ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሠጠ አስቸኳይ መግለጫ
የአማራ ሕዝብ ላለፉት ረጅም ዓመታት እንደ ሕዝብ ሲደርስበት የነበረውን መስፈሪያ-የለሽ መከራ፣ አገርና ሕዝብን ለማቆየት ሲል ስቃዩን ችሎ ሰላማዊ የለውጥ ሁኔታ ይፈጠራል በሚል ሲታገስ ቆይቷል።
ትዕግሥቱን ፍርሃት፣ ዝምታውን የተሸናፊነት፣ መንግሥት ማክበሩን እንደ አላዋቂነት ተወስዶ በመከራ ላይ መከራ ሲደራረብበት ቆይቷል። ይህ ሁሉ የአማራው ታጋሽነት የአገርን ሕልውና ከአደጋ ለመጠበቅ፣ የንጹሃን እልቂትን ለማስቀረትና በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ መፍትሄ ይገኛል ከሚል ፍጹም ስልጡንነት ነበር
ሆኖም የአብይ አህመድ የኦሮሙማ የፓለቲካ አይድዮሎጂን ተከትሎ፣ የአማራውን ሕህዝብ፣ ከክርስትናና ከሙስሊም እምነት ተከታዮች ጋራ አጥፍቶ፣ በምስራቅ አፍሪካ የኩሽ ግዛት ለመፍጠር የጀመረው የፋሺዝም የዘር ማፅዳትና የመስፋፋት ፓሊሲ ከኢትዮጵያም አልፎ በመላው አፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ ታላቅ የፀጥታ ችግር ፈጥሮ፣ ቀጠናውን የኃያላን ጦር አውድማ ሳያደርገው ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲው አስፈላጊውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
ይህ የጉግማንጉግ ሰው-በላ የአራዊት አገዛዝ ለሠላም የተዘረጋውን የሕዝባችንን እጅ ለመቁረጥ ምሳሩን መዞ እልቂትን አውጇል። ዐማራው ህልውናውን ለመከላከል ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይል ብቻ በመሆኑ ሳይወድ በግድ በጠላቶቹ ጋባዥነት ወደ ለየለት ጦርነት ውስጥ ገብቷል።
አማራ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት የአብይ አህመድ የኦሮሙማ-ኦህዴድ-ኦነግ አገዛዝን ወረራ ለመመከት በበርካታ ግንባሮች እየተፋለመ ይገኛል።
ሕዝባችን እየተፈጸመበት ያለውን መረን-የለሽ ጭፍጨፉ፣ አፈናና ግድያ ዝም ብሎ ከመመልከት ወደ ሁለገብ የተከላካይነት ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የተጋድሎው ግለትና የጦር ግንባሩ ስፋት አማራው የሚያደርገውን ትግል በበለጠ ውጤታማና አሸናፊ እንዲሆን የተቀናጀ አመራር የሚሰጥ አካል ማዋቀር አስፈልጓል።
ይህንንም የሚያቀናጅ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል።
የአማራው የተለያዩ ክፍላተ አገሮች፣ በሥራቸው የፋኖ ብርጌዶች ያሏቸው ኮማንድ ