Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by TGAA » 31 Aug 2023, 23:05

በአይዲያል አለም ውስጥ ብንኖር አሁን በወያኔ የተተከለውና በኦሌፍ እየተኦተኮተ የመጣው የብሄር የመንግስት አወቃቀር ባይኖር እጅግ የሚመረጥና ከብዙ ችግር የሚያወጣን ይሆን ነበር ፤ አሁን ግን እንደምትሰማው የወያኔ ፣ የኦነግ ደጋፊዎች እንዲሁም የነርሱን ስነ ልቦና የወረሱ በሞላ የኤትኒክ ፊደራሊስም ወይም ሞት እያሉ ነው ፤ ስለዚህ ሁለተኛ ያለው ምርጫ የኤትኒክ ፊዴሬሽኑ በአካባቢው ባለው የህዝብ ብዛት እንዲወስን ቢደረግ ወይም ትግሉም በትክክለኝ ሴንሰስ ላይ ተመስርቶ የኤትኒክ ፊዴሬሽኑ ቢዋቀር በከተማውም በገጠሩን ፤ በዚያ መሰረት አካባቢውን ሰው እራሱን ቢያስተዳድር ፤ የኢትኒክ ቁማርተኞች በዚህ አይነቱ መዋቅር ምንም ፍላጎት የላቸውም ፤ 20 ሚሊዮን በኦሮሚያ የሚኖሩ የተለያዩ ኢትዮጵያዊያን የህብረተሰብ ክፍሎች ተመጣጣኝ ውክልና ቢያገኙ ሁሉም እራሱን መከላከል የሚችልበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው ፤ ስለዚህ ይህን ሀሳብ የአማራ ህዝብ ቢጫወት ፤ ውጊያውንም በዚያ መንገድ አጠናክሮ ቢሄድ ያዋጣዋል ወይስ ምን አይነት ችግሮች ይታዩሀል ፤if you can't fight them join them. do you see any good in it .

Horus
Senior Member+
Posts: 42684
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by Horus » 01 Sep 2023, 00:10

TGAA,
ቪዲዮውን አላየሁትም፣ አንተ ከጻፍከው ከተነሳን ሱሊማን ሁለት ቁልፍ ነገሮችን ነው ያነሳው ፤ አንደኛ፣ ፋኖ ምን አይነት አገር አቀፍ ፕሮግራም ቢያረቅቅ ነው የ88 ብሄሮች ድጋፍ ሊያገ የሚችለው የሚል ነው ። ማለትም ለምንድን ነው ሌሎች ብሄሮች የአማራን ትግል መደገፍ ያለባቸው?

ሁለተኛ ፣ ፋኖ ከኦረሙማ ወይም ወያኔ የተለየ ምን አይነት አዲስ የኢትዮጵያ ፕላን ወይም ፕሮግራም ወይም የለውጥ አይነት አለው? ፋኖ ከብልጽግና ምን ይለየዋል የሚለው ነው ።

በአንድ ቃል ይህ በብሩህ አይምሮው የታወቀው ወጣት የመጨረሻውን ግዙፍ የፋኖ ችግር (ፋኖ መፍታት ያለበት) ችግር አንስቷል ። ይህም ማለት አማራ ለመላ ኢትዮጵያ ስርዓታዊ ለውጥ ያለው መፍትሄ ወይም ፕሮግራም ምንድም ነው? ምን መሆን አለበት የሚለው ነው።

በግርድፉ የተነሳው የጎሳ ፌዴሬሽንን ከርክሞ መቀጠል የሚለው በጣም መብራራት አለበት ። የትንተና ጥያቄ?

ለምንድን ነው የጎሳ ፌዴሬሽን የማይሰራ፣ ኢፍትሃዊ፣ ዝርክርክ፣ ሙሰኛና አውዳሚ የሆነው? ጎሳ የሚባለ ጽንሰ ሃሳብ ዘመናዊ ፖለቲካ ማደራጃ ዘዴ ነው ወይ? ይህ ጥያቄ በጥልቀት መመለስ አለበት ።

