የሆነ ማንነት ፈብርከህ ልትከበር እስከ ምትሞት እየታከት ነው ። ያንተ ቁጥር 1 ችግርና የውድቀትህ ምንጭ ይህ ነው ። መመሪያ እራሱ ቃላቱ ፋና እና ዲካ ላስተማረህ ግዕዝ አክብሮት ስጥ! አንድ ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ ካልቸር ይማራል ያ ምንም ማለት አይደለም ። ያን እስከ ካድክ እና በእረኛነትና ወራሪነት ባህሪህ እስከ ቀጠልቅ ድረስ አሁን ያለውን ጥላቻ ነው የምታመርተው!
እስቲ መጀመሪያ ቋንቋህ ከየት እንደ መጣ እወቅ?!
ሲቀጥል እነዚህ ምታያቸው ቋንቋቸውን ለውጠህ ግን ባህላቸው ተሸክመህ ያለሀው ክርስትናንን፣ እልልታን ያስተማሩህ፣ ሹሩባን ያስተማሩህ፣እንጊጫን ያስተማሩህ ፣ ኤሬቻን የሰጡህ አባቶችህ አያቶችህ የገላንና ያዬ ጉራጌዎች ናቸው ። ዛሬ ዘራችውን ልታጠፋ ትዳክራለህ !!!
ይህ የምታየው የፊቃቆ ለቀማና (የአክርማ ለቀማና) የአዳብና ባህል ከነገ ፍልሰታ ነሃሴ 15 ደመራ መትከያ ጀምሮ አዲስ አመትን (አክራሚ) አልፎ እሰከ መስቀል የሚከበረው የልጃገረዶችና ወጣቶች በዓል ነው ። ለሰጠንህ ካልቸር አመስግን !!!
ፊቃቆ ማለት አክርማ ሴቶች ልዩ ልዩ ስፌት የሚሰሩበት ስንደዶ ሳር ነው ። አንዲት ልጃገረድ ለጋብቻ ደርሳ የሴትነት ሙያ የምትማርበት ማለት ነው ። አዳብና ማለት አደይ አብና ማለት ነው። የአደይ አበባ መስጠት፣ መስጫ ባህል ሲሆን በንቁጣጣሽ ለጃገረዶች ከቤት ቤት የሚሰጡት አበባና እስከ መስቀል ድረስ በነጻ ለጨዋታ ወጥተው ከጎረምሶች ጋር በመጫወት በሎሚ የሚወጉበት ፍቅረኛ የሚመርጡበት ውድ የጉራጌ ወጣት ባህል ነው ።
እስቲ የገላን ልጃገረዶች ይህን ባህል እስካሁን ይዘውት እንደ ሆነ እናያለን ። አንተ ግ ን መጀምሪያ ታሪክን አትካድ፣ ሁለተኛ ይህን ሁሉ ባህል ያስተማሩህ ቅድመ አያቶችክን አትካድ! ችግርህ ያ ነው ከየት እንደ መጣህ እየካድ ወደፊት ለመሄድ መሞከርህ !
ፍቃቆ ማለት ይህ ነው!