ከልጅነቴ ጀምሮ የማዉቀዉን የኢትዮጵያ ኣዲስ ኣመት መምጫና እና አከባበር ባህል እዚህ መድረክ ላይ መጻፍ ካሰብኩኝ ብያንስ ሁለት ኣመታት ሆነዋል። ኣዲስ ኣመት በመጣ ቁጥር ሳልጽፈዉ ኣለፈ እና ለሚቀጥለዉ ኣመት እያልኩ የዚህም ኣመት ልያልፍ ደረሰ።
በልጅነት የየሁት በሃገሩ ሁሉ ተመሳሳይ ይመስለኝ ነበር። ኣሁን ነዉ ወይስ ኣይዴለም ብዬ እራሴን ለመጠየቅ ደረስኩ። ምናልባትም ይህ ኣዲስ ጥያቄ እንዳይሆን ኣዲስ ኣመት እየመጣ ሳላካፍል ያዘገየኝ።
ኣሁን የማዉቀዉን ባህል የየትኛዉ የኢትዮጵያ ማህበረስብ ወይም ጎሳ ነዉ ብዬ በጥልቀት የምታዉቁትን ወይም ያጠናችሁትን ልጠይቅ። ምናልባትም በየቤቱ የሚከበር ባህል መቼ እንደተጀመረ ባይታወቅም ዘላቂነት ያለዉ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
ከሆነ መቼ የተጀመረ ነዉ ዘመናትን ኣሳልፎ ዛሬ የደረሰዉ?
የማስታዉሳቸዉ የሚከተሉት ናቸዉ። በትክክል ካላስታወስኩ እታረማለሁ። የዘነጋሁ ካሉ ይጨመሩበት።
አመርቲ፥ የመስቀል አይነት ሆኖ ኣንዱ ጫፍ ላይ ለክር ማስገብያ መጠንቆ ያለዉ ነዉ። እናቶች ኣንገቶቻቸዉ ላይ ኣነጠልጥለዉ ይኖራሉ።
መስቅል፥ መስቀል መስቀልም በዓልም ነዉ።
ቡሄ፥ ነሃሴ 12፣ የሚካኤል ቀን ወንዶች ልጆች ችቦ በማብራት የሚከበር። ለኣመት መለወጫ ችቦ አራት ግዜ ከሚበሩት ዉስጥ ይህ የመጀመርያዉ ነዉ።
ችቦ በኣብዛኛዉ ቀመጤ ከሚባል አነስተኛ ዛፍ ነዉ የሚዘጋጀዉ። ለችቦዉ መብራት ሁለት ሳምንታት ሲቀሩ ኣስቀድሞ ተቆርጦ እንዲደርቅ ይሆናል።
የቡሄ ቀን ብቻ ነዉ እናቶች ሆነ ብለዉ ለእያንዳንዱ ልጅ ለብቻ ሙልሙል ዳቦ ሰርተዉ ለእራት የሚሰጡት።
ሙከ ዻባ፣ ጋፈ ገርማማ፥ እነዚህ የቡሄ ማግስት ነሃሴ 13 ይፈጸማሉ። ሙከ ዻባ ማለት ዛፍ ተከላ ማለት ነዉ። ችግኝ ሳይሆን ያደገ ወይራ ዛፍ በኣንድ የሃገር ኣዛዉንት ተቆርጦ ኣማካይ ቦታ ይተከላል። ካልተሳሳትኩ የክረምት ረግረግ መሬት ከዛ በኋላ መጠንከር እንደምጀምር ለአከባቢዉ ምልክት ማስቀመጥ ነዉ።
የክረምት ረግረግ መሬት መጠንከር መጀመሩን ማሳያ የዛኑ ቀን የፈረስ ገርማምሳ ማሳየት ነዉ። የፈረስ ገርማምሳ በማሰገር እና መጋለብ መካካል ነዉ ማለት ይቻልል። ልግልብያ/ጉሉፉ/ጋሎፕ መንደርደርያ ነዉ።
የዛን ቀን ግልብያ የማይሆነዉ ረግረግ መሬት ላይ ግልብያ ፈረስን የሚጎዳ ሰለሆነ ፈረስን ላለመጉዳት ነዉ። መሬት እየጠነከረ ሲሄድ ለግልብያ እየተዘጋጀን ነዉ ለማለት ነዉ።
እንቁጣጣሽ ዋዜማ፥ እንግጫ ይነቀል እና ለማግስቱ ይዘጋጃል። ችቦ በኣባቶች እና ወንዶች ልጆች ይበራል። የቤተሰብ ግቢ ዉስጥ። ለኣባቶች ይህ የመጀመርያዉ ችቦ ማብራት ነዉ። ለወንዶች ልጆች ሁለተኛዉ ነዉ።
