Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አንብር መስቀልየ በድበ መስቀል--> መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ - የግማደ መስቀሉ ስፍራ ወሎ ቤተ-አማራ።

Post by Abere » 27 Sep 2023, 16:32

አንብር መስቀልየ በድበ መስቀል--> መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ - የግማደ መስቀሉ ስፍራ ወሎ ቤተ-አማራ።

አንብር መስቀልየ በድበ መስቀል(መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ)” የሚል ህልም አየ፡፡ ንጉሱም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጲያ አውራጃዎች በሸዋ በደርሄ ማሪያም፣ በመናገሻ ማሪያም፣ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ባለማግኘታቸው በራዕይ እየደጋገመ መስቀሌን በመስቀለኛ ስፍራ አስቀምጥ እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ለ7 ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ በዚያም ተገለፀላቸው መስቀለኛውን ቦታ የሚመራህ አምደ ብርሃን ይመጣል አላቸው፡፡ እሳቸውም ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ የብርሃን አምድ ከፊታቸው መጥቶ ቆመ፡፡
በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል አምባ መርቶ አደረሳቸው፡፡ በዕውነትም ይህች ግሸን የተባለችው አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀለኛ ቦታ ሆና ስላገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው፡፡ በዚያም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሰርተው መስቀሉንና ሌሎች ነዋየ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው በ14ኛው ክፍለ ዘመን የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው፡፡