Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 12:45

በተለምዶ ኢመደበኛ፣ ሽምቅ፣ ህዝባዊ ዉጊያ ተብሎ ዛሬ ላይ ወዳጅም ጠላትም የሚያነበው የጦርነት መከወኛ ታክቲክ፣ ስልት፣ ብልሃት ወይም ዘዴ ነው።

ነገር ግ ን አንድ እስትራተጂ፣ እስትራታጀም፣ ወይም ታክቲክ ለወዳጅም ለጠላም ከታወቀ አንዱ ላንዱ ዝግጅት በማድረግ ስለሚያፈርሰው ትልቁ የጦር መሪነት ብቃት መለኪያው የጠላትን ግምት መሻርና ጠላትን እውቀት አልባ ማድረግ ነው ።

ስለሆነም ጠላት ከገዘፈ ከፋፍለው፣ ካፈገፈገ አሳድደው፣ ከዘመተብህ አፈግፍግ ወዘተ የሚሉት ክላሲካል የህዝባዊ ጦርነት ስልቶች ሁሉም ስለሚያቃቸው እነሱን መሸምደድ ብቻ ወደ ድል አይወስድም ።

ስለሆነም የአንድ ሸማቂ ዉጊያ ስልት ልክ እንደ ፋኖ ቩካ መሆን አለበት ። ቩካ የሚባለው ኮድ እሲህ አላብራራም፣ ይዘቱ ግን የሚከተለው ነው ።

ቩካ ስልት እርግጠኛ አይደለም ። ጠላት ይህ ነው ብሎ ሊያውቀው አይችልም። የቩካ ስልት ምን እንደ ሆነ የሚወስነው የሸማቂው ታክቲከኛ ብቻ ነው ። ሌላው ቀርቶ የሸማቂው ወታደሮች እንኳን አያውቁትም ። ዉጊያ አውድ ላይ ሲተገብሩት ብቻ ነው ምን እንደ ሆነ የሚያውቁት ።

ቩካ ስልት ተለዋዋጭ፣ እጅግ ተለዋዋጭ ነው ። ጠላት ለዚህ ስልት መዘጋጀት አይችልም ። ማለትም ሸማቂው ጦር የሚቀጥለው ግጥሚያ እንዴት እንደ ሚያደርገው ጠላት ማወቂያ ዘዴ የለውም ። የሽምቅ ዉጊያ ሕዝባዊ ስለሆነ የዚህ ጦር ሰላዮች መላ ሕዝቡ ስለሆኑ እጅግ በጣም አሁናዊ መረጃ የሚያገኘው የሸማቂው ታክቲከኛ ነው ። ስለዚህ የተለዋዋጭ ስልት ንጉስ የሸማቂው መሪ ነው እንጂ የጠላት ጦር ጄኔራል አይደለም።

ቩካ ስልት ውስብስብ ነው ። በተላይ እንደ ፋኖ ባለ በመላ አገር የተዘራና እስከ ታች ድረስ ራሱን ችሎ ፣በራስ እዝነትና በራስ ቻይነት የሚንቀሳቀስ ግዙፍ ብትን ጦር እጅግ ውስብስብ ወይም ኮምፕሌክስ ስለሆነ ለአንድ የጠላት ጄኔራል በጣም አስቸጋሪ ክስተት ነው። የጠላት ጄኔራል የእሱን ወታደሮች የሚያዘጋጀው የጠላትን ሁኔታ በውል ሲያውቅ ነው ። ኮምፕሌክስ የሽምቅ ኃይል ለዚህ አይመችም፣ ጠላት እንዳያውቀው ተፐውዞ የተራጀ ስለሆነ!

በመጨረሻም ቩካ ስልት አሻሚ ነው ። ማለትም አንድ ሸማቂ ጦር ምን እንደ ሚፈልግ፣ ምን እንደ ሚያስብ፣ ማን እንደ ሆነ ወዴት እንደ ሚሄድ ለጠላት ግልጽ እንዳሆን የተቀረጸና የተደራጀ ስለሆነ የጠላት አይምሮ በአሻሚ ግምቶች እንዲጠመድ ማድረግ ነው አንዱ የቩካ ስልት ።

እነዚህ ዋና ዋናዎቹ የፋኖ ስልቶች ናቸው! ለዚህም ነው ግዙፉን የኦሮሙማ ሰራዊት እዚም እዛም በትኖ እንደ ፈቀደው የሚያሽከረክረው! ከዚህ ቀደም እንዳልኩት ሙሉ ኢኒሺዬቲቭ በፋኖ እጅ ነው ። ይህም ማለት ፋኖ የትም ቦታ ተገዶ አይዋጋም ። ሁሉም ቦታ ሲፈግና በፈለገው መንገድ ነው የሚዋጋው !

