Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by Assegid S. » 09 Aug 2023, 08:39

https://www.eaglewingss.com/



ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

ከጥቂት ቀናት በፊት … William Scott Ritter ያዘጋጀውን ‘Agent Zelenski’ የሚል የኣንድ ሰዓት ከሃያ-ሁለት ደቂቃ እርዝማኔ ያለውን documentary ፊልም ተመልክቼ እንደጨረስኩ … ‘ጥቁሩ ዘለንስኪ’ ፊቴ ላይ ድቅን አለ። በእርግጥ … አሁን ሀገራችን ላይ ባለው ነባራዊ ሁኔታ፥ ለምዕራባውያኑ ፍላጎት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ በማገልገል የወኪል ዘለንስኪን መሳይ ተግባር እየከወነ ያለው ግለሰብ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይሁኑ ወይንስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ለመወሰን ትንሽ ሰከንዶችን ማጥፋቴ አልቀረም። በመጨረሻ ግን … በጥቂት ግራም ልዩነት  ምርጫዬ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢያዘነብልም፥ በዚህ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት በመነገድ ረገድ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚጫወቱት ሚናም ቀላል እንደማይሆን በደንብ እገነዘባለሁ።

ይህን ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ በሙሉ መመልከት … የዩክሬሩ Volodymyr Zelenskyj እንዴት ወደ ፕሬዚደንትነት ስልጣን እንደመጡ፣ የትና በማን  በወኪልነት ተመልምለው እንደተሰማሩ ጠለቅ ያለ ምልከታ ለመስጠት ቢረዳም፥ ወሳኝና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተነፃፃሪነት አላቸው ብዬ ያሰብኳቸውን … የምዕራቡ ዓለም ለፕሬዘደንቱ በኣስቸኳይ እንዲተገበሩ የሰጣቸውን ኣሥር ተግባራት (Tasks) ብቻ በመንቅስ ቪዲዮውን እንደሚከተለው አሳጥሬ አቅርቤዋለሁ።

ተመልካች የራሱን ግንዛቤ እንዲይዝ ይረዳል ብዬ በማሰብም … ከእያንዳንዱ ተግባር (task) በተጓዳኝ በሀገራችን ውስጥ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ናቸው ብዬ የማስባቸውን ግልፅ እውነታዎች በኣጭር ዝርዝር አስቀምጫቸዋለሁ።



TASKS given to Volodymyr Zelenskyj:

1. THE RUSSIAN LANGUAGE. To eliminate the Russian language. (ተነፃፃሪ ተግባር: የአማርኛ ቋንቋን ማዳከምና ማጥፋት)
[*]በኣዲስ አበባና በክልል ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን የማዳከም እንቅስቃሴ። በትግራይና በኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚገኙ በማናቸውም ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኣማርኛ ቋንቋ ትምህርት እንዳይሰጥ ማገድ። በኣማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር የኣማርኛ ቋንቋ ጥናት ተቋማትን መዝጋት። በዶክመንተሪ ፊልሙ ውስጥ በቀረቡ ምሁራን አስተያየት መሰረት ይህ ቋንቋን የማዳከም ተግባር ለ ‘ethnic cleansing’  ወሳኝና የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።

2. SPLIT IN UKRANIAN ORTHODOX CHURCH. To finalize the Church split. (ተነፃፃሪ ተግባር: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ክፍፍል)
[*]አሁን እንደሚታየው በመንግስት ድጋፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቢቻል በእያንዳንዱ አልያም በኦሮሚያና በትግራይ ክልል ደረጃ ከፋፍሎ ማደራጀት። በዶክመንተሪ ፊልሙ ውስጥ በተጠቀሰው አስተያየት መሠረትም … የዚህ ተግባር ዋነኛ ዓላማ ከቤተክርስቲያኒቱ መጠሪያ ላይ ያለውን ‘Russia’ (ወይንም ‘ሞስኮ’) የሚለውን ስም መፋቅ እንደሆነ ሁሉ ... ወደ ሀገራችን ነባራዊ እውነት ስንቀይረው ደግሞ … ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ መጠሪያ ስም ላይ ‘ኢትዮጵያ’ የሚለውን ገላጭ መደምሰስ ይሆናል።

