Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

ፋና ወጊው ፋኖ!

Post by Assegid S. » 10 Aug 2023, 17:44

በመጀመሪያ የፋኖን ስርወ-ቃልና ትርጉም ግንዛቤ እንዲኖረን ያደረገውን ወንድም Horus ላመስግን። ከዛም ... ፋኖ እንደ ስሙ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ከዘር ገነኑ የኦህዴድ አገዛዝ በእምቢተኝነት ለመውጣት ፋና ወጊ ሆኗልና ትልቅ ምስጋናና ክብር ይገባዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ህንድ ፊልም “አክተሩ” እንጂ “ስክሪፕቱ” ብዙም ስለማይቀየር ጅማሬውን አይቶ ፍፃሜውን መገመት፣ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን መተንበይ ፍፁም አይከብድም። ስለዚህም ነበር አስቀድሜ ከዓመት በፊት የህወሃት ጦርነት ሲዳከም : አንተ ነህ ባለተራ … ተዘጋጅ ኣማራ! ስል የነበረው።

ዕድሜ ለፋኖ ህወሃትና ኦህዴድ በኣማራው ሰማይ ላይ ሲከመሩት የነበረው የጥፋት ደመና … እንደ ፍላጎታቸው ዶፍ ሆኖ ሳይዘንብ አካፍቶ ብቻ እንዲበተን ተደርጓል። ባለተራ ኦሮሙማ ናት። የሸኔ ቁጭ ብሎ መሽናትና ለመሪው አስቀድሞ እሮሮ ማሰማት ይህን ዕውነት ከመገንዘብ ነው። ፈጣሪንና ህግን ንቃ ሰቆቃ ያበላችው ህዝብ ከእንቅልፉ ነቅቷል። አሁን ክልሌ ውስጥ ነው ብላ ኣሳር ያስቆጠረችው ብሔር ብሔረሰብ እንደ ክላስተር ቦንብ በየሥፍራው የመፈንዳቱ እውነት የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው።

ይህ የፋኖ ድንገተኛ ጥቃት ለኣማራና ለሌላው በኦሮሙማ ዘረኛ አገዛዝ ስር ለወደቀው ማህበረሰብ ወሳኝ ምዕራፍ ጥሏል። እንዴት? ከተባለም … በጥቂቱ:

• ለብሔር ብሔረሰቦች መነቃቃትና ለኦሮሙማ ጉልበት መንቃት (መሰነጣጠቅ) ፋኖ ጉልህ ሚና ተጫውቷል (ጥርስ ከማነቃነቅም በላይ ሔዷል።)

• በኣማራ ክልል ጥቂት የማይባሉ የብኣዴን አሽከሮችን ከማፅዳቱም ባሻገር ሌሎች በእግራቸው እንዳይተኩና ለመተካትም እንዳያስቡ ከፍተኛ ስጋት በመፍጠር ረገድ
የተሳካ እንቅስቃሴ ነበር።

• ይህ የፋኖ ተጋድሎ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በኣጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ኣማራ ከኦሮሙማ መሩ መንግስት በሚገባ ለይቶታል። ለዚህም ደግሞ የፋኖ ተጋድሎ
ብቻ ሳይሆን ኣዲስ ኣበባ በኣማራ ተውላጆች ላይ እያደረሰ ያለው የጅምላ እስርና ማንገላታት ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል - ያደርጋል።

• ኣላዋቂ የሆኑ ሰዎች የኣማራ ገበሬ ዘንድሮ ባለማረሱ በሚቀጥለው ዓመት ክልሉ ይጎዳል ብለው ሆድ ሊያስብሱን ይሞክራሉ። የተራበ ህዝብ በር ዘግቶ የሚያለቅስ፣
መንገድ ዳር ቆሞ የሚለምን አድርገው ለመሳል ቢሞክሩም ... ትልቁ እውነት "A hungry man is an angry man"
እንደሚባለው ... 'የተራበ ህዝብ መንግስትን ነው የሚበላው'። ስለዚህም ይህ ዘንድሮ ገበሬውን በኮማንድ ፖስት ዘመቻ ከእርሻ ማስተጓጎል ... ለከርሞ
የሚነድ የእሳት ፍም እንደማዳፈን ነው።