የእንቁጣጣሽ ቀን፥ በጠዋት ተነስተዉ፣ ቁርስ እየተበላ እንግጫ ይጎነጎን እና የቤት ምሶሶ እና ኣናት ላይ ይታሰራሉ። የቤት ምሶሶ ላይ የሚታሰረዉን የሚጎነጉን የቤቱ ኣባወራ ነዉ። ሌሎች ለራሳቸዉ ይጎነጉናሉ። ያልቻለ ከታላቅ ወንድም ወይም ኣባት እርዳታ ይደረግለታል።
ብዙም ረፈድ ሳይል አባወራ በግ ያርድ እና ወድያዉ ከስጋ ዉስጥ ትንሽ ዘልዝሎ፣ ዉጪ እሳት ተቀጣጥሎ፣ ዝልዝሉን ወይራ እንጨት ላይ ኣድርጎ ጠብሶ የቤተሰብ አባላትን ሁሉ ያቀምሳል። በባህል አባወራ ከማረድ እስከ ጠብሶ ማብላት ምግብ መስራት ይህ ነዉ።
ከዘ የበጉ ስጋ ተሰርቶ ጣላ እየተጠጣ አመት በኣሉ ያልፋል። ከሰኣት በኋላ ሴቶች ልጆች ተሰባስበዉ በሰፈር ቤቶች እየሄዱ ለምለም እያሉ ስጦታን ያገኛሉ።
የዘን ቀን አባወራ ከግቢዉ ከወጣ መንገድ ላይ ያገኘዉን ሌላ ሰዉ በገ ገነ ነጋን ባታኒ ቦቃ ብራ ኣርግተን፣ ሰዴን ሰዴተት ነጋን እስኒፍ ሃ ናነኡ ይላል፣ ይባባላሉ።
እብደ እጆሌ፥ ይህ ወንዶች ልጆች ብቻ የምያበሩት ሶስተኛ ችቦ ማብራት ነዉ። ከደመረ ቀን፣ በተልምዶ መስቀል የሚባለዉ፣ ጥቂት ቀናት በፊት ነዉ። የመስከረም ሚካኤል ቀን ይሁን ከዘ በኋላ ለግዜዉ ዘንግቻለሁ።
መስቀል፥ ይህ ዋናዉ የችቦ ማብራት ቀን ነዉ፣ መስከራም 16። በየግቢዉ ሳይሆን በሰፈር፣ ጎረቤቶች ተሰባስበዉ ኣብረዉ ትልቅ ደመረ በመስራት።
ደመራን የምያዘጋጁት ተባብረዉ ነዉ። የዛኑ ቀን በሬን ለቅርጫ የምያርዱት ተባብረዉ ነው። ከቅርጫ እና ጠላ ጋር መስቀል ትልቅ ድግስ ነዉ። ለዚህም ነዉ መስቀል ፊ ገልገል ዋኪ ህን ቀቡ የሚባለዉ። መስቀል እና ማታ ስስት የለዉም ማለት ነዉ።
ሴቶች ልጆች የቤት በር ጎኖች ላይ ኬሎ ወይም አደይ አበባዎችን ዘርዘር ኣድርገዉ በማስቀመጥ ቤቱን ያሳምራሉ።
ኣብረዉ ችቦ የምያበሩት የእያንዳንዱ ቤተስብ ወንዶች ሁሉም ችቦዎቻቸዉን ከየቤቶቻቸዉ ወስደዉ ደመራዉን በኣንድነት ያቀጣጥላሉ። ቀኑ መጨለም ሲጀምር።
በሰፈሩ ኣንጋፋ የሆነ አባወራ ደመራዉን በችቦዉ ማቀጣጣል ይጀምራል። ኣንዴ ከተጀመረ ደመራዉ ዙርያ ሰልፍ ገብተዉ በክብ እየዞሩ ደመራዉን በችቦዎቻቸዉ እየወጉ፣ ከፋትን እየረገሙ፣ መጨረሻ ላይ ችቦዎቻችወን ወደ ደመራዉ ወርዉረዉ ሲቀጣል ቆመዉ ያያሉ። ጎረምሳዎች ካሉ የመስቀል ባህል ዘፈን እየዘፈኑ ይቆያሉ።
የመስቀልን ችቦ ማብራት ክፋትን መርገም ብቻ ሳይሆን እርቅንም ለማስፈን ነዉ። ሰዎች ተቃርነዉ ኣብረዉ ችቦ ኣያበሩም ኣሉ። ይህ ማለት ኣስፈላጊ ክሆነ በሰፈሩ እርቅ በየ አመቱ ይመጣል ማለት ነዉ። ወይም መቃራን በሰፈሩ ከኣንድ አመት በላይ እድሜ ኣይኖረዉም ማለት ነዉ።
