በ3ኛ ሳምንቱ አክራሚ (እጅግ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ቅዱስ ቀን) አዲስ አመትን እንቀበላለን! ያ ነገ ነው!
ከእንቁጣጣሽ ማግስት ጀምሮ ልጃገረዶች ማታ ማታ ደመራ ጋ እየወጡ ይዘፍናሉ! ጎረምሳ ምጅሩን (ደመራውን) ያሰባል! በቁጥቋጦ ይጠቀጥቃል! ገድራ (ችቦ) በጭራሮ ለያንዳንዱ ሰው ይሰራል ።
መስክረም 14 የጀመረ ለ3 ቀን የልጆች፣ የሴቶች፣ እና ታላቁ መስቀል ! በMeskel - The Festival The Birth of Light ይበላለቃል!
ከትልቁ መስቀል እስከ ጥቅምት አቦ (ጥቅምት 5) ታላቁን ባለ ብዙ ጨዋታዎቹ የአዳብና (አደይ አብና) በወጣቶች ይደሰታል
ከህዳር ሚካኤል ጀምሮ እረኛ ከብት እያበላ ገና መጫወት ይጀምራል
ትንሽ ቆይቶ ወጣቱ ማታ ማታ ከቤት ቤት እንዞሪቴ (ሆያ ሆዬ) በመዞር ገንዘብና እህል ይሰበስባል (የዚህ እንዞሪቴ ቪዲዮ ከስር ተመልከት)
ይህ እስከ ገና ሄዶ የገና እለት የገና አገርና አገር ግጥሚያ ይሆናል
የሴቶች ሆያ ሆዬ ኢምር ኢመርም እንዲሁ
ይህ ባጭሩ ነው !