• በኣጠቃላይ ... ቤት ፈረሳውና ማፈናቀሉ፣ ኃይማኖታዊ ልዩነቱና ጫናው፣ ወዘተ ይህን የኦሮሞ የበላይነት ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ለሚደረገው
የፍፃሜው ጦርነት ለፋኖ ጥሩ እርሾ ይሆናል።

ህዝብ ጣፊያው ብቻ ሳይሆን አንጀቱ ጭምር ሓሞት (ምሬት) ተሞልቷል! ከእንግዲህ ቦኃላ የአገዛዙ 'ኢትዮጵያ ትበተናለች' ጩኸት ማስፈራሪያም ማስተዛዘኛም ለመሆን ጉልበት የለውም። እንኳን ተመልሶ ለመለቀም ዕድል ሊኖራት እንደቆሎ መበተን አይደለም ... ለምን ተመልሶ ለመታፈስ ዕድል ላታገኝ እንደ ጨው አትሟሟም! ሁሉም የድርሻውን ይዞ ይወጣል ሲል አምርሯል። ህዝብ እንጂ ሀገር የሚመሰርተው ... ሀገር ህዝብ አይፈጥርም!

Revelations
Senior Member+
Posts: 34515
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ፋና ወጊው ፋኖ!

Post by Revelations » 10 Aug 2023, 18:09

ፋኖ ጥይቱ ብቻ ሳይሆን ስለ ፋኖ የተዘፈኑ ዘፈኖች፣ ቀረርቶዎች እና ሽለላዎን ያስደነበሩት ፋሽስታዊ የኦሮሙማ አገዛዝ ስልክ እየበረበረ እነኝህን ሙዚቃዎች ሲያገኝ ማሰርና መደብደብ ብቻ ስይሆን እስከመግደል መድረሱ ደጋግሞ እየተዘገበ ነው::

Horus
Senior Member+
Posts: 37036
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋና ወጊው ፋኖ!

Post by Horus » 10 Aug 2023, 22:46

አሁን የኢትዮጵያ ናሬቲቭ ተለውጧል ! ይህ ዝም ብሎ ቀላል ለውጥ አይደለም ። የጎሳ ትርክት በዲፎልት የሚቀበሉት ተረት ወይም ሚጥዝ መሆኑ አከተመ ። ስለዚህ ትግሉ አሁን በሁሉም የህይወታችን መስክ ነው ፤ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይኮሎጂ፣ ታሪክ ፣ አርት ፣ ካልቸር ፣ ወዘተ ። ኢትዮጵያዊ ፋኖነት ከዚህ በኋላ መሽኮርመን አቁመን ማኖ አማኖ አንድ ላንድ መግጠም ነው በሁሉም መስክ ። የብሄር ጥያቄ የሚባል ተረት አክትሟል ። ለውጡ እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ ነው ። የተጨቆነ ብሄር የሚባል የለም። ያለው ሌሎችን ለመግዛት የሚያሰል ፖለቲክኛ ነው። ያንን ደሞ አንድ ላንድ ገጥመን መታገል ነው ።

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ፋና ወጊው ፋኖ!

Post by sun » 10 Aug 2023, 23:14

Assegid S. wrote:
10 Aug 2023, 17:44
በመጀመሪያ የፋኖን ስርወ-ቃልና ትርጉም ግንዛቤ እንዲኖረን ያደረገውን ወንድም Horus ላመስግን። ከዛም ... ፋኖ እንደ ስሙ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ከዘር ገነኑ የኦህዴድ አገዛዝ በእምቢተኝነት ለመውጣት ፋና ወጊ ሆኗልና ትልቅ ምስጋናና ክብር ይገባዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ህንድ ፊልም “አክተሩ” እንጂ “ስክሪፕቱ” ብዙም ስለማይቀየር ጅማሬውን አይቶ ፍፃሜውን መገመት፣ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን መተንበይ ፍፁም አይከብድም። ስለዚህም ነበር አስቀድሜ ከዓመት በፊት የህወሃት ጦርነት ሲዳከም : አንተ ነህ ባለተራ … ተዘጋጅ ኣማራ! ስል የነበረው።