ደመራዉ ዉስጥ መተጀቦ የሚባል ዋና ዛፍ መሃሉ ላይ ይተከላል። ያ ዛፍ ተቀጥሎ እስኪወድቅ ወደ ቤት ኣይመለስም።
ችቦ ከቤት ሲወጣም ሆነ ወደቤት ከተመለሱ በኋላ የተለዩ አከባበሮች ኣሉ።
ችቦዉ የሚበራበት ምድጃ ዉስጥ ጀባ የሚባል የግራር ግንድ ኣስቀድሞ ተቆርጦ መቀጣጥል ይጀምራል። ከዛ ግንድ እና ምድጃ እሳት ዉስጥ ነዉ አባ ወራ የመጀመርያዉ ችቦ ለኳሽ የሚሆነዉ። ችቦዉን ከለኮሰ በኋላ የቤቱን ምሶሶ እና ኦኮሌ የሚባል የወተት ማለብያ ለምልክት ያህል ያስነካል፣ እየመረቀ። ከዛ በኋላ ነዉ ችቦዉን ይዞ ከቤት ወጥቶ ሌሎችም ወንድ ልጆች ችቦዎቻቸዉን ማቀጣጠል የሚጀምሩት።
ደመራዉን ኣቀጣጥለዉ ወደቤት ከተመለሱ በኋላ ኣባት ወንዶች ልጆቹን፣ እናት ሴቶች ልጆቿን ይመርቃሉ።
እናት ገንፎ ሰርታ ትጠብቃለች። አባትም፣ እናትም በርጩማዎቻቸዉ ላይ ተቀምጠዉ፣ ቀቤ የሚባል የወተት ማስቀመጫ ክዳን ላይ ገንፎ በትንሹ ጎድገድ ብሎ፣ እዛ ጎድጓዳ ላይ የነጠረ ቅቤ ተደርጎ፣ ሰርዶ ተነቅሎ ተዘጋጅቶ ልጆቻቸዉን ይመርቃሉ።
አባት ወንዶች ልጆቹን፣ እናት ሴቶች ልጆችዋን ከታላቅ ወደ ታናሽ ተራ በተራ ሳርዶዉን ቅቤ ዉስጥ እየነከሩ አንገት እና ግንባር ላይ እያስነኩ ይመርቃሉ። ምርቃቱ ካበቃ በኋላ ሁሉም የክዳኑን ገንፎ ተራ በተራ ይቀምሳሉ።
የማልረሳዉ ምርቃታቸዉ ሉቡን ዖል፣ ሉቡን ቡል፣ አደ አርገዹ የሚል ነዉ።
ሉቡ የህይወት እስትንፋስ አይነት ይመስለኛል። በባህል አንገት ዉስጥ ነዉ ያለዉ ብለዉ የምያስቡ ይመስለኛል። ሉቡን በሄ ማለት ህይወት ኣለፈ ማለት ነዉ። የልብ ትርታ እንደመቆም ኣይነት።
ሉቡን ዖል፣ ሉቡን ቡል ማለት በሉቡ ዋል፣ በሉቡ እደር ማለት ነዉ። አደ አርገዹ ማለት ግንባር ይስጥህ ማለት ነዉ። የመሪነት ምኞት ነዉ።
እንደ እኔ አስተሳሰብ የኣዲስ ኣመት ምንነት ኣንዱ ቁልፍ ሉቡን ዖል፣ ሉቡን ቡል ነዉ። ከሌላ ወቅት ይልቅ የክረምቱ ለህይወት የምያሰጋ ስለሆነ በሰላም ማለፋቸዉን ማክበር እና ለሚቀጥለዉም አመት በሰላም እንዲደርሱ መመኘት ይመስለኛል።
ያ ለሊት የሚገባደደዉ ጎረምሳዎች በየቤቱ እየዞሩ እያወደሱ ገንዘብ በማሰባሰብ ነዉ።
ምጅሪ፥ መስከራም 17 ከሰኣት በኋላ የደመራዉ አመድ ቦታ ቡቁሪ የሚባል የሚጠጣ እና ኬሎ ወይም አደይ አበባን ወስዶ፣ ካልተሳሳትኩ ለኣድባርም በረከት ኣድርገዉ፣ መስቀል ይገበደዳል።
ኣሁን የታሪክ ጥያቄ የሆነብኝ ይህን እኔ እያየሁ ያደኩበትን ባህል የትኛዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወይም ጎሳ ነዉ ይህ ነዉ የእኔ ባህል የሚለዉ? በተለይ ይህ ባህል ቦረና በደንብ ይታወቃል? መሃል ኢትዮጵያ ይህ ነዉ የእኔ ባህል ማለት ይችላል?