አንዱና ዋነኛው ችግር ጎሳና ቋንቋ የፖለቲካ አስተዳደር (የፖለቲካ ስልጣን አከፋፈልና ስርጭ) መስረት ስለ ሆነ ነው ። ፖለቲካን የሚዘውሩት (ሚነዱት) ጥቅሞች ስልጣን፣ ሃብት (መሬት ዋናው ነው)፣ ክብር (ማንነትና) ዝና (መታወቅ) ናቸው ። ጎሳ የፖለቲካ ማደራጃ በልሆነበት አገር እነዚህ 4 ጥቅሞች በህገ መንግስት ይፈታሉ፣ ይበየናሉ ። ህግ አንድ ሰው እንዴት ስልጣን እንደ ሚይዝ፣ ሃብት እንዴት እንደ ሚያፈራ፣ ማነንቱ እንዴት እንደ ሚከበርና ዝናና እውቅና (ሜሪት ሲስተም ) ያበጃል

አሁን ጥያቄው አንድ ጎሳ አብሮ አይኑር፣ ባህል አይኑረው፣ ቋንቋውን አያበልጽግ፣ ወዘተ አይደለም ። ያ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ስምምነት ተደሷል ።

መከልከና መኖር የሌለበት አንድ ጎሳ አብሮ ባንድ መሬት ኖረም ተበታትኖ ኖረ የሚኖርበት መሬት የዚያ ጎሳ የግላ ንብረት ስለሆነ ባለሙሉ መብት ያ ጎሳ ስለሆነ ሌሎች ጎሳዎች በዚያ መሬት ላይ እኩል ባለቤትነት የላቸውም የሚለው የኦሮሙማ ተረት መሻር አለበት ። አንድም ጎሳ ያንን መሬት የፈጠረ ስላልሆነ ። ስለዚህ ይህን የመሬት ጥያቄ ከፊውዳሊዝም የገባርነት ጥያቄ የባሰ ግፈኛ ስለሆነ ያ ቁጥር የፋኖ ፕሮግራም ችግር ይሆናል ማለት ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፖለቲካ በጎሳ ክምችንትና ቀመር ከተዋቀረ አንድ ዜጋ እንዴት ነው መንግስት ውስጥ የሚወከለው? የአንድ ዜጋ ፖለቲካዊና ህጋዊ መብቶች ምንጭ ምንድን ናቸው? ጎሳዊ መሆኑ ነው ወይስ ሰባዊ መሆኑ? ወዘተ?

በእኔ ግምት ኢትዮጵያ ለግዜው ምናልባት 2ኦና 30 አመት ሁለት ፓርላማ ያሰልጋታል ። አንድ የዜጋዎች ፖለቲካል ኮሚቲ የሚደራጁበት ዘመናዊ ኮንግሬስ እና ሁለተኛ የታችኛው ፓርላማ የጎሳዎች ካልቸር፣ ባህል፣ ቋንቋና ሌሎች አሁን ስር የሰደዱ የጎሳዎች ሚዛን የሚጠብቅ ኮንግሬስ ያስፈልጋታል

ማንኛውም የጎሳ ፌዴሬሽን በፍጹም የዜጋዎች ሙሉ መብት የሚጠብቅ ስርዓት አይሆንም !!!

ፋኖ የተወለደው እና ሂስቶሪካል አስፈላጊነቱ የተከሰተው አንድ አማራ የሆነ ዜጋ ሰብአዊ መብቱ ማለትም ከላይ የጠቀስኳቸው 4 ጥቅሞች የሚያስከብርለት (ፖለቲካ ስልጣኑ፣ ሃብቱ፣ ማነቱና ዝናው/ስሙ።ታሪኩን) መንግስትና ህግ ስለሌለ ነው ። ያን የሚመስል መንግስት በጎሳ ፌዴሬሽን በፍጹም አይኖርም ።

ስለዚህ የጎሳ ኃይሎች አልፈርስማ ካሉ ለነሱ ጉዳይ አንድ ምክር ቤት ተቋቁሞ ለ120 የኢትዮጵያ ዜጋዎች ዘመናዊ በአንድ ዜጋ ድምጽ የቆመ ታላቁ ፓርላማ መመስረት የግድ የግድ ነው !!

ስለረዘመ ይቅርታ !

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by TGAA » 01 Sep 2023, 00:45

አጥጋቢ መልስ ነው ፤ አመሰግናለሁ !