ይህ ማለት ደሞ በዉጊያ ሳይንስ የፋኖ ጦር አዛዥ (ታክቲከኛ) ፋኖን ብቻ ሳይሆን የአቢይ ሰራዊትም ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያዘው ይህው የፋኖ ታክቲከኛ ነው ። ይህ ነው ሱፒሪየር የጦር ችሎታ የሚባለው! የጠላትን ጦር ምን ማድረግ እንዳለበት ማስገደድ !!! ይህን መሰሉ ችሎታ ፈረንጆች ብሪሊየንስ ይሉታል!
Last edited by Horus on 27 Aug 2023, 14:49, edited 7 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 13:08


Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Wedi » 27 Aug 2023, 13:20

Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 13:34


Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 14:23


Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 18:16

Are we witnessing the Tet Offensive of 1968?
በንቁጣጣሽ ዋዜማ የፋኖ ማጥቃት ቴትን አስታወሰኝ !!

የአማራ ጦርነት ፣ ያቢይ አህመድ ኳግማየር (መቀመቅ)




Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 27 Aug 2023, 18:35


Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 28 Aug 2023, 15:31

በዚህ ሰው አስተታየት 6ቱ የፋኖ ጥንካሬዎች

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 29 Aug 2023, 17:14

በእኔ ግምት የፋኖ ፈረስ ፊቱን ወደ ደቡብና ምስራቅ እያዞረ ይመስለኛል ። ሁለቱ መስመሮች አንዱ ከሰሜን ሸዋ ተነስቶ በምስራቅ ሸዋ አድርጎ ወደ ድሬና ሃረር የሚዘልቀው ይሆናል ። በዚህ ግምባር ፋኖ ሰፊ ድጋፍና የፋኖ ምንጭ እንዳለው ግልጽ ነው! አደራጅ ብቻ ነው የሚፈልገው ።

ሁለተኛው ግምባር ከደቡብ ጎጃም ተነስቶ መተከልና ግቤ በረሃን ይዞ ታላቁ ኦሞ ወንዝን ተገን አድርጎ ጋሞና ጋምቤላ የሚወርደው ቲያትር ነው ። እዚያም አደራጅ እንጂ ፋኖ የተዋጊ ወጣት እጥረት የለበትም ።

ያቢይ ኦሮሞሙና ኦላ ሳንድዊች የሚሆኑት ያኔ ነው!

ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላታል!!

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10921
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by ethiopianunity » 29 Aug 2023, 22:08

Horus,

As long as the real Fano, not those of Weyanes who hijacked the name Fano must resist any fake support that is not genuine, for example, I hear there are troops coming in from israel, really does Israel is more close to Egypt than Ethiopia, is colony project not true friendship, they want Nile so they want to destroy Amara,and want to keep the people they programmed, "Bete Israel" is meant to destroy Ethiopia and its people is project of Egypt and Israel. Saudi must release our 1 million Ethiopians. By dividing us, we are destroying eachother so that we can not stand together and be the voice. Go to Ethiopian communities in Diaspora, they do absolutely nothing for those in need, they are looting from the host government and diaspora and they don't do anything. The house divided will not stand. I am getting convinced the current government is puppet of Liberation Fronts especially Shabia and foreigners.

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 29 Aug 2023, 22:20

ፋኖ ቩካ ነው! አለ ሲሉት የለም! የለም ሲሉት አለ! ቩካ ማለት ይህ ነው! ቩካ እንደ ንፋስ መንፈስ እንደ ንፋስ መለዋእጥ! ቩካ ማለት እርግጠኛ ሲሉት አጠራጣሪ፣ ሲጠራጠሩ ማስረገጥ! ቩካ ማለት ማሰሳሰብ ቩካ ማለት ጠላትን በግምት ወጥሮ መያዝ በቃ ቩካ ማለት ። ጠላት ሲመጣ መጥፋት፣ ጠላት ሲሄድ ማሳደድ፣ ቩካ ማለት የጠላትን መዋጋት ፍላጎት በማምከን ማሸነፍ ! ያ ነው ቩካ ! ቩካ በህዝባዊ ማዕበል ሚሊዮን ልጅገረዶችን ጂንጂን እያጠጡ ማስፈጀት አይደለም ! ሸማቂ ማለት ፋኖ ነው !