3. REWRITING HISTORY. (ተነፃፃሪ ተግባር: ታሪካዊ እሴቶችን ማፍረስና ታሪክን ቢቻል እንደ ኣዲስ አልያም አዛብቶ መፃፍ)
[*]ይህ ካለፈው የህወሃት አገዛዝ ጀመሮ እየተሞከረ ያለ ክንዋኔ ቢሆንም፥ በኦህዴድ መንግሥት ግን በስፋትና በኣፋጣኝ መሬት ላይ እየወረደ ያለ ተግባር ነው። ለምሳሌም፦ የኣድዋንና የምኒልክን ታሪክ ማዛባት፣ የበዓሉን አከባበር ልማድና ቦታን መቀየር፣ ነባር ታሪካዊ ቅርሶችን (ሓውልቶችን፣ ቤተ-መንግስቶችን፣ ቤተ-እምነቶችን) ማንሳትና ማፍረስ፣ ሰንደቅ-ዓላማን መቀየርና ቀድሞ ከሚሰቀልበት ቦታ (ከመኪናና ከልብስ ጥለት ላይ ጭምር) ማስወገድ፣ ታሪክን የሚያውቁና የሚያስተምሩ ምሁራንን (አቶ ታድዮስ ታንቱን ጨምሮ) ማንገላታትና ማሰር … ወዘተ የመሳሰሉት ተግባራት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

4. UKRANIANS BANS DOMESTIC TV CHANNELS. (ተነፃፃሪ ተግባር: የግል ጋዜጣና ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና)
[*]ምንም እንኳ በሀገርችን ውስጥ በግለሰብ ደረጃ አየር ላይ የሚውሉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ባይኖሩም፥ የመንግስትን የውጭ ተልኮ አስፈፃሚነት የሚያጋልጡና የሚቃወሙ ጋዜጦችን መዝጋትና ጋዜጠኞችንም ማሰር የእለት ተእለት ተግባር ነው። የፍትህና ሌሎች ጋዜጦች ህትመት መቋረጥ፣ በስፋት እየቀጠለ ያለው የጋዜጠኞች እስርና መሰደድን እንደ አስረጅ መውሰድ ይቻላል።

5. BAN THE OPPOSITION. (ተነፃፃሪ ተግባር: ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች ማስወገድ)
[*]ይህን በተመለከተ… ከኣማራ እስከ ጉራጌ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ላይ በሰፊው እየተፈፀመ ያለው የግድያ፣ የማፈን፣ የድብደባና እሥር ተግባር ግልፅ ማስረጃ ነው።

6. MILITARY BIOLABS.

7. MERCENERIES. (ቅጥ ያጣውና ቅልጥ ያለው የህወሃትና የኦህዴድ ቅጥረኛነት)
[*]መጥፎ እድል ሆኖ ካለፈው የህወሃት አገዛዝ ጀምሮ እስከ አሁኑ የኦህዴድ መንግስት … ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም የፖለቲካ ፍላጎት አስፈፃሚነት መዳፍ ሥር ለመውጣት አልተቻላትም። ኢትዮጵያ የኣሜሪካንን ጦርነት ስትወጋ ቀላል በማይባል ቁጥር የዜጎቿን ህይወት አጥፍታለች - አስጠፍታለች። አሁንም ያለው እውነት ከዚህ የተለየ አይደለም። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ በኣፋቸው ‘ለኣሜሪካን ጥቅምና ደህንነት መስዋዕት እሆነለሁ’ ሲሉ መነበባቸው ነው።

ከዚህ ባሻገር … በኣፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት በቸልታ ሊመለከቱት የማይገባው ስጋት፣ የወልቃይትና የኣካባቢው ይዞታ ነው። ይህ መሬት በኣንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በቅጥረኛው ህወሃት አገዛዝ ሥር የሚወድቅ ከሆነ … ለይመሰል በሚፈረም ወታደራዊ ስምምነት … ሰዓታት እንኳን ባልሞላ የጊዜ ፍጥነት …  የኣሜሪካን ወይንም የምዕራባውያን ጦር በቦታው ላይ ሊሰፍር እንደሚችል መጠርጠር ተገቢ ነው። የውጭ ወራሪዎች ከ’ምዕራብ ትግራይ’ ይውጡ የሚል የኣዛኝ ቅቤ ኣንጓች ግፊት ዓላማው ወታደራዊ-ሰፈራ ነው። ይህ ደግሞ ከመንግሥት ለውጥ (በእነርሱ አጠራር ከ Regime change) እስከ ሀብት ስርቆት (resource looting) ድረስ በቀጠናው ላይ የሚፈፅሙትን ዓለማቀፋዊ ወንጀል ቀላል ብቻ ሳይሆን ስውርም እንዲሆን ይረዳል።