Horus
Senior Member+
Posts: 42684
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by Horus » 01 Sep 2023, 02:01

TGAA wrote:
01 Sep 2023, 00:45
አጥጋቢ መልስ ነው ፤ አመሰግናለሁ !
TGAA,
የልጁን ውይይት ሰማሁት!
ሱሊማን ሲጀምር በጣም ጠንካራ ትክክለኛ አቋም ይዞ ተነሳና ሲዘጋ ሃሳቡ እየደከመ መጣ ። ለምን በል?

እጅግ ጠንካራ ክርክሩ፤
አሁን ባለው የጎሳ ፌዴሬሽን ውስጥ አማራ ትክክለኛ ወክልና ያስፈልገዋል፣ ወልቃይት፣ ራያ፣ ደራ፣ አዲስ አበባ፣ መተከል የአማራ አገሮች ናቸው የሚለው ትክክል ነው ። የአዲስ አበባ ማጆሪቲ አማራ እንደ ሆነ እኔ በግሌ ስለማውቅ ።

ሲቀጥል አማራ ባለበት በየትኛውም የኢትዮጵያ መሬት በትክክል ተቆጥሮ በቁጥሩ ልክ መወከል አለበት፣ ፋኖም ሆነ ፋኖ የሚያቆመው ያማራ መንግስት አማሮች ባሉበት ማንኛውም የኢትዮጵያ ክልል/ ምድር መብታቸውን ማስከበር አለበት የሚለው እጅግ ትክክል ነው ። የነዚህን አማሮች መብት የሚያስከብር መንግስት ስለሌለ ፣ አዲስ አበባ ያለው የኦሮሞ መንግስት ይህን ማድረግ ስለማይችል ።

ሌላው የልጁ ትክክለኛ ግምት የጎሳ ስሜትና ፍላጎት በአጭር ግዜ አይለወጥም ያለው ትክክል ነው ። ለዚህ ነው እኔ ሁለተኛ የጎሳ ፓርላማ ያስፈልገናል ያልኩት ።

የሱሊማን ህሳቤ ከራሱ ጋር የሚጋጨው አማራ ከፈለገ ራሱን የቻለ አገር መሆን አለበት፣ ሊሆን ይችላል፣ ይሆናል የሚለው ነው።

ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ ፣ ማለትም በሌላ ራሱን የቻለ ካሻው አገር ሊሆን የሚችል ሉአላዊ ክልል ውስጥ ትግሬ ሆና አፋር፣ ኦሮሞ ሆነ ሱማሌ ደቡብ ሆነ ጋምቤላ ውስጥ ያሉ አማሮች መብት ያላቸውና መብታቸው መጠበቅ አለበት የምንለው ከማንኛውም ጎሳ በላይ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባል ሉአላዊ አገር ስላለች ብቻ ነው ።

ኢትዮጵያን አፍርሰህ ያንተን ክልል ሉአልዊ ካድረክ በኋላ ሌላ ሏላዊ ክልል ወይም አገር ውስጥ የሚኖሩ አማሮች መብት ከውጭ መጥተህ ልታስከብር አትችልም። ካማራ አገር ውጭ የሚኖሩ አማሮች በሚኖሩበት ክልል ሕግ ስር ስለሚኖሩ ። As Ferenis say, 'you can not eat your cake and have it too.

ኤርትራ ስትገነጠል ኤርትራዊያን የውጭ ዜጋ እንደ ሆኑት ማለት ነው ። ዛሬ ኢሳይሳ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራዎችን መብት በጉልበት ማስከበር አይችልም። ኢትዮጵያን ስላፈረሰ!

ሱሊማን ይህን ማወቅ አለበት ! የጎሳ ብሄረተኝነት የተወሰነ ጥቅም አለው! እስከ መጨረሻ ከገፋሃው መልሶ እራስክ ነው እስር ቤት የሚቀፈድድህ !

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by TGAA » 02 Sep 2023, 00:30

