Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ፋኖና . . . . .

Post by sarcasm » 13 Aug 2023, 09:25

" አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርሙኛል " እንዲል ከያኒው
ተጻፈ በአናንያ ሶሪ


አንድ ከኩራተኛው ክልል የሄደ ሯጭ ነው አሉ....

"እኛ እንዴት ከነኚያ እናንሳለን?! እንደውም እኔ ክልላችንን ወክዬ እሮጣለሁ" ይልና ቲፎዞዎቹን ሰብስቦ ስታዲየም ይገባል...

ኋላ ሩጫው ይጀመርና ከፊት መምራት ይጀምራል ባንዴ....

ደጋፊዎቹ ስሙን እየጠሩ፦ "..... መራቸው! መራቸው! መራቸው!" ይላሉ በፈንጠዚያ

ትንሽ ቆይቶ ይደክምና እኩል መሮጥ ይጀምራል ከሌሎቹ ሯጮች...

ይሄኔ ደሞ ስሙን ይጠቅሱና ፦ " ታጀበ! ታጀበ! ታጀበ! " ይሉለታል።

ሊጠናቀቅ አካባቢ፦ ወደኋላ ይቀራል፤ ደጋፊዎቹም እየጠሩት በስሙ "ነዳቸው! ነዳቸው! ነዳቸው" ይሉለታል!

መጨረሻ ላይ ሰውዬው በጀብድ እንጂ በስልት አልገባበትምና ትንሽ ያጥወለውለዋል፣ ወዲያውም ሽቅብ ማስመለስ ይጀምራል!

ደጋፊዎቹ፦ "ናቃቸው! ናቃቸው! ናቃቸው!" ይሉ ገቡ ጭራሽ 🙂

የደገፍነው እየወደቀብን ሳለ፣ በጭብጨባ እስከሞት መሸኘት ግን ምን ይሉት ዠግንነት ይሆን?!

# ለማንኛውም ለአቶ ዮሐንስ ቧያሌው የ"እንኳን ደስ አለህ!" መልዕክቴን አድርሱልኘ!

ሃሃሃሃሃ

Please wait, video is loading...