8. A LEGALIZATION OF NAZISM.
[*]በኣንድ ዘርና ሀይማኖት ላይ ያተኮረ የጥላቻ ንግግር፣ የጅምላ እስር፣ ግድያና መፈናቅል እንደ በጎ ተግባር ተቆጥሮ ከክልል መሪዎች እስከ ተራ የመንገድ ላይ ቦዘኔዎች በኣደባባይ በከፍተኛ ድምፅ የሚደሰኩርበትን መድረክ ማየት እንደ Latinos carnival  አዝናኝ ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የሰማናቸውና የምንሰማቸው “የጀርባቸውን አጥንት ሰበርነው፣ ዓይናቸውን አስለቀስነው፣ ህጋዊ ድሆች አደረግናቸው” ወዘተ የሚሉ … ህዝብን ለኣረመኔያዊ ተግባር ማነቃቂያ የሚውሉ ቃላቶች … ከቀድሞው የኣውሮፓ ፋሽስትና ናዚዝም ስርዓት መፈክር የሚለዩት በትርጉማቸው ሳይሆን በተነገሩበት ቋንቋና ዘይቤ ብቻ ነው።

9. SALE OF LAND. (ተነፃፃሪ ተግባር: የጫካ ከተማ፣ ሸገር city complex እና ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች)
[*]ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የኦህዴድ አገዛዝ በከፍተኛ ደረጃ ደሃውን በማፈናቀል ተጠምዶበት ያለው ንግድ መሬት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ  ‘እናንተ ገንዘብ አልሰጣችሁኝም ስለዚህም ምንጩንና ባለቤቱን ልትጠይቁኝ አትችሉም’ የሚሉን … ነገር-ግን ቀላል  የማይባል የመሬት ሽፋን እየወሰዱ ያሉት ፕሮጀክቶች ይህን እውነት አስረጂዎች ናቸው። በቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነቡት የጫካ ቤተ-መንግስት፣ የሸገር ከተማ ኮምፕሌክስና ሌሎች ፕሮጀክቶች ባለቤትነታቸው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ (በሀገር በቀል ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊ ዜጎች ስም)  ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች እንደሆነ አያጠራጥረም።

10. SIGN AN AGREEMENT THAT UKRAINE RECEIVES WEAPONS AND EQUIPMENTS ON CREDIT.
[*]እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት የሥርዓቱ ባለሟሎች ውጪ አጠቃላይ ዜጋው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የውጭ ዕዳ ክብደቱና የገንዘብ ግሽበቱ ቀጥተኛ ተጠቂ ነውና ይህን በተመለከት ምንም ማለት የሚኖርብኝ መስሎ አይሰማኝም። ይሁንና ግን … አሁንም ቢሆን መንግሥት በሥልጣኑ ለመቆየት IMF እና World Bank’ ን ለመሰሉ አበዳሪ ተቋማት አስገዳጅ inhumane pre-conditions እጅ በመስጠት የሚቀበለው ብድር … ቢያንስ መጪው ሁለት ወይንም ሦስት ትውልድ ለምዕራባውያኑ በዕዳ የተያዘ ‘ተንቀሳቃሽ ንብረት’ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርገዋል።

N.B. ሙሉ ዶክመንተሪ ፊልሙን ለመመልከት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይቻላል።

A Scott Ritter Investigation: Agent Zelensky
William Scott Ritter Jr. (born July 15, 1961) is an American author, pundit, former United States Marine Corps intelligence officer and former United Nations Special Commission (UNSCOM) weapons inspector.

Ritter served as a junior military analyst during Operation Desert Storm. He then served as a member of the UNSCOM overseeing the disarmament of weapons of mass destruction (WMD) in Iraq from 1991 to 1998, from which he resigned in protest. He later became a critic of the Iraq War and United States foreign policy in the Middle East.

Zmeselo
Senior Member+
Posts: 37345
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by Zmeselo » 09 Aug 2023, 09:25

Ukraine says woman held in plot to assassinate President Volodymyr Zelenskyy as airstrikes kill 3. Ukraine's intelligence agency, the Secret Service of Ukraine (SSU), said Monday that it had arrested a woman in connection with an alleged assassination plot against President Volodymyr Zelenskyy.
https://www.cbsnews.com/news/ukraine-ru ... v-kherson/

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10941
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by ethiopianunity » 09 Aug 2023, 10:16

Don't forget the foreigners have projects for each country around the world, for Ethiopia which started 60 some years ago after the overthrow of Ase H/Selassie, this project has been implemented under Derg for example, no body knows why our people who speak Gala (my pardon) the reality the word "Oromo" never existed prior to Derg regime, Derg named or changed the former name to Oromo. Where did it come from? It is not wrong to change name as the Oromos can do what they want, I believe there is sinister in this Oromo changing. Many anti Ethiopia, anti veterans have been implemented, then Tplf continued, then pp government could be doing the final project against Ethiopia and people of Ethiopia. There is no support or opposing this government as it was being given a chance after 27 years of Tplf debacle, but, any anti Ethiopian especially the people they want to destroy to make a way for foreingers is the lands of Amara, Tigray and Afar, especially Amara, they have to break it. The so called Debub, Oromiya are happy as pp party is promising them it is their turn so they are cleaning house especially in Oromiya pro Ethiopia. Have you heard any news in Oromiya, what is happening? What their media is? Can you imagine, their media is OMN, anti Ethiopian, anti Amara, media. Those leaning towards Ethiopianism are covertly being eliminated, no other Ehtiopians are allowed to enter Oromiya. Why did Abyi quickly took over the country? Because the Youth all over Ethiopia were united that ousted Tplf. Quickly the Aby group and the welcomed OLF including Jaware lied it was Kero who over threw Tplf. The so called FULL supporters of this regime can only be because they have full or part blood that is why and what used to be the Ethiopian army sacrificed the people is now changed to pro pp/Oromiya army. They forgot why Olf was invited, why Welega people are being killed, why Dawd Ibsa is silent is in power in Wellega. Why is it that it is easy to start war in Tigray and Amara and not Wellega? Why did it take Mekelakeya not willing to get in Wellega and eliminate the murderers? Could it be it is the Oromiya region doing the killing? If Mekelakeya is in Wellega, the war will also be against Oromiya that is why. Why is it ok to stary war with Amara and Tigray region and not in Oromiya? Could it be because the future power in Ethiopia is Olf or getting ready the break up of Ethiopia?

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10941
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by ethiopianunity » 09 Aug 2023, 10:24

Also, on the other hand, Amara is being programmed for its own elimination, such as agents of foreigners and Tplf are inside Amara and making it easy for the current regime and foreigners to attack Amara. Basically, Amara is set up to destroy itself by implants into the region. Don't forget, majority of Ethiopians speak Amharic very well and very easy to pause they hailed from Amara, there is no way of identifying if they are truly from there originally. Take for example, Eritreans, you don't know they are Eritreans unless they start speaking Tigrigna.

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by Assegid S. » 09 Aug 2023, 15:08

Zmeselo wrote:
09 Aug 2023, 09:25
Ukraine says woman held in plot to assassinate President Volodymyr Zelenskyy as airstrikes kill 3. Ukraine's intelligence agency, the Secret Service of Ukraine (SSU), said Monday that it had arrested a woman in connection with an alleged assassination plot against President Volodymyr Zelenskyy.
https://www.cbsnews.com/news/ukraine-ru ... v-kherson/
Hello Brother Zmeselo. Thank you so much for the informative comment. It is obvious that the man is a walking dead; either Kremlin or White House will silence him. Scott Ritter concluded his documentary (12’ 25’’) saying: Agent Volodymyr Zelenskyj has accomplished the tasks assigned by foreign intelligence agencies, the question is: will those in power still need someone who KNOWS TOO MUCH and wants too much?

As of me, they will finish him sooner or later. They don’t want to risk a gruesome confession he might do if he stays alive. Those ranchmen in the White House are well known for SLAUGHTERING the BULL after fattening with salt and molasses 8)

Best Wishes, Brother Zmeselo.

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

Post by Assegid S. » 09 Aug 2023, 15:18

ethiopianunity wrote:
09 Aug 2023, 10:24
Also, on the other hand, Amara is being programmed for its own elimination, such as agents of foreigners and Tplf are inside Amara and making it easy for the current regime and foreigners to attack Amara. Basically, Amara is set up to destroy itself by implants into the region. Don't forget, majority of Ethiopians speak Amharic very well and very easy to pause they hailed from Amara, there is no way of identifying if they are truly from there originally. Take for example, Eritreans, you don't know they are Eritreans unless they start speaking Tigrigna.
Hello Brother ethiopianunity; thank you so much for the detailed comment. I agree with everything you wrote here and above. You have mentioned important events and related persons to deepen the understanding. I must thank you for that.

Just to answer your question, no; I’ve never heard or seen OMN / OPDO media reporting the mass killing as well as the illegal internal displacement done in Oromia region. It is also my regret that, because of the common Amharic language, we are in a very hard position to sieve out OPDO and TPLF infiltrators who disguise themselves as Amhara to abort our struggle for FREEDOM. ለዛም ነበር እነዚህንና ሌሎች በእርግጥም ኣማራ ሆነው ለህወሃትና ለኦነግ ቅጥረኛ የሆኑትን ግለሰቦች አስመልክቶ ከሁለት ዓመታት በፊት ... ትግላችን ፍሬ አፍርቶና መብታችን ተጠብቆ መኖር እስክንጀምር ድረስ ኣማራነት define መደረግ ያለበት በተግባር እንጂ በጭራሽ በደም መሆን የለበትም ያልኩት።

Thank you so much again for the detailed comment, Brother ethiopianunity 8)

Wish you all the best

Post Reply