-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 13222
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 13222
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Re: ታሪክ ያለዉ ታሪኩን ይናገራል፣ ታሪክ የሌለዉ ስለፈልፍ ይዉላል!
ይህን አፈታሪክ በልጅነቴ ብዙ ግዜ ሰምቻለሁ።
አፈ ታሪኩ የሚለዉ ሊበን የተባለ የቦረና ሰዉ ወልሶ የደረሰዉ ከሶስት ባለቤቶቹ ጋር ነበር።
ወልሶ ከደረሰ በኋላ ሶስቶቹንም ባለቤቶቹን ኣንድ ቀን ማታ ምድጃ ኣዳፍኑ ኣላቸዉ። የኣንዷ ኣደረ፣ የሌሎቹ ሁለቱ እሳቱ ጠፋ።
ምድጃ ያደረላትን ለኣንቺ የሚሆነዉ ቦታ ይህ ነዉ ብሎ እዛ ጎጆ ሰርቶ ከዛም ወልሶ ተወለደ።
ወልሶ ላይ ምድጃ ያላደረላቸዉን ሁለቱን ባለቤቶቹን ይዞ አመያ ደረሰ። እዛም ኣንድ ቀን ሁለታቸዉንም ምድጃ ኣዳፍኑ ኣላቸዉ።
የኣንዷ ኣደረ፣ የሌላዋ ጠፋ። ከዛም ያደረላትን ለኣንቺ የሚሆነዉ ቦታ ይህ ነዉ ብሎ እዛ ጎጆ ሰርቶ ከዛም አመያ ተወለደ።
አመያ ላይ ምድጃ ያላደረላትን ይዞ ኩታዬ ደረሰ እና ኣንድ ቀን ምድጃ ኣዳፍኚ ኣላት። እዛ ኣደረላት። ከዛም ለኣንቺ የሚሆነዉ ቦታ ይህ ነዉ ብሎ እዛ ጎጆ ሰርቶ ከዛም ኩታዬ ተወለደ።
ይህ መቼ እንደሆነ ከአፈ ታሪኩ መስማቴን ኣላስታዉስም። ኣሁን ስገምት የግራኝ መሃመድ ወረራ ዘመን ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ።
ብዙ ዘመናትን ያላስቆጠረ ስለሆን መቼ እንደነበረ ማጥናቱ የሚከብድ ኣይመስለኝም።
የቦረናዉ ሊበን እዛ ሳይደርስ በፊት እዛዉ አከባቢ ይኖሩ የነበሩ ጎሳዎች ኣሉ። ለምሳሌ ምናሲ የሚባል ጎሳ ከሊበን ጎሳ የተወለደ ሳይሆን እዛዉ አከባቢ ቀድሞ ይኖር የነበረ ጎሳ ነዉ። የ ምናሲ ጎሳ ከኣጼ ምናስ ስም የመጣ ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም።
እነ ሀብተግዮርጊስ ዲነግዴ ከሊበን ጎሳ ይሁን ወይም እዛዉ አከባቢ ከነበሩት ጎሳ ወይም ተጋብተዉ የተዛመዱ ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም።
ሌላ ግልጽ ያልሆነልኝ ካልዘነጋሁ እሌኒ ሞጋሳ የእዛዉ አከባቢ ሰዉ መሆኗን ኣንብቤኣለሁ።
ከግራኝ መሃመድ ወረራ በፊት የኖረች ከሆነ የአባቷ ስም እንዴት ሞጋሳ ሆነ?
መኮብሊስ ከኩታዬ በፊት የኖረ ነዉ ወይስ ከኩታዬ ጎሳ የተወለደ ነዉ?
ይህ አፈ ታሪክ ሰፊ ጥናት የምያስፈልገዉ ይመስለኛል። የጎሳዎች የባህል መጣጣም እና መማማር ጨምሮ።
ለጦርነት ቆራጥ የመሆን ባህል በቀላሉ የሚመጣ ኣይዴለም። ዌረረ፣ ወረራ፣ እና ዋር መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ጥንታዊ ቃል ቢሆንም የእነ ባልቻ ቆራጥነት ቦረና ዉስጥ በወቅቱ ታይቶ ነበር?
ይህ ቦረናዎች ቆራጦች ኣይዴሉም ለማለት ኣይዴለም። ሌላ አፈ ታሪክም ትክክል ከሆነ ቦረና የደረሰዉ አባይ ባቦ ቆራጥነትም የሚደነቅ ነዉ።
ስለዚህ ግዜያዊ የኬኛ የእኛ ፖለትካ ንፋስን ጥልቅ ጥናት ይቅደም።