Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

አሁንም ድረስ በ ትግራይ ማጎሪያ ውስጥ እየተሰቃዩ ያሉ በ አብይ አገዛዝ የተረሱ የመከላከያ አባላት ፡ የመንግሰት ያለኽ እያሉ ነው

Post by Za-Ilmaknun » 13 Nov 2023, 12:16

የ ኦህዴድ አገዛዝ እራሱን የ ኢተዮዽያ መንገስት በማስመሰል ከ ትህነግ ሰራዊት ጋር እንዲዋጉለት የላካቸው የሰራዊት አባላት በምርኮኝነት ተይዘው ላለፉት ሁለት አመታት የት ወደቃችሁ የሚላቸው አጥተው፡ በትህነግ ቂም የጠገበ ዱላ በየማጎሪያው እየተደበደቡ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ሞራል የለሽ ሰውበላ አገዛዝ የሚታገል ካለ ደሙ ደመከልብ ከመሆኑም በላይ ፡ በየደረሰበት ለሚያደርሰው ጥፋት ከጠያቂነት አይድንም፡፡ የትህነግን ወረራ ለመቀልበስ በየዱር ገደሉ ወድቀው የቀሩት የመከላከያ አባለት ዛሬ ላይ ቤተሰባቸው ስለመስዋእትነታቸው ሳይነገረው እርሙን ተሽክሞ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል ግን ጨፍጫፊው ትህነግ የ አራት ኪሎ ታማኝ ቡችላ በመምሰል የ አብይን ወንበር ለማስጠበቅ የተዋደቀውን ሰራዊት በመፈረጅ፡ ተረት እየሰራበት ይገኛል፡፡ አሁን ላይ የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ እና ቅርስ እያወደመ ያለው ሰራዊት በቅርቡ የአኦህዴድ መኳንንቶች ተጠያቂነቱን ለሱ አሸክመው እኛ ከደሙ ነፃነን ብለው እንደሚክዱት እየኖርንበት ያለ እውነታ ነው፡፡የ ኦህዴድ አገዛዝ የ ክህደትና ጭካኔ መገለጫ የወንበዴ መሀይማን ስብስብ መሆኑን በተግባር ደጋግሞ እያሳየን ነው፡፡