Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42670
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ፍትህ ነው! ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!

Post by Horus » 12 Oct 2023, 01:48

በእኛ በጉራጌዎች ካልቸር ኬር ማለት ሰላም፣ ስርዓት፣ ማለት ነው ። የጉራጌ ካልቸር የኬር (ኬራማ) ካልቸር ይባላል።

ስርዓት የሌለው ነገር ሁሉ ቀውስ ነው ! ፍትህም ሆነ ሰላም፣ ስርዓትም ሆነ እኩልነት መቆሚያቸው ፍቅር ነው !

የጥላቻ ካልቸር ውስጥ የሚጨማለቁ ፍትህ አልባ፣ ስርዓት አልባ፣ ስኛት የለሽ ፣ የግፍ አምላኪዎች ሰው የመሆን ምስጢር፣ ከንሰሳ በላይ፣ ከአራዊትነት በላይ ማደግ ያልቻሉ እጅግ አሳዛኝ ፍጡራን ናቸው !

በዚህች አለም ላይ የማንኛውም ፣ የማንኛውም ችግር መፍትሄ ፍትህ ብቻ ነው! ሌላ የችግር መፍትሄ የለም !!

ሆረስ ነኝ
https://www.youtube.com/shorts/cdo2DvJTLEA


Horus
Senior Member+
Posts: 42670
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ፍትህ ነው! ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!

Post by Horus » 12 Oct 2023, 03:02

ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን ነው ! መስቀልና የወጣቶ መፋቀሪያ ሴራ (ስርዓት) ሊያበቃ 4 ቀናት ብቻ ቀርተዋል ዘና በሉ ! በነገራችን ላይ በ ግኧዝ ሴራ ማለት ነጠላ ስም ሲሆን አንድ ሕግ፣ ደምብ፣ ወይም ሲስተም ማለት ነው ። የሴራ ብዙ ስሙ ሴራት (ስርዓት) ነው ። በተለምዶ ስርዓት ወይም ስነ ስርዓት የምንለው ሴራዎች ማለት እንጂ አንድ ስነት ብቻ አልነበረም ። አንድ ነጠላ ስርዓት ፣ ለምሳሌ ከታች ያለው የጋብቻ (ሸባል) ወይም ፍጥምጥም (ጨግ) አንድ ሴራ ነው እንጂ ስርዓት (ሴራዎች) አይደለም! ጉራጌ ኬር ይሁን ሲል ሴራ ይሁን፣ ስርዓት ይሁን ሰላም ይሁን ማለቱ ነው!


Naga Tuma
Member+
Posts: 7362
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ፍትህ ነው! ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!

Post by Naga Tuma » 12 Oct 2023, 14:02

Horus wrote:
12 Oct 2023, 01:48
ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!
ትክክል።

ሴረ ቱማ መቼ እና የት እንደተጀመረ ማወቅም ያስፈልጋል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42670
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ፍትህ ነው! ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!

Post by Horus » 12 Oct 2023, 19:24

Naga Tuma wrote:
12 Oct 2023, 14:02
Horus wrote:
12 Oct 2023, 01:48
ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!
ትክክል።

ሴረ ቱማ መቼ እና የት እንደተጀመረ ማወቅም ያስፈልጋል።
ሴራ የትንታዊት ግብጽ ስልጣኔ ቃል ሲሆን ዛሬ የአብራሃማዊ ሃይማኖቶች ፣ ክርስትና፣ እስልምና እና ጁዴኢዝም የተመሰረቱበት ጽንሰ ቃል ነው ። ግሪኮች ከግብጽ ወስደው ኬራቲ (ኃይል ወይም ፈጣሪ ኃይል) የሚሉት ሲሆን ላቲን ወስድ ክሪኤሽን የሚለው ቃል ነው ። በእስልምና ኬይር ሲሆን ቁርዓን ሸሪአ (ኢስላሚክ ሕግ) የሚባለው ነው ኬር ወይም ሴራ ማለት ። ሴራ ኬራ ማለት ነው ። ኬይር ማለት በአረብኛ መልካምነት (ኬርታ በጉራጌኛ) ወይም ጉድነስ ማለት ነው ። በሳንስክሪት ፣ በህንዶች ቅዱስ ቁንቋ (ልክ እንደ ግእዝ) ኬይር ማለት ልክ እንደ አረብኛውና ግዕዙ ፤ሰላም፣ ስራዐት (ኦርደር)፣ የነገሮች ሁሉ ደህንነት (መልካምነት) ማለት ነው። ሌላው ቀርቶ ምርቃት፣ ባርኮት፣ ኬርታ የሚለው ቃል ነው። ኢስላም፣ ሰላም፣ ማለት ኬራም ማለት ነው ።

ኬርታ የጉራጌ ብቸኛ ዩኒቨርሳል ኮስሞሎጂና የእምነቱም የካልቸሩም መነሻና መቆሚያ መሰረት ነው ። እግዚአብሄር በጉራጌኛ እዝጌር ይባላል! እዝጌር ማለት እዝኬር ማለት ነው ። ጉራጌ ሌላ ቃል የለውም። እዝ ኃይል ማለት ሲሆን እዝኬር ሁሉን ነገር በስርዓት፣ ህግጋትና ሰላም ያቆመ ኃይል ማለት ነው ።

ስለዚህ ነው ጉራጌ ምንም ነገር ሲጀምርና ሲጨርስ ኬር ዪሁን የሚለው! ኬርታ የሌለው ሰውም ሆነ ሕዝብ ሴራ፣ ሰላምና ፍቅር ሊኖረው አይችልም፤ እመነትም ሆነ የሞራል ፍልስፍና ስለማይኖረው! ምንም ነገር ኬር የሚሆነው፣ መልካም የሚሆነው ልክ ሲሆን፣ ትክክል ሲሆን ፣ ፍትህ ሲሆን ነው ። በፍትህ የማያምን ሰው ሰላም ሊኖረው አይችልም ፤ በፍትህ የማያምን ፍትህን የማያመልክ ሰውም ሆነ ሕዝብ ሴራ ሊኖረው አይችልም፤ ሴራ የሌለው ሕዝብ ሰላም የለውም!

Horus
Senior Member+
Posts: 42670
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ፍትህ ነው! ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም! ሰላም ማለት ስርዓት ማለት ነው!

Post by Horus » 13 Oct 2023, 01:42

የጉራጌ ሴራ! የጉራጌ ፍትህ! የጉራጌ ሰላም በተግባር ይህን ይመስላል! ይህ አንድ የጋብቻ ሴራ ነው ። የወንድ ቤተሰብ ወደ ሴት ቤተሰብ ለጋብቻ ሽማግሌ ልከው እሺታ በሚያገኙብትና ፍጥምጥም የሚደረግበት ቸግ የሚባለው ሴራ (ስርዓት) ነው ። እዚህ ቪዲዮ ውስጥ የኬርታ ምርቃት ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስና ሙስሊም የጉራጌ ቤተሰቦች አስደማሚ ፍቅር ተመልከቱ! ይህ ነው የፍቅር የሰላም የኬርታ ካልቸር የሚባለው !


Post Reply