መልሱን ኣላዉቅም።
አመርቲን እየየሁ ኣድጌ የጥነት ግብጽ ምስሎች ዉስጥ ሳይ አመርቲ ምን ያህል ጥንታዊ ነዉ ብያለሁ። ስለጎርፍ ማስቸገር ታሪክ ኣንብቤ ሉቡን ዖል፣ ሉቡን ቡል ምን ያህል ጥንታዊ ነዉ ብያለሁ። አከ ሉቡ ኮታን ጃለዸን ኣስታዉሼ ሉቡ እና የእንግሊዘኛዉ ቃል ላቭ ለምን ይመሳሰላሉ ብያለሁ።
በነገራችን ላይ ኦ እና ዖ ልዩነት ሊኖራቸዉ እንደሚችል ለመጀመርያ ግዜ ዖል የሚለዉን ቃል ስጽፍ ነዉ። ከኦል ወይም ወደላይ ለየት ያለ መስሎኝ።
Re: አመርቲ፣ መስቀል፣ የኢትዮጵያ ኣዲስ ኣመት፤ ይህ ባህል የየትኛዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወይም ጎሳ ባህል ነዉ፧ ምን ያህል ጥንታዊ ነዉ?
ከዚህች ትዉስታ መጣጥፍ ስንት ጥናቶች መዉጣት ይችላሉ?
ሕዝቡ ምን ያህል ዘመናትን ባህሉን በነፃነት ስያከብር እንደኖረ ይታወቃል?
መስከረም 1 የግዕዝ አዲስ ዓመት ነዉ። የእኛ አዲስ ዓመት ጃኑዋሪ 1 ነዉ ብላችሁ አስገርማችሁን የነበራችሁ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ጃኑዋሪ 1 አከባቢ ሕዝቡም ሆኑ ኣድባሩ የምያዉቁት ከሙከ ዻባ እስከ ዳመራ ወይም ደመራ እና ምጅሪ የምታዉቁት ኣለ?
ጃኑዋሪ 1 ታህሳስ 22 አከባቢ መሆኑ ነዉ። ታህሳስ 22 አከባቢ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕዝቡም ሆኑ ኣድባሩ የማያዉቁት ከሙከ ዻባ እስከ ዳመራ ወይም ደመራ እና ምጅሪ የምያዉቁት የሌለ ከሆነ ኢትዮጵያዊያን ጃኑዋሪ 1 የእኛ አዲስ ዓመት ነዉ ማለት ቅዠት ወይም ቃጀኡ እንጂ ምንድነዉ?
ከሆነ ከዚህ ያህል ቅዠት ወይም ቃጀኡ ጎትቼ ካወጣሁት ጋር ሰዉ አፉን ይከፍታል?
ለመሆኑ የኦል እና ዖል ልዩነት በግዕዝ እንደዚህ ግልጽ ከሆነ የግዕዝ መሠረት ምን ቢሆን ነዉ?
ሕዝቡ ምን ያህል ዘመናትን ባህሉን በነፃነት ስያከብር እንደኖረ ይታወቃል?
መስከረም 1 የግዕዝ አዲስ ዓመት ነዉ። የእኛ አዲስ ዓመት ጃኑዋሪ 1 ነዉ ብላችሁ አስገርማችሁን የነበራችሁ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ጃኑዋሪ 1 አከባቢ ሕዝቡም ሆኑ ኣድባሩ የምያዉቁት ከሙከ ዻባ እስከ ዳመራ ወይም ደመራ እና ምጅሪ የምታዉቁት ኣለ?
ጃኑዋሪ 1 ታህሳስ 22 አከባቢ መሆኑ ነዉ። ታህሳስ 22 አከባቢ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕዝቡም ሆኑ ኣድባሩ የማያዉቁት ከሙከ ዻባ እስከ ዳመራ ወይም ደመራ እና ምጅሪ የምያዉቁት የሌለ ከሆነ ኢትዮጵያዊያን ጃኑዋሪ 1 የእኛ አዲስ ዓመት ነዉ ማለት ቅዠት ወይም ቃጀኡ እንጂ ምንድነዉ?
ከሆነ ከዚህ ያህል ቅዠት ወይም ቃጀኡ ጎትቼ ካወጣሁት ጋር ሰዉ አፉን ይከፍታል?
ለመሆኑ የኦል እና ዖል ልዩነት በግዕዝ እንደዚህ ግልጽ ከሆነ የግዕዝ መሠረት ምን ቢሆን ነዉ?