Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Za-Ilmaknun » 21 Nov 2023, 18:46

A second round of peace talks between Ethiopia's government and a rebel group aimed at ending a decades-old conflict in the country's largest region Oromiya has ended without a deal, both sides said on Tuesday.

The negotiations in Tanzania between the government and the Oromo Liberation Army (OLA) followed talks in April and May that also failed to produce an agreement.

https://www.yahoo.com/news/ethiopia-say ... 09182.html


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Za-Ilmaknun » 22 Nov 2023, 14:09

ከሃዲዎቹ ክህደት ተፈጸመባቸው #ግርማካሳ

ራሱን ኦላ ብሎ የሚጠራዉና በዋናነት በወለጋና ጉጂ ዞኖች የሚንቀሳቀሰው ቡድን፣ በዋና መቀመጫው፣ በቄሌም ወለጋ አንፊሎ ወረዳ፣ ከብልጽግና ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ፣ በርካታ ከፍተኛ ኮማንደሮቹ እንደሞቱ፣ ዋና አዛዡም ጃል መሮ ራሱ ሊገደልና ሊያዝ ሰዓታት ሲቀሩት፣ ከአራት ኪሎ በነ ጌታቸው ጉዲና በኩል ትእዛዝ መጥቶ የብልጽግና ጦር እንቅስቃሴዉን እንዲያቆም መደረጉን፣ ጃል መሮ በሌላ ሄሊኮፕተር ከአካባቢው እንደተነሳ፣ ከብልጽግናዎች ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ውይይቱ ተደርጎ ካለቀ በኋላ፣ ለድራማ ወደ ታንዛኒያ እንደተኬደ ገልዤ ነበር፡፡

በማከልም፣ "እነ ጃል መሮ በአሁኑ ወቅት በታንዛኒያ ናቸው፡፡ ከብልጽግናዎች ጋር አስቀድመው የተስማሙበትን ካላከበሩ በቀር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አይችሉም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የነ ጃል መሮ ነገር ያበቃለት ይመስላል፡፡ እነ ጃል ከብልጽግና ጋር የተስማሙትን ካከበሩ፣ የኦላ ቅሪት ጦር አብዛኛዉ የብልጽግና ጦርን የመቀላቀል ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ካልሆነ ግን እረኛ የሌላቻው በጎች እንደሚበተኑት፣ የኦላ ጦር የተበታተነ ይሆናል፡፡ በቀላሉም ይተናል፡፡ ብዙዎችም ተስፋ ቆርጠው እጅ ሊሰጡ ወይንም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሊመለሱ ይችላል" ነበር ያልኩት፡፡

እነ ጃል መሮ ያውቃሉ፣ የአብይ አህመድ አገዛዝ በተለይም በወለጋና በጉጂ ማህበረሰብ ምን ያህል እንደተጠላ፡፡ እንደ ሌንጮዎቹና እንደነ ቀጀላ መርዳሳ፣ የብልጽግና አካል ሆነው፣ ከብልጽግና ጋር ተስማምተው፣ በነ አብይ አህመድ ቃል የተገባላቸውን ስልጣን ቢያገኙ ለጊዜው ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ግን ሰዎቹ ብልጥ ናቸው፡፡ ወድቆ እየተንፈራገጠ ካለ ፣ መጨረሻው ከተቃረበ አገዛዝ ጋር መነካካት አልፈለጉም፡፡ ታንዛኒያ እንደሄዱ፣ በዳያስፖራ ያሉ የኦነግ ደጋፊዎችን በዙም አነጋገሩ፡፡ በዚያ የተሰጡ አስተያየቶች እንደ ምክንያት ቆጥረው፣ ፍሬቻ አብርተው ታጠፉ፡፡ እነ አብይ አህመድን አፍንጫችሁን ላሱ አሏቸው፡፡ ተስማምተው ሄደው፣ በታንዛኒያ ብልጽግናዎችን ከዷቸው፡፡ ከሃዲዎቹ ነርሱም ተካዱ፡፡ ለገሰ ቱሉ ተናዶ መግለጫ ሰጠ፡፡

እነ ጃል መሮ በነ ደቡብ አፍሪካ ጥገኝነት ሊጠይቁ አስበዋል እየተባለ ነው፡፡ ድርድር የተባለው እንደከሸፈ ሁለቱም ወገኖች እየተናገሩ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ምንድን ነው የሚሆነው ብትሉኝ፣ እንዲህ ነው ፣ እንደዚያ ነው ብሎ ለመገመት ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ፡

ኦላ በወለጋና በጉጂ በስፋት የመንቀሳቀስ አቅምና ጉልበት ይኖረዋል ብዬ አላስብም፡፡ ኮማንደሮቹ ከተገደሉበትና ከተሰደዱበት፣ በሜዳ ላይ ያለ መሪ በሌበት ሁኔታ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ ሌላ መሪ እስኪነሳ ድረስ፡፡ አንድ በሉ፡፡

በዚያ ላይ ኦላ ከአምስት አመት በላይ ተዋግቶ ያመጣው ምንም አይነት ውጤት ስለሌለ፣ ህዝቡ ከሰላም እጦት የተነሳ ስለተማረረ፣ በረሃብም በወረሺኝም እያለቀ ስለሆነ፣ ማሸነፍ በማይቻል በተራዘመ ጦርነት መሰቃየት ስለማይፈልግ፣ ጦርነቱን አይደገፍም፡፡ ያለ ህዝብ ድጋፍ ደግሞ ኦላ ብዙም ገፍቶ መሄድ አይችልም፡፡ ማሸነፍ የማይቻልን ጦርነት እያደረጉ የህዝብን መከራ ማራዘም ደግሞ ድንቁርና ነው፡፡ ሁለት በሉ፡፡

በዚያ ላይ የኦላ ጥያቄዎች ተራና ትርኪምርኪ የስልጣን ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ሲያደርጉት የነበረው ጦርነት አምስት ሳንቲም ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጥቅም ጋር የተገናኘ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ በድርድሩ ወቅት አቀረቡት የተባሉ ጥያቄዎችን እንመልከት፡፡

"አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ትሁን" የሚለው አንደኛው ነው፡፡ ይህ የ እብደት ጥያቄ ነው፡፡ የወለጋ ህዝብ ተደምሮ የአዲስ አበባን ህዝብ አያክልም፡፡ ወደ አስር ሚሊዮን ነው የሚጠጋው፡፡ ይህ ህዝብ "ቢመችሽም ባይመችሽም፣ ሸገር ፊንፊኔ አይሆንልሽም" ነው እያለ ያለው፡፡ የአስር ሚሊዮን ህዝብ መብትን ረግጠው፣ ከመሃሉ ህዝብን ጋር የኦሮሞ ማህበረሰብን ማጋጨት እንዴት ነው ነጆና አርጆ፣ ጃርሶና ጉሊሶ፣ አቦምሳና አጋምሳ፣ ኮፈሌና በደሌ የሚኖረውን ኦሮሞ የሚጠቅመው ?

ሌላው በኦሮሞ ክልል የሽግግር መንግስት ይቋቋም ያሉት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የስልጣን ጥያቄ ነው፡፡ እነርሱ ስልጣን ማግኘታቸው በምን መስፈርት ነው ለኦሮሞ ጥቃም እንደሚያስገኝ ማስተማመኛ የሚሆነው ? ይኸው እነ ቀጀላ መርዳሳ፣ እነ ሌንጮ ባቲ በስልጣን ተንበሽብሸው የለም እንዴ ?

ኦሮሞኛ የኢትዮጵያ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን ያሉት ነገር ደግሞ አለ፡፡ ይሄንን ማን ተቃወም ? ይህ ጥያቄዎቻቸውን ራሱ ብልጽግና አክብሮት በፓርቱ ደረጃ ኦሮሞኛ የፓርቲው የስራ ቋንቋ ሆኗል፡፡ ምንም ተቃዋሞ በሌለበት ጉዳይ ጦርነት ውስጥ መግባት ምን አመጣው ?

የጠራ፣ ህዝብን የሚያሳምን፣ የህዝብ መሰረታዊ የመኖር፣ የሰላም፣ የፍትህ፣ የልማትና የእኩልነት ጥያቄዎችን አንግቦ ያልተነሳ ድርጅት የትም አይደርም፡፡ ሶስት በሉ፡፡

የብልጽግና ጦር የኦላ መሸሸጊያ የነበሩ በርካታ የወለጋ ጫካዎችን መቆጣጠር ከቻለ፣ አንፊሎ ወረዳ እንዳደረገው፣ ኦላ እንደ ልብ የመንቀሳቀስ አቅም አይኖረውም፡፡ አራት በሉ፡፡

ኦላ ከፋኖዎች ጋር መተባበር ቢችልስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ኦላ ከፋኖዎች ጋር ሊተባበር አይችልም፡፡ ለፋኖዎች ኦላ ማለት የኦሮሞ ብልጽግና ማለት ነው፡፡ ፋኖዎች እኮ እነ አብይ አህመድን የሚታገሉት ሰዎቹን ብለው አይደለም፡፡ ከሰዎቹ በግለሰብ ደረጃ ጸብ የላቸው፡፡ አስተሳሰባቸውም ፖለቲካቸውን እንጂ፡፡ ኦላና እነ አብይ ደግሞ በስልጣን እንጂ የተጠሉት፣ በአስተሳሰብ ፣ በፖለቲካ የአንድ ሳንቲም ሁለት ግልባጮች ናቸው፡፡

ግርማ ካሳ

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Za-Ilmaknun » 22 Nov 2023, 14:17

Very interesting insight!! Now Diriba kumssa & Co. are in refugee camps while those who are torturing the oromo people are basking in the glory of power gotten through treacherous political overtures.


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Za-Ilmaknun » 22 Nov 2023, 14:34

While Mr. Tullu, who is an ADP representative in PP, is raving and ranting about why the OLF branch of OPDO is not taking the terms offered to it for a lavish "eternal" life in Addis, Jal Kumssa is pointedly eyeing only the throne at arat killo. In the mean time the OLF branch is speaking out about the attrocities committed by the OPDO branch against the Amhara community in the Oromo fiefedom.

ከዚህ ቀደም በታንዛኒያ ዛንዚባር የተካሄደው ንግግር ያለ ውጤት ተጠናቆ እንደነበር ያስታወሰው መንግሥት፣ የአሁኑም ፍሬ ሳያፈራ ውጤት አልባ ሆኖ መቅረቱን በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታትም የሽብር ቡድኑ ካለፈው ስህተት ተምሮ የድርድር ነጥቦቹንም ኢትዮጵያ ከደረሰችበት ምዕራፍ ጋር ለማጣጣም ይሞክር ይሆናል በሚል ተስፋ ሁለተኛ ዙር ውይይት በታንዛንያ ዳሬሰላም ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወቀው መንግሥት፣ ‹‹በሽብር ቡድኑ ዘንድ በዚህኛው ዙርም ‹መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ› ከሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርድር ነጥብ ማምጣት አልቻለም ሲል ድርድሩ የከሸፈበትን ምክንያት አስረድቷል።

‹‹በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በሕዝቦች ሕይወትና ንብረት ጉዳት በማድረስ የሰላም ጠንቅ ሆኖ ከቆየው የሸኔ የሽብር ቡድን ጋር፣ በታንዛንያ ዛንዚባር ከወራት በፊት ውይይት ተካሂዶ ሳይቋጭ መቅረቱ ይታወሳል፤›› ያለው መንግሥት፣ ‹‹በዚሁ ውይይት ወቅት የሽብር ቡድኑ ከ60 ዓመታት በፊት የኦሮሞም ሆነ የሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በሙሉ ጥያቄዎች የነበሩና ተመልሰው ያደሩ ጥያቄዎችን አንስቷል፤›› ብሏል።

በተለይም ከለውጡ በኋላ በሥራ ላይ የዋሉ ጉዳዮችን ከማነብነብ ውጪ የሚቆጠርና የሚቋጠር አጀንዳ ማምጣት ያልቻለው ኦነግ ሸኔ፣ በመንግሥት በኩል በስክነትና በማግባባት ላይ ብቻ ታጥሮ በቀጠሮ ተንጠልጥሎ እንዲቆይ ማድረጉ ተመራጭ አካሄድ ነበር ሲልም መንግሥት አስታውቋል።

‹‹ነገር ግን የኢፌዴሪ መንግሥት በአገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ኢትዮጵያ ያሏትን ፀጋዎች ወደ ተጨባጭ ሀብትና አቅም ቀይራ ብልፅግናዋን ታረጋግጥ ዘንድ ካለው ጉጉት በመነጨ፣ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ ዕልባት ለመስጠት ሞክሯል። ነገር ግን የሽብር ቡድኑ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል፤›› ብሏል።

‹‹ኦነግ ሸኔ በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል፤›› ያለው መንግሥት፣ ውይይቱ በትናንትናው ዕለት ያለ ውጤት መበተኑንና ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ውይይቱ እንዲሳካ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ሁሉ ምሥጋናውን አቅርቧል፡፡

https://www.ethiopianreporter.com/124237/

Abere
Senior Member
Posts: 15369
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Abere » 22 Nov 2023, 15:12

What a mockery, this is just a stunt to deceive innocents. OLF sitting across the table with OLF. This is like an illusion a person is talking to himself; and he listening to his own talks. These chimpanzees should look for another universe where they can show this foolish drama. Our universe has figured this silly drama a long time ago. Oneself at Arat Killo and the other self in the jungle - oneself in two places at the same time. It has been always an agreement of 100% on purpose, action and direction. Bleed, destroy Ethiopia and deliver the Chimpanzee kingdom of Orroommiiaa.

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: OPDO talking to itself gone ashtray. The greed and the scramble for rowdy power collapsing under its own weight

Post by Za-Ilmaknun » 22 Nov 2023, 15:26

Abere wrote:
22 Nov 2023, 15:12
What a mockery, this is just a stunt to deceive innocents. OLF sitting across the table with OLF. This is like an illusion a person is talking to himself; and he listening to his own talks. These chimpanzees should look for another universe where they can show this foolish drama. Our universe has figured this silly drama a long time ago. Oneself at Arat Killo and the other self in the jungle - oneself in two places at the same time. It has been always an agreement of 100% on purpose, action and direction. Bleed, destroy Ethiopia and deliver the Chimpanzee kingdom of Orroommiiaa.
They are the worst!! It is sad to see Ethiopia falling in the hands of such scumbags of the world and falling apart in short amount of time. They lie, they cheat, they murder. All TPLF was able to accomplish was bleeding Ethiopia for 17 years, looting the country brazenly for 27 years and finally handing the country over to such ruthless thieves and murderers as promised by the evil Zenawi. They are paying the price with us, though. :mrgreen: Karma cought up with them.

Post Reply