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 31 Aug 2023, 01:28

ፋኖ ቩካ1 ከተማ ያዘ ሲሉት መልቀቅ ! ይከላከላ ሲሉት ማጥቃት! ያጠቃል ሲሉት ማፈግፈግ! ዉጊያ ዶግማ አይደለም ! ቋሚ ቀኖናም የለውም! ዉጊያ አርት ነው! ትወና ነው! የጠላ ጦር እስከ ሚሰለቸው ማመላለስ ነው የዉጊያ አርት !

ብራኑ ጁላ አሸነፍኩ ብሎ መግለጫ ሲያውጅ ብብቱ ስር ተተኩስበታለህ! ተስፋ ታስቆርጠዋለህ! ያቺ አመቺ ማንም የምያውቃት ወቅት ከተፍ እስከ ምትል!

በችኮላ የሚካሄድ ሕዝባዊም ሆነ ሽምቅ ጦርነት የለም!

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 31 Aug 2023, 14:20

አረቦችና የወደቀው አቢይ አህመድ!

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 16 Sep 2023, 13:38

Abere,
ስለ ተማከለና ያልተማከለ የፋኖ አደረጃጀት ያልከውን እንዲህ ብዬው ነበርኮ ፣ የፋኖ ስራ ረቂቅ ነው። ገና ድሮ ነው ስልታቸውን የወደድኩት!!!
viewtopic.php?f=2&t=330013

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 17 Sep 2023, 17:15



Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 18 Sep 2023, 21:53

የፋኖ ዉጊያ ስልት እንደ አርትና የሲምፎኒ ኦርኬስትራ ማለት ነው! በጀግንነትም በብልሃትም እጅግ እጅግ የተዋጣለት ታሪካዊ ክስተት ነው ! አሁን በግዙፉ የሸክላ ዝሆን ኦሮሚያ ምን እንደ ሚሆን እንገምት!

ኦሮሞያ በቆዳ ስፋት ሰፊ ነው ! በሰው ቁጥር ሰፊ ነው ! ያ ያ አው ግዙፍ ነው !

ግን አንድ ሳይንስ አትርሱ አንድ እጅግ ረጅምና ደንዳና ሰንሰለት ያለው ጥንካሪ በክብደቱና ርዝመት ልክ ሳይሆን አንዷ ደካማ ቀለበት በአላት ጥንካሬ ልክ ነው ። ደሞም ኦሮሞና ኦሮሚያ ብዙ ብዙ ደካማ ቀለበቶች፣ ብዙ ዊከስት ሊንኮች አላቸው ። ፋኖ እነዚያ ስስ ብልቶችን ነው እየለየ የሚበጥሰው !

ብዙ ኮተት የተሸከመ መንገደኛ ርቆ አይሄድም ይባላል! የኦሮሚያ ግዝፈት አንዱ ተሸናፊ ከሚያደርጉት ፋክተሮች አንዱ ነው !

እንኳን ለዚህ አይነት ውይይት አበቃን !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 24 Sep 2023, 19:39

የአቢይ አህመድ የግል ዘበኛ የሆነው የዲክታተሩ ፕሪቶሪያን አርሚ ጥበበኛው ፋኖ እንደ መፔት አሻንጉሊት ተቀመጥ ሲለው ይቅመጣል፣ ተነስ ሲለው ይነሳል ፣ ሽሽ ሲለው ይሸሻል፣ ተዋጋ ሲለው ይዋጋል ። ፋኖ የራሱን ዉጊያ መች፣ የትና እንዴት እንደ ሚዋጋ መወሰን ብቻ ሳይሆን ብርሃኑ ጁላን እንደ ዥዋዥዌ እያሽከረከረው ነው ! ያ ቩካ የሚባለው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 25 Sep 2023, 15:22