Horus wrote:
01 Sep 2023, 02:01

ሆረስ ሉኡላዊ የሆነ የአማራም ሆነ የሌላ ማህረሰብ ሀገር ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም ፤ ቢሞከርም ፕሪፒችዋል ዋር ብቻ ነው ሊኖር የሚችለው ፣፤ ነገር ግን የወያኔ አሁን ደግሞ ዎሮሙማ የጎሳ መንግስቶች ፤ አወቃቀር እውነተኛ የጎሳ ውክልና እንዲኖር ሳይሆን፤አወቃቀሩ የሚጀምረው መሬቱ ከጎሳ ጋር በመስፋት ማንም ይኖርበት ማን የቦታ ባሌቤትነት ፍትሀዊ ባልሆነ ሆኔታ በማረጋገጥ ነው፤ የኛ ነው ካሉ በኋላ ማንም በመሬቱ ላይ ነዋሪ የሆነው ሰው መብት የለሽ ሁለተኛ ዜጋ በማድረግ ነው ፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ዜጋ በሚኖርበት ሙሉ መብት ያለው ፤ በፓርላማ ውክልና ያለው ፤ በሚፍለገው ቋንቋ የሚናገር ፤በሚመቸው ቋንቋ የሚጽፍ ፤ ከሌላው ህብረተሰብ ጋር በሚያተርፈው መንገድ የሚነግድ እንዲሆን ማድረግ የጎሰኛን ዘራፊ ስርአት ማድከም ይቻላል፤ ያ ደግሞ የዜግነት ፖለቲካን የበለጠ ተወዳጅ እያደረገ ያመጣዋል ፡ ስለዚህ የዚህ የጎሳ ፖለቲካ ኢንሴንቲቨ የሆነውን አግባብ የለሌው የፖለቲካ ጉልበትና የዘረፋ ኢኮኖሚ ከስሩ ማድረቅ ተገቢ ነው ፤ እዚህ ላይ ነው የሱሌማን ሀሳብ ጥንካሬው ፤ በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተማዎች በብዛት በሚገኝበት እራሱን እንዲያስተዳድር ተወካይ በፓርላማ እንዲኖረው የሚደረገው ትግል ቅድምያ እንዲኖረው የሚያስፈልገው ፤ 35 በላይ የሆነውን የጎሳ ፖለቲካ ዋርካ በራሱ ሾክ የምታደማው፡ ለምን የዜጋ ፖለቲካ ምንም እንኳን የሰለጠነ ፤ ምርጥ የምንፈልገው ስርአት ቢሆንም በአሁኑ ሰአት ደክሟል ( እነብርሀኑም ከኦሮሙማ ጋር በመታከክ ትልቅ ጉዳት አድርሰውበታል ) ስለዚህ ትክክለኛና ማንም ሰው በግልጽ በሚገባው ፤ ትግሉም በአጭሩ ብዙ ድጋፍ የሚያገኝበትን መንገድ መዘየድ የግድ ይላል ፤ ስለዚህ ሁሉም በሚኖርበት ቀዬ የራሱ ተወካይ እንዲኖረው ማድረጉ ፤ ግልጽ ፤ፍትሀዊ ፤ ነው ፤ አንተ ያቀረብከው ሀሳብ በፓርላመንት ውስጥ የዜገነትና በጎሳ የተካፈለ ፓርላም መኖር ምንም እንኳን ሀሳቡ ቢስብም በተጨባጭ ማድረግ ይከብዳል ፤ ይህ አደረጃጀት ውጤት እንዲኖረው ከሁለት አንዱ ደካማ መሆን አለበት ፤ የዜግነት ፖለቲካ በጠነከረበት የጎሳ ፖለቲካ ደካማ ነው ፤ በተገላባጭ ደግሞ የጎስ ፖለቲካ በጠነከረበት የዜግነት ፖለቲካ ደካማ ነው የሚሆነው _ሚቹዋሊ ኤክስክሉሲቭ ኮንሴፖቶች ስለሆኑ፤

Horus
Senior Member+
Posts: 42684
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆሩስ አባ መላ ይህንን የሱሌማን አብደላ ትንተና ስምተህ ሀሳብህን ብትቸረን ?

Post by Horus » 02 Sep 2023, 01:47

TGAA,
ይህኮ የቆየ ክርክር ነው ። የጎሳ ብሄረተኘት ለአፋርም፤ ከአማራም ለኦሮሞም እኩል ነው፣ አንድ ነው። ፍትሃዊ ሲስተም ሊፈጥር አይችልም ። ጎሳዎች ሁሉ የተለያየ ብዛት ስላላችው። እያንዳንዱ ጎሳ ሰዉ ቁጥር ስልጣን፣ ሃብትና ማንነት ማግኘት አለበት የሌውማ ሁሉም ጎሳ የሚጠይቀው ነገር በጎሳ ፌዴሬሽን ውስጥ ።

ከዚያስ?
ዜጋና ጎሳ ሲስተሞች ተጻራሪ የሆኑት ጎሳ የፖለቲካ ሲሰም ስለተደረገ ነው። ያ ተደርጎ አልሰራም። በፍጹም አይሰራም ። በዚያ መልክ ኢትዮጵያ አገር ሆና አትቀጥልም ። አማራ ምራጫ አለው ልክ እንደ ኦሮርሞና ትግሬ ኢትዮጵያን አፍርሶ የራሱ አገር መሆን ። ይህ ምንም ንቅንቅ የማይል ሳይንስ ነው። የጎሳ ፌዴረኢሽን በለው ኮንፌዴሬሽን እንደ ሲስተም ከቀጠለ ትግሬ አገር ይሆናል፣ አፋር አገር ይሆናል፣ አማራ አገር ይሆናል ፤ ኦሮሞ አገር ይሆናል ፣ ሱማሌ አገር ይሆናል ። ደቡቦች የሆነ አይነት አገር ይሆናሉ ። ይህን መካድ አይቻል፣ ።

የሱሊማን መደምደሚያ ያ ነው ። አስፈላጊ ከሆነ አማራ አገር መሆን አለበት ነው ያለው ። ያ ደሞ የማራ ልሂቃን አቋም ከሆነ ኢትዮጵያጵያን እንደ አገር ማስቀጠል የሚሉትን ሃሳብ መተው አለባቸው ። ልብ አድርግ የጎሳ ብሄረተኘት ለኦነግ ስህተት ሆኖ ለፋኖ ትክክል ሊሆን አይችልም ፣ከኢትዮጵያ አገርነት አንጻር !!

ለዚህ መፍትሄው የብሄር ጥያቄን (ዛሬ ላይ የአማራ ብሄር ጭቆና ጥያቄን ጨምሮ) በታቸኛው ፓርላማ ከዜጋዎች ፓርላማ ያነሰ ስልጣን ያለው አካይነት ይፈታል ። ይህ ፓርላማ አይደለም ኢትዮጵያን አገር የሚያደርጋት፣ የዜጋዎቹ ፓርላማ ነው ። ኢትዮጵያን አንድ አገር የሚያደርጋት ። የጎሳዎቹ መንግስት ለግዜው እንዲኖር ብንገደድም እንደ ሲስተም ከቀጠሉ የሆነ ኢትዮጵያ ቢያንስ በ10 አገሮች መበተኗ የግድ የግድ ነው።

ስለዚህ የጎሳ ክልሎች ሏአላዊ አይሆኑም የሚለው መሰረት የለውም ። ኤርትራ አገር ነች ። ትግሬን አገር ከመሆን የያዘው የኢትዮጵጵያ መኖር ነው ። ስለዚህ እነዚህ ክልሎች በስምምነት ሁሉም አግር መሆን ከተስማሙ በስምምነት ኢትዮጵያን እንዳገር አፍርሰው የራሳቸውን አገር ከማቆም ማንም አይከለክላቸውም ። እነዚህ ተገንጣይ ጎሳዎች ዛሬ ላይ ያለም ተቀባይነት የማያገኙት ታሪካዊ የሆነች አገር ኢትዮጵያ የምትባል ስላለች ነው ።

ስለዚህ ምን እንደ ምንመኝ እግጅ እግጅ በጥንቃቄ መምረጥ አለብን ።

ስለዚህ የአማራ ብሄር ጭቆና ጥያቄ ምን እንደ ሆነ ፣ይህ ጭቆና መልስ የሚያገኘውና የሚያበቃው ምን ምን ነገሮች ሲሟል እንደ ሆነ ግልጽ መሆን አለብህ ። ኦሮኖችን ውሰድ የኦሮሞ ብሄር ጭቆና ጥያቄ ከተመለሰ ዘመናት አልፈዋል ። ግ ን አሁንም አለ። አሁን ጥያቄው የእኩልነት ሳይሆን የበላይነት ነው ። ይህ የጎሳ ብሄረተኘት ሁሉ መድረሻ ምኞት ነው ። ትግሬ በቁጥር ከጉራጌ አይበልጡም ። እስከ ዛሬም የሚታገሉት ለበላይነት ነው።

እመነኝ የጎሳ ብሄራዊ ጥያቄ ከወሰኑ ካለፈ ኢትዮጵያ ፈርሳ ለዘላለም የሚዋጉ 10 አገሮች እንሆናለን ።

Post Reply