Misraq wrote: ↑18 Dec 2023, 10:19
ወንድማችን ሆረስ ብዙ ግዜ ጠቃሚ ሃሳብ ታነሳና የመፍትሄ ሃሳብ ሳትሰነዝር ታልፈዋለህ፥፥ እድሜና እውቀት ጠገብ እንደሆንክ እናውቃለን ስለዚህ እስቲ ኢትዮጵያ ከገባችበት ቅርቃር እንዴት ትውጣና የሁሉም ዜጋ መብት እኩል የሚከበርበትን የነጻነት ፍኖተ ካርታ አሳየን
በራስህ ስሜት ተውጠህ ሌሎችን ማዳመጥ አልቻልክም እንጂ ለጥያቄህ ከሞላ ጎደል አበረ ከላይ መልስ እየሰጠህ ነው ።
እኔ እዚህ ፎረማ ላይ ቢያንስ 20 ግዜ የለጠፍኩት ውልፍጥ የማይ አቋምና እምነት አለኝ ።
እሱም የኢትዮጵያ አጀንዳ ይባላል ። ኢትዮጵያ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊያን ከተደራጀችና ከተመራች ያላት ብሄራዊ አጀንዳ፣ ያላት ብሄራዊ ፋይዳና ፐርፐዝ በጣም ቀላልና ግልጽ ነው ። ልብ በል ይህ የማንም ጎሳ፣ ቡድን ኃያል ሆነ ደካማ፣ ትንሽ ሆነ ትልቅ ዘውግ ፍላጎትና ህልም አይደለም ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚሽን ማለት ነው ።
እነሱም 4 ናቸው ፤
ኢትዮጵያ የምትባለው ሕዝብና አገር ብሄራዊ አንድነቷ የጸና፣ ጠንካራና የተረጋጋች (እስቴብል) አገር መሆን አለባት፣ መሆን ነው አላማዋ ። ይህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ቁጥር አንድ ነው ። ከዚህ አጀንዳ ውጭ የሚያስብ ሁሉ ኢትዮጵያዊ አይደለም፣ እራሱን በፈለገው ስምና ቅጽል ቢጠራ ።
ኢትዮጵያዊ የተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (Political Community) ፍትህ (እኩልነት)፣ ነጻነት እና ዴሞክራሲ መፈለግ ብቻ አይደለም፤ ያለ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ መኖር አይችልም። ሰላም የሚባል ነገር እስከ አለም ፍጻሜ አያገኝም። ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚባል ነገር አይኖሩትም ። ስለዚህ 2ኛው የኢትዮጵያ ፋይዳ፣ የኢትዮጵያ አላማ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነትን መወለድና ማሳደግ፣ ማለትም ነጻና ፍትሃዊ ሕዝብ መሆን ነው ። ይህን የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ያልገባቸው ወይም የማይቀበሉ ጸረ ኢትዮጵያ ስብስቦች ናቸው የዚህ ሁሉ መከራና ውርደት ምክንያቶች ።
3ኛው የኢትዮጵያ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን የሚባሉት ሕዝብን፣ ዜጋዎችን የበለጸጉ፣ ያደጉ፣ የለሙ፣ የተማሩ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ ሕዝብ፣ ዚጋ ማድረግ ነው 3ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳና ፋይዳ ። ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገር፣ እንደ አንድ ሕዝብ፣ እንደ አንድ ማህበር፣ እንደ አንድ ሲስተም አላማ፣ ፋይዳ አላት ። ይህን ፋይዳ ለመተግበር ነው ህያው ሆና ምትቀጥለው ። የኢትዮጵያ አጀንዳን አንድ ሁለት ብለው መቁጠር የማይችሉ መሃይም የጎሳ ጥርቃሞዎች ናቸው የዚህ ሁሉ ሰቆቃ ምክንያቶች ።
በመጨረሻም 4ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ የሚፈጥር፣ ችግር የሚፈታ፣ የሚራመድ፣ ከከባቢውና ኢኮሎጂው ጋር የታረቀ፣ አፈሩን። ዉሃውን፣ እንሳሳውን፣ እጸዋቱን፣ አየሩን በሃላፊነት የሚንከባከብ ፣ መንፈሳዊ ፣ በፈጣሪ ኃይል የሚያምን በሞራልና ስነ ምግባር መርሆዎች የተለጎመ ካልቸር መፍጠር፣ መገንባት እና መጠበቅ ነው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር ምንድን ነው? ምን መሆን አለበት ብለው መጠየቅ የማይችሉ ቀድሞ ነገር እራሳቸው ካልቸር አልባ የሆኑ ከብቶች ናችው በዚህ ታላቅ ሕዝብና ታላቅ አገር ጫንቃ ላይ ተቀምጠው ያለም ማፈሪያ ያደረጉን ።
የኢትዮጵያ መፍትሄ ይህ ብቻ ነው ። ከዚህ ውጭ ያሉት በሙሉ ተፈራራቂ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው ። እነዚህ 4 ቀላል ግቦች እንዳይሳኩ ሌት ተቀን የሚባክኑ መሃይሞች፣ እረኞች፣ አረመኔዎችና የውጭ ጥላት አሽከሮች ናቸው ኢትዮጵያን በዚህ መከራ ውስጥ ይዘዋት ያሉት ።