Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጦርነቱን ባርከው ያስጀመሩ የኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች፤ ባላቸው ተፅዕኖ ልክም ለተፈፀመው በደል ውድመት የዘር ጭፍጨፋ መፈናቀል ረሃብ አስገድዶ መድፈር ከፖለቲከኞች እኩል ሚና አድርገዋል

Post by sarcasm » 01 May 2022, 10:32

"የሚያባሉን ፖለቲከኞች ናቸው" ..ተቀዳሚ ሙፍቲ በዛሬው እለት የተናገሩት ቃል ነው ..

ከወራቶች በፊት የሀይማኖት አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደጦር ግንባር ለመዝመት ወስነው ነበር

በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ አምላክ በሚል የዳቦ ስም ፈጣሪን ወገንተኛና የእነሱ አሃዳዊ ፖለቲካ ጉዳይ አስፈፃሚና ጠበቃ ለማድረግ የቻሉትን ሁሉ እንዳደረጉ መረሳት የለበትም።

ትምቢቱም ፤ እውነቱም ፤ እምነቱም ፤ ሀይሉም ፤ የእነሱ ብቻ እንደሆነ ከመፅሀፉም ከሀይማኖትም ከታሪክም ሲያመሳክሩ ... የእነሱን ቅዱስነት የሌላውን ዲያቢሎስነት ሲስሉና ሲገልፁ ጦርነቱን በመንፈሳዊ ፤ በመለኮታዊ ፤ በተአምራት አውድ ሲተነትኑ ሲያቀጣጥሉ እንደነበር መታወቅ አለበት።

በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ ጉዳዩ የአለማዊ ፖለቲካ ቀውስ ያመጣው ጣጣ ሳይሆን የቅዱስነትና የእርኩስነት ሀይማኖታዊ መንፈሳዊ ካባ ሲደረብለት ተመልክተናል።
ታዲያ ይህንን ጉዳይ ያላስተባበሉ የሀይማኖት አባቶች .. ጦርነቱን ባርከው ያስጀመሩ የሀይማኖት ስር ቁማርተኞች ፤ ከሰማያዊ ከፍታ ወርደው በግልፅ ለአንዱ ወገን ድጋፋቸውን የሰጡ ሼሆች ፓስተሮችና ቄሶች እንደነበሩ ማስታወስ አለብን።

የሀይማኖት አባቶች .. የእኩልነት ፤ የፍትሀዊነት ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም ፤ የአንድነት ፤ የእርቅ ፤ የወንድማማችነት ፤ የአብሮነት ፤ የሰብዓዊነት ተምሳሌት መሆን ሲገባቸው በግልፅ ይህንን ሽረው ለአንዱ ወገንተኛ ከሆኑ በኃላ ... ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸው ጉዳዩን አክርሮት ነበር።

ሳጠቃልለው የሀይማኖት አባቶች .. ከሰማያዊና ከስነምግባር አስተምህሮ ዝቅ ብለው ጦርነት ደግፈው መግለጫ ሰጥተዋል።

አለማዊ ፖለቲካ ላይ ተነክረው ተሰሚነታቸው አጥተዋል። ወገንተኛ በመሆን ህዝቡን ለሁለት ከፍለውታል። የሴራ ፖለቲካ ላይ ተነክረው ተፅዕኖቸውን አጥተዋል።
ለዚህ ሁሉ ጥፋቶች የአብይ አህመድ የፖለቲካ አካሄድ ድርሻው የአንበሳው ነው። ለጥቅም ያደሩና ከመንግስት ጋር ያበሩ የሀይማኖት አባቶች ደግሞ ሁለተኛ ተጠያቂዎች ናቸው።

አሁን ላይ ለገባንበት ቀውስ መፍትሔ ሲያቀርቡ የሚደመጡ ተው ሲሉ የሚሰሙ .. ብሎም በህዝቡ የሚፈሩ የሀይማኖት አባቶች የሉንም ማለት ይቻላል። ቢኖሩም ድምፃቸው አይሰማም።

እንደ ሀገር በፖለቲካ ሽኩቻዎች ምክንያት ኢኮኖሚያችንን ወይም ሰላማችንን ብቻ አይደለም ያጣነው... ማህበራዊ ስነልቦናዊ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችንም ጭምር ነው የናድነው። ባለቀ ሰአት ሰበብ መደርደር ማላከክ ምንም አይፈይድም።

የሀይማኖት አባቶች ትግራይ ላይ በተፈጠረው ጦርነት ፣ ቀውስ ፤ ውድመት ፣ ግድያ ፣ የዘር ጭፍጨፋ ፣ መፈናቀል ፣ ረሃብ ፣ አስገድዶ መድፈር .. ወዘተረፈ ከፖለቲከኞች እኩል አስተዋጽኦ አላቸው። ባላቸው ተፅዕኖ ልክም ለተፈፀመው በደል ትልቅ ሚና አድርገዋል።

ይህንን ታሪክ ፈፅሞ አይረሳውም !!
Please wait, video is loading...
Finfinne Times

Abere
Senior Member
Posts: 15394
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጦርነቱን ባርከው ያስጀመሩ የኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች፤ ባላቸው ተፅዕኖ ልክም ለተፈፀመው በደል ውድመት የዘር ጭፍጨፋ መፈናቀል ረሃብ አስገድዶ መድፈር ከፖለቲከኞች እኩል ሚና አድርገ

Post by Abere » 01 May 2022, 11:24

አይ ትግሬ እንድህ ሆነ በቃ? ውለታ ተረሳ? ፓትርያርኩ አባ ማትያስ እኮ ጠዋት ማታ ትግራይ! ትግራይ! እያሉ ነው - አማራ እና አፋርን እረሱት እንጅ። ምናልባት አማራ እና አፋር የጡት-እምነት ልጆች ሳይሆኑ አይቀሩም መሰለኝ። እኔ የሚገርመኝ ለምን ትግራይ ዋና ጥላታቸው ወያኔ አይኮንኑም? ወያኔ ካልጠፋ ትግሬ ሺ አመት ገና ያለቅሳል። እውነቱ ይኸ ነው።አለባብሶ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ። ሰላም ከፈለጋችሁ ወያኔን ንቀሉ። ከዚህ ውጭ በሰው ሳይሆን በእራሳችሁ ነው የምትቀልዱት።

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ጦርነቱን ባርከው ያስጀመሩ የኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች፤ ባላቸው ተፅዕኖ ልክም ለተፈፀመው በደል ውድመት የዘር ጭፍጨፋ መፈናቀል ረሃብ አስገድዶ መድፈር ከፖለቲከኞች እኩል ሚና አድርገ

Post by sarcasm » 20 Aug 2023, 10:22

sarcasm wrote:
01 May 2022, 10:32

ይህንን ታሪክ ፈፅሞ አይረሳውም !!
Please wait, video is loading...
Finfinne Times
በታሪክ ብቻ ሳይሆን አሁንም accountability በተግባር መጠየቅ የግድ ነው።

Post Reply