አሁናዊ የአማራ ጦርነት ስሌት ምን ይመስላል?
መስከረም 15 ቀን 2016 ዓም

አሁናዊ የፋኖ አላማ ምንድን ነው? የፋኖ ግዜያዊ ግብ ከተሞችን በመቆጣጠር መንግስትና አስተዳዳሪ መሆን አይደለም። የሲቪል መንግስትና አስተዳደር በየከተማው ቢያቋቁም ለነዚያ ሁሉ ፖሊስና ደህንነት በማዘጋጀት የሽምቅ ተዋጊም መንግስትም ሊሆን አይችልም ። ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ እሚያስችለው የሲቪል አደረጃጀት የለውም ። ስለሆነም እስከ ተወሰነ ድሮ የነበረው የአስተዳደር መዋቅር አገልግሎት በመስጠት እንዲቀጥል ይፈልጋል። በማንኛውም ግዜ መንግስት ከሌለ የሚከተለው አናርኪና ስርዓትአልበኝነት ስለሆነ።

በመሆኑም የፋኖ ግዜያዊ አላማ የብልጽግናን የበላይ አለቆችን የፖሊስና ሚሊሺያ አለቆችን በማስወገድ የአቢይ አህመድ አስተዳደር በአማራ ምድር ሽባ ማድረግ ነው ። በድሮ አዮታዊ ቋንቋ ይህ የትግሉ ኔጋቲቭ ፕሮግራም ይባላል፤ ያለው ስርዓት ማፈራረስ ይባላል ። የፋኖ መንግስት ማቋቋም የትግሉ ፖዘቲቭ ፕሮግራም ይባላል።

በመላ አማራ ተዘርቶ ያለው የፋኖ ኃይል በአንድ እዝ የሚመራ ወጥ ሰራዊት ይሁን ወይ አይሁን የሚለው በቀላሉ የሚታይ ጥያቄ አይደለም ። አሁን ላይ አንዱ ትልቁ የፋኖ አድቫንቴጅ ያልተማከለ፣ ራስ እዝ፣ እንደ አካባቢው ሁኔት በነፋስ ፍጥነት የሚንቀሳቀስ አደረጃጀት መሆኑ ነው ። ያልተማከለ ሰራዊትን ማኔጅ ማድረግ እጅግ ይቀላል ። ስለሆነም ምን ምን አይነት ነገሮች ሲሟሉ ነው አንድ እዝ ያለው ወጥ ሰራዊት መሆን የበለጠ አድቫንቴጅ የሚኖረው የሚለው ቁልፍ ጥያቄ የሚያውቁት ራሳቸው የፋኖ ታክቲከኞች ናቸው ።

የአቢይ አህመድ አሁናዊ አላማ ምንድን ነው? የብርሃኑ ጁላ ስሌት ፋኖን በየከተማው እና ባላገሩ እያሳደደ ማጥፋት (የሽምቅ ተዋጊን በዚያ ዘዴ ማጥፋት ስለማይቻል) አይደለም። በያንዳንዱ የአማራ ከተሞች ውስጥም የብልጽ ግና አስተዳደር ለመመለስ ወይም ለማስፈን እና ለመከላከል አይደለም። ፋኖ እነዚህን አስተዳደሮች በማንኛውም ግዜ ሊያፈርሳቸው ስለሚችልና እንዲሁ ፋኖ ከተሞችን ይዞ የማስተዳደር አሁናዊ አላማ እንደ ሌለው ስለሚታወቅ ።

የአቢይ አህመድ አሁናዊ ዋና ስጋት ፋኖ ማዕከላዊ መንግስትን ለመገዳደር የሚያስችለው ወታደራዊ አደረጃጀትና ቁመና እንዳይዝ ለማድረግ ነው ። አሁን ያለው ዉጊያ በዚሁ መልክ ከቀጠለና የመከላከያ ወታደሮችና መሳሪያቸው ቀስ በቀስ ቀደ ፋኖ ከተሸጋገረ ፋኖ እራሱ ብሄራዊ መከላከያነት ማደርጉ የግዜ ጉዳይ ብቻ ስለሚሆን ። ለዚህም ነው ዛሬ ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ኮንሰንትሬት አድርጎ የጄኔራል ሙሃባውን ጦር ሊወጋ እየተዘጋጀው ያለው ። የሙሃባው ፋኖ ከሁሉም በላይ የተደራጀ ሰራዊት ነው ስለሚባል ።