ዕድሜ ለፋኖ ህወሃትና ኦህዴድ በኣማራው ሰማይ ላይ ሲከመሩት የነበረው የጥፋት ደመና … እንደ ፍላጎታቸው ዶፍ ሆኖ ሳይዘንብ አካፍቶ ብቻ እንዲበተን ተደርጓል። ባለተራ ኦሮሙማ ናት። የሸኔ ቁጭ ብሎ መሽናትና ለመሪው አስቀድሞ እሮሮ ማሰማት ይህን ዕውነት ከመገንዘብ ነው። ፈጣሪንና ህግን ንቃ ሰቆቃ ያበላችው ህዝብ ከእንቅልፉ ነቅቷል። አሁን ክልሌ ውስጥ ነው ብላ ኣሳር ያስቆጠረችው ብሔር ብሔረሰብ እንደ ክላስተር ቦንብ በየሥፍራው የመፈንዳቱ እውነት የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው።

ይህ የፋኖ ድንገተኛ ጥቃት ለኣማራና ለሌላው በኦሮሙማ ዘረኛ አገዛዝ ስር ለወደቀው ማህበረሰብ ወሳኝ ምዕራፍ ጥሏል። እንዴት? ከተባለም … በጥቂቱ:

• ለብሔር ብሔረሰቦች መነቃቃትና ለኦሮሙማ ጉልበት መንቃት (መሰነጣጠቅ) ፋኖ ጉልህ ሚና ተጫውቷል (ጥርስ ከማነቃነቅም በላይ ሔዷል።)

• በኣማራ ክልል ጥቂት የማይባሉ የብኣዴን አሽከሮችን ከማፅዳቱም ባሻገር ሌሎች በእግራቸው እንዳይተኩና ለመተካትም እንዳያስቡ ከፍተኛ ስጋት በመፍጠር ረገድ
የተሳካ እንቅስቃሴ ነበር።

• ይህ የፋኖ ተጋድሎ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በኣጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ኣማራ ከኦሮሙማ መሩ መንግስት በሚገባ ለይቶታል። ለዚህም ደግሞ የፋኖ ተጋድሎ
ብቻ ሳይሆን ኣዲስ ኣበባ በኣማራ ተውላጆች ላይ እያደረሰ ያለው የጅምላ እስርና ማንገላታት ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል - ያደርጋል።

• ኣላዋቂ የሆኑ ሰዎች የኣማራ ገበሬ ዘንድሮ ባለማረሱ በሚቀጥለው ዓመት ክልሉ ይጎዳል ብለው ሆድ ሊያስብሱን ይሞክራሉ። የተራበ ህዝብ በር ዘግቶ የሚያለቅስ፣
መንገድ ዳር ቆሞ የሚለምን አድርገው ለመሳል ቢሞክሩም ... ትልቁ እውነት "A hungry man is an angry man"
እንደሚባለው ... 'የተራበ ህዝብ መንግስትን ነው የሚበላው'። ስለዚህም ይህ ዘንድሮ ገበሬውን በኮማንድ ፖስት ዘመቻ ከእርሻ ማስተጓጎል ... ለከርሞ
የሚነድ የእሳት ፍም እንደማዳፈን ነው።

• በኣጠቃላይ ... ቤት ፈረሳውና ማፈናቀሉ፣ ኃይማኖታዊ ልዩነቱና ጫናው፣ ወዘተ ይህን የኦሮሞ የበላይነት ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ለሚደረገው
የፍፃሜው ጦርነት ለፋኖ ጥሩ እርሾ ይሆናል።

ህዝብ ጣፊያው ብቻ ሳይሆን አንጀቱ ጭምር ሓሞት (ምሬት) ተሞልቷል! ከእንግዲህ ቦኃላ የአገዛዙ 'ኢትዮጵያ ትበተናለች' ጩኸት ማስፈራሪያም ማስተዛዘኛም ለመሆን ጉልበት የለውም። እንኳን ተመልሶ ለመለቀም ዕድል ሊኖራት እንደቆሎ መበተን አይደለም ... ለምን ተመልሶ ለመታፈስ ዕድል ላታገኝ እንደ ጨው አትሟሟም! ሁሉም የድርሻውን ይዞ ይወጣል ሲል አምርሯል። ህዝብ እንጂ ሀገር የሚመሰርተው ... ሀገር ህዝብ አይፈጥርም!

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ፋና ወጊው ፋኖ!

Post by sun » 10 Aug 2023, 23:18

Revelations wrote:
10 Aug 2023, 18:09

Post Reply