Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15397
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ፋኖ ከፍተኛ የሚሊታሪ እና የፓለቲካ ታሪካዊ ድል አግኝቷል። ለኦነግ-ብልጽግና ዕንቆቅልሽ ሁኖበታል - የበኩር ልጁ ብአድን እንዳይሆን ተደርጎ ተባሯል።

Post by Abere » 09 Aug 2023, 08:58

ፋኖ ከፍተኛ የሚሊታሪ እና የፓለቲካ ታሪካዊ ድል አግኝቷል። ለኦነግ-ብልጽግና ዕንቆቅልሽ ሁኖበታል - የበኩር ልጁ ብአድን እንዳይሆን ተደርጎ ተባሯል።

በአማራ ፋኖ እና በኦነግ-መከላከያ መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ህዝብ ከሚገባ በላይ የተረዳው

1ኛ) ፋኖ ከበርካታ ወራት ትግል በኋላ በአጭር ጊዜ የአማራ ዞኖችን እና ከተሞቻቸውን በብዛት በመቆጣጠር የመከላካየ ካምፓችን በማጥቃት በርካታ ወታደሮችን በመማረክ እና በመደምሰስ የተሻሉ የጦር መሳሪያዎችን በሰፊው እንድታጠቅ አድርጎታል። ይህም ፋኖ በብቃት እና በጥራት መሳሪያ በማግኘት የሚሊታሪ አቋሙን አሳድጓል። የተጠናከረ ወታደራዊ ዕዝ መስርቷል - በርካታ ብርጌዶች ተመስርተዋል። ይህን ሁሉ የፈጸመው በቀላል ኪሳራ ብቻ ነው። ከመከላከያ ጋር ሲነጻጸር ፋኖ ምንም የተነካበት የሰው ሃይል የለም - የተገደል ወይም የተማረከ መሪ የለም። በመከላከያ በኩል ግን በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ቆስለኞች በርካታ ምርኮኞች እና ቀላል የማይባሉ ዕዞች እና ብርጌዶች ተደምስሰዋል ወይም ፈርሰዋል።

2ኛ) አይነኬነኝ እያለ በአማራ ህዝብ ላይ ቀደምት ለትግሬ ወያኔ ተላላኪ አሁን ደግሞ ለኦነግ ተላላኪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን ለአልፉት 32 አመታት ግፍ ሲፈጽም የኖረው ብ አድን አሳፊሪ ውርደት በመከናነብ ከአማራ ክፍለሀገራት እንደ ህዳር ሚካኤል ቆሻሻ ተጠራርጎ ከአማራ ክልል ተወግዷል - ተባሯል። በኢትዮጵያ ደረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር ብቻ ሊጥ እንደ ደፋች ውሻ ተባርሮ ትሰድቷል። ስደተኛው በአድን የወደፊት ስም ይዟል። ይህ ከፍተኛ የፓለቲካ ድል ነው። ለሌሎች ጭቆና እና ግፍ መሯቸው ለሚታገሉ ክልል ህዝብ አርዕያ ነው። ለምሳሌ የትግራይ ህዝብ 50 አመት በወያኔ ይረገጣል እራሱን ከወያኔ በዚህ መልክ ነጻ ሊያወጣ ይችላል፤ ሌሎች ክልሎችም።ከእንግድህ በአማራ ክልል የብ አ ደን ሹም ሁኖ መስራት በህይወት እና በቤተሰብ ላይ መፍረድ ይሆናል። ብልጽግና አማራን ማስተዳደር አይደለም ከቢሮ ወጥቶ በእግሩ መመለስ የማይችልበት መቀሰፍት ተፈጥሮበታል። በአማራ ፋኖ ድል ተደርጓል።


3ኛ) ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ተሰፋ ሁኗል። ከዚህ በፊት የወያኔን ወረራ በመቀልበስ ብቃት እና ችሎታውን እንዳሳየ ዛሬ ይህ ሃይል የአገር ግብር ገንዘብ እየበላ ወታደርነኝ ከሚለው ከእርሻው ላይ ተነስቶ የሚዋጋ ገበሬ አላማ እና ጀግንነት የላቀ መሆኑን። ህዝብ ከተነሳ አንዳች ሃይልም በፊቱ መቆም እንደማይችል እያሳየ ነው። አሁን ፋኖ የሚሊታሪ ይሁን የፓለቲካ ትኩሳት ነው የግፍ ምንጭ የሆነውን የ4 ኪሎ ጨፍጫፊ እንቅልፍ ነስቶታል። የኢትዮጵያ ህዝብ መፍራት ያለበት ግፍ አለመፈጸም እንጅ ሌላ ምንም የሚያስፈራው ሃይል ሊኖር እንደማይችል ፋኖ መሪ ሁኖ እያሳየ ነው። አብይ አህመድ እና ኦሮሙማ ያለቀላቸው ጉዳይ ነው ።


4ኛ) የኢትዮጵያ መከላከያ እጅግ ደካማ፤ ከአፍሪካ በጣም ዝቀተኛ የመዋጋት ወኔ ያለው፤ ከማንኛውም የውጭ አገር ጦርነት ቢያደርግ በቀላሉ የሚሸነፍ መሆኑን ነው። ከምስራቅ አፍሪካ 1ኛ ደረጃ እየተባለ የሚወራለት በጣም አሳፋሪ ውሸት መሆኑን ነው። ጅቡቲ ወይም ደቡብ ሱዳን እንደ አገር ከባድ መሳሪያ ስለሚኖራቸው በቀላሉ ገርፈው ሊያሸንፉት የሚችል የሞተ ሰራዊት ነው። ለዚህም ሱዳንን እና ግብጽን ጫማ ላይ ወድቆ የሚለማመጠው።
አማራ ፋኖ የመከላከያ ባዶነት አጋልጧል። ይህም ኢትዮጵያ አዲስ መከላከያ የሚያስፈልጋት መሆኑን ያስመሰክራል።