በእኔ እምነት ይህን የብርሃኑ ዘመቻን ፊት ለፊት ገጥሞ ኃይል ማባከን አያስፈልግም ። ብርሁን ሰሜን ወሎ ሲመጣ ፋኖ ደቡብ ወሎ ወርዶ ሌላ ጥቃት ማድረግ ነው ያለበት ። ጠላት አድቫንስ ሲያደርግ አፈግፍግ ይላል ሳይንሱ ። ከዚያ የብርሃኑን ሰራዊት በትናንሽ ቡድን በመከፋፈል ማምከን ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 05 Oct 2023, 01:39

እዚህ ሪፖርት ውስጥ አንድ የቆቦ ሰው ፋኖ ሰው ነው ወይስ መንፈስ ሲል ይጠይቃል! ያ ነው ቩካ የሚባለው !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 42570
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፋኖ ዉጊያ ስልት፡ ቩካ

Post by Horus » 07 Nov 2023, 02:49

ይህን ሃረግ ስጀምር የብርሃኑ ጁላን ጭንቅላት የሚቆጣጠረው የፋኖ ታክቲከኛ ነው ብዬ ነበር ። ለምሳሌ አሁን በመላ አማራ ከ10 እስከ 20 ግምባሮች የሚካሄደውን ውጊያ አስተውሉ ። የዛሬ ወር አካባቢ ያቢይ ታክቲክ ምን ነበር?

በአንድ ቦታ ግዙፍ ሰራዊት በማሰለፍና በማሸነፍ ተራ በተራ ፋኖን ማጥፋትና ከተማ አገር መያዝ ነበር ። ፋኖ ገና የጠላት ጦር መንገድ ላይ እያለ በመቁረጥ ያን ታክቲክ ዋጋ ቢስ አደረገው ።

የብርሃኑ ጁላ ጂሎችን ገደል እየከተተ ያለው የፋኖ ስልት ማፈግፈግ የሚባለው ነው ። ፋኖ በትልቁ ያወጀው ነገር እኛ ካሻን በማንኛውም ግዜ ከተማ ይዘን ከዚያም ጠላት ለማጥቃት ሲመጣ እናፈገፍጋለን አለ ፋኖ ። ይህ በጣም ተለመደ ስልት ነው ። ጠላት ሲሸሽ አሳድደው፣ ጠላት ሲታጠቃ አፈግፍግ ይላል የህዝባዊ ጦርነት ሕግ።

አሁን ይህቺን የሰሙ የጁላ ጂሎች ምን ቢሉ ጥሩ ነው ። ከ50 እስከ 100 ሺ ሰራዊት በ10 እስከ 20 ግምባር በአንድ ግዜ ማዕበል እንዘራለን፤ ያን ስናደርግ ፋኖ እንዳለው ከሁሉም ቦታዎች ያፈገፍጋል ። ያኔ እኛ ከተማና ገጠሮችን ይዘን የብልጽግና እስትራክቸር መልሰን እናዋቅራለን ብለው ስልት ሰለጡ ያቢይ ጄኔናሮች!!!

ይህ ሲሆን ፋኖ አባ ቩካ ምን ቢዘይድ ጥሩ ነው?! ይህን የብርሃኑ ጂል ስልት የበላው ፋኖ መጀምሪያ ጁላ ሰራዊቱን ባከማቸበት ትተው በቀጠነበት አውድ መቱት፤ ሲቀጥል አፈገፍጋለሁ ብሎ ጁላን የሸወደው ፋኖ ቀጥ ብሎ ቀን ተሌሊት በ20 ግምባሮች ገጠመው ።

አያችሁ አሁን ላይ ፋኖ አላፈገፈገም ! ጅላ ለረጅም all out ዉጊያ አልተዘጋጀም ። ስለሆነም 100 ሺ የጁላ ጦር በ30 ውይም 40 ሚሊዮን አማራ ውስጥ በቅርቡ እንደ ጨው ይሟሟል !

ቩካ ማለት ይህ ነው ። የጠላት ዉጊያ ፕላን መቆጣጠር !!!

Post Reply