቅነቱ ለብቻዬ ደነቀኝ።

ወድያዉም ለብቻዬ ሁሉም ባህል እንደዚህ ጥልቅ ኣይዴለም ኣልኩኝ። ይህን የበለጠ ማስተዋል ከኢትዮጵያ ባህል ወጥቶ ማየት ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ይህ ልምድ ለማካፈል እንጂ ሰዉ ለዚህ ብሎ ከሃገር ይዉጣ ለማለት ኣይዴለም።

የኢትዮጵያን ባህል በጥልቀት ያስተዋለ የሁሉም የአለም የሰዉ ጎሳዎች ባህል ተመሳሳይ ሊመስለዉ ይችላል። በተለይ ለዕዉነት ያላቸዉ ባህላዊ አስተሳሰብ።

በተለያየ ምክንያት የሰዉ ልጅ ሌላዉን ለጥቃቅን ነገሮች የማታለል ባህርይ ኣለዉ። ለምሳሌ የኑሮ ዉድነት ኢትዮጵያ ዉስጥ የከበደዉ ዉጪ ሃገር ዘመድ ያለዉ እየተሽኮረመመ ከፍ ያለ እርዳታ ለማግኘት ይህ ያ እያለ ዘመዱን ይጠይቃል። ወይም ኑሮ እየከበደዉ መጠየቅ ከብዶት ችግር ዉስጥ ሆኖ ኣታስብ ይላል።

እንደዚህ አይነቱ ዕዉነት ኣለመናገር እና ሆነ ብሎ ዉሸት መናገር የተለያዩ ናቸዉ።

ከዓመታት በፊት ሌላ ሰዉ በአፋን ኦሮሞ የጻፈዉ ዉስጥ ሌላ በጣም ጥልቅ የሆነ አጭር አገላልጽ ኣንብቤ ለብቻዬ ይህ ቋንቋ በጣም ጥንታዊ መሆን ኣለበት ኣልኩኝ።

ከኢትዮጵያ ወጥቶ የተለያዩ ሃገሮችን በስራ ምክንያት ሄዶ ያየ ሰዉ ኣንድ ግዜ ዋቅን ኢትዮጵያት ዴብሴ አነ ሃ አጄሱን ጄዼ ብሎኝ ነበር። እግዝኣብሔር ወደ ኢትዮጵያ መልሶ ይግደለኝ ኣልኩኝ እንደማለውት ነዉ።

የሚገርመዉ ይህ ሰዉ እዚሁ አሜርካ ዉስጥ ተማሪ ሆኖ ኢትቶጵያ ኋላ ቀር ስለሆነች ተስፋ እንደሌላት ሲናገር ሰምቼ ኣያልፍላትም ማለት ኣይዴለም ብዬ መክሬዉ የነበረ ነዉ።

ቋንቋ የባህልን ጥልቀት የሚገልጽ ከሆነ የጥልቀቱ ምንጭ ምን ነበረ? የመነጨዉ ከመቼ ጀምሮ ነበረ?

የእኔ ግምት በጣም ጥንት ግዜ የጀመረ ነዉ። ምስክሮቹ ኣዳኙ እና ነብዩ ሳይወለዱ በፊት።

ከኢትዮጵያ ዉጪ ኖሬ ያስተዋልኩኝ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባህል የምያሳቅቀዉን የማይሳቀቅ የሰዉ ልጅ ባህርይ መኖሩን ነዉ።

ያስተዋልኩኝ ልክ ከሆነ ስለኣንድ አስተሳሰብ የመሳቀቅ ችሎታ ያላቸዉ እና የሌላቸዉ ኣዕምሮዊች መኖራቸዉ ነዉ።

በእኔ አስተያየት የሰዉ ልጅ ስልጣኔ መለያዉ የዚህ ችሎታ መኖር እና ኣለመኖር ነዉ።

ችሎታዉን ያላዳበረዉን ፕሪሞርድርያል ኮንሲዩመር ሶሳይቲ እላዋለሁ።

ይህ ማህበረሰብ በልጅነቴ እረኛ ሆኜ ካስተዋልኩኝ የክብት ባህርይ ጋር ይመሳሰላል። ለሽ የሆነ በቂ የሆነ ሳር እየጋጠ ያለ በሬ ሌላ በሬ ወደ ሌላ ለሽ ሳር ሲሄድ ካየ ቀንዱን ቀና ኣድርጎ ሮጦ በቀንዱ ገፍቶ መጋጥ ይቀጥላል። ለሁለቱም በቂ ለሽ ሳር እያለ ኣንዱ በሬ በቃል ሳይሆን በቀንዱ ይጋፋል።

የሰለጠነ ኣዕምሮ በቃል ይገስጻል። ግፍ እያለ። ጩቡ እያለ። ሰፉ እያለ። ነዉር እያለ።

እነዚህን ቃላት የባህል መገለጫ ሆነዉ መጠቀማችንን እንጂ እነማን እንደጀመሯቸዉ እና መቼ እንደተጀመሩ የምናዉቅ ኣይመስለኝም። እኔ ኣላዉቅም።

የእኔ አስተሳሰብ የሰዉ ልጅ ትልቅ ኣዕምሮ ዉስጥ ህሊና ትንሽ ስፍራ ያላት ይመስለኛል።

ይህቺ ትንሽ ስፍራ የለማላቸዉ ሰዎች ኣሉ ብዬ ኣስባለሁ። ይህቺ ትንሽ ስፍራ ገና ጠፍ የሆነባቸዉ ሳዎችም ኣሉ ብዬ ኣስባለሁ።

ይህቺ ትንሽ ስፍራ ገና ጠፍ የሆነችባቸዉ እነዚህን ቃላት ማፍለቅ ይቅር እና ቃሉ ራሱ በቋንቋቸዉ ዉስጥ እስክዚህ ዘመን ድረስ ዬለም። ኣለ የምትሉ ካላችሁ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ጩቡ ወይም ግፍ ወይም ካርማ ምን ይባላል? ታቡ እንዳትሉኝ።

ይህቺን ትንሽ ስፍራ ጥንት ግዜ ያለማዉ ምን ነበር?

ጦርነት ይሆን? ጠፉ ስፍራዎች ላይ ጦሮች ኣርፈዉ ይሆን? ከዛ በኋላ ስፍራዉ ለምቶ የሰዉ ልጅ ሁሉ ኣብሮ የሚወለድ ይመስለን ይሆን? ያ ቢሆን በኣንድ ነገር ላይ ሁሉም እኩል የመሳቀቅ ችሎታ በኖራቸዉ። ሁሉም ጎሳዎች እኩል ችሎታዎች እንደሌላቸዉ ግልጽ ሲሆን ኣይደንቀንም።

በዛ ዉስጥ ያለፈ ሕዝብ ነዉ ነጋ፣ ሰላም፣ ሻሎም ማለትን ከጥንት ግዜ ጀምሮ ባህሉ ያደረገዉ? ያንን ባህሉ ያላደረጋ ሕዝብ ነዉ በዚህ ዘመን አርምስቲስ የሚለዉ? እስከዚህ ዘመን ድረስ ፒስ ማለትን ጥልቅ ባህሉ ማድረግ ያቃተዉ?

በዚህ ዘመን ስለዕዉነት ደንቀዉኝ ያለፍኩኝ ሁለት ምሳሌዎች ኣሉ።

ኣንዱ እዚህ ኣሜሪካ ኖሮ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰዉ ዳዊት ዮሓንስ ኣንድ ግዜ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የተናገረዉ ነዉ። ካልዘነጋሁ የተጻፈዉ ሁሉ እዉነት ነዉ ማለት ኣይዴለም ሲል ሰማሁኝ። ያንን አባባል ሳልሳማ በፊት የተጻፈ ዕዉነት ነዉ ብዬ ኣስብ ነበር። ዕዉነት ያልሆነ የሚጻፍ ኣይመስለኝም ነበር።

ሌላዉ የሃገር ሰዉ ኤዳ ነምን ጉዳን ህን ሶባ ብሎ የጠየቀዉ ነዉ። ትልቅ ሰዉ ይዋሻል እንዴ እንደማለት ነዉ። ሱፍ ለብሰዉ፣ ከረባት ኣስረዉ፣ ቴሌቭዥን ፊት ቀርበዉ ለህዝብ የሚሰራጭን ዉሸት ኣይቶ፣ ሰምቶ ታዝቦ።

የእሱም ድንቅ ጥያቄ ያደገበት ባህል ለዕዉነት ያለዉን አመለካከት ያንጸባርቃል። ዉሽት መስማት ማሳቀቅን ያንጸባርቃል።

ሁለቱም ያላቸዉን ባህል ነዉ ያንጸባረቁት።

Abere
Senior Member
Posts: 15358
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ኢትዮጵያን የበለጠ ማወቅ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ነዉ

Post by Abere » 21 Dec 2023, 10:34



ውጭ አገር ማዬት እና መኖር ከሁሉም በላይ ገንዘብ ሊገዛው የማይችል አንድ ትልቅ ጸጋ ቢኖር በአለም ዙሪያ ያሉ የሰው ልጆች ባህል ባህርይ እና አኗኗር ለመገንዘብ ያስችላል። በአንድ ገበያ ላይ ሁሉንም መሸመት እንደ ማለት ነው። One-stop shopping. ምንም ሳያይ እድሜውን የጨረሰ ሰው ለእኔ ያሳዝነኛል - ተወለደ - ሄደ ነው። ዳሩ ግን ወጭ አይተው አንዳች የባህርይ ለውጥ ማሳየት ያልቻሉ ደግሞ የበለጠ ያሳዝናሉ - ተምረውም ያልተማሩ፤ አግኝተውም ያጡ ይመስላሉ። የግጭት ፈረስ በመሆን ግጭትን በአጋሥስነት ይረዳሉ።


አንድ ትልቅ ነገር ግን አለ። ይኸው በሁሉም አለም እና ህዝብ ዘንድ ውሸት፤ ማታለል፤ መቦትለክ ፤ ማጭበርበር አለ። የማጭበርበሩ እና የመቦትለኩ ጉዳይ ምጥቀት፤ስልት እና ረቂቅነት ብቻ ነው የሚለያየው። Differential in level of sophistications and harm. የረቀቀው ውሸት እና ቡትልክና የጉዳቱ እና የጡጫው ምት ይለያያል። ጎረምሳ ከሚጭነኝ ምነው ጅብ በበላኝ ያለችው የአህያዋ አባባል እንደማለት ነው። ታዳጊ አገር በሆነችው ኢትዮጵያ ለምሳሌ ስርቆት ቀጥታ ከረሃብተኛ አፍ ስንዴ ሰርቆ አስፈጭቶ መሸጥ ይሆናል።

እንደ ሰዎች ግናዛቤ ሊለያይ ይችላል። በእኔ አተያይ ግን ኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል አንድ ወጥነት ባህርይ እንጅ ብዙ ዝብርቅርቅ ዘር የላትም። ኢትዮጵያዊያን አንድ የሚያደርጋቸው ውርስ የባህል እና የዘር ባህርይ ከሚለያያቸው እጅግ የገዘፈ ነው። ይህ ወጥነት ግን ማጠናከር ሲገባ እንድውለቀለቅ የሚያደርጉ አፈንጋጭ ሃይሎች አሉ - ጥቃቅን ኢምንት ሰፈራዊ የወጋ ወግ ልዩነት በማግዘፍ የውሸት አረፋ ቁልል በመከመር ኢትዮጵያ ልክ አንድ የአለም አህጉር አድርገው በመሳል ግጭት ይፈጥራሉ። ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይስትም ነው እና በፍዳ እና በመከራ ዘመን እንኳን ኢትዮጵያዊ ለአገሩ አብሮ ይቆማል። ግን አብረን መብላት አብረን መኖር ደግሞ ማወቅ እና መቻል አለብን። አንድት ባህልም የማንም ጎሳ የግል ሁና አታውቅም ወደፊትም አይቻልም። አገርም ባህልም የጋራ ነው። ኢምንት ጉዳይ አግዝፎ ማየት ደግሞ ውጭ ኑሮ ምን የባህርይ ለውጥ ያላመጣ ወይም ውሃ ውስጥ ገብቶ ውሃ አርሶት ያልታጠበ ጉድ ( weird, anomalous creature) ነው።

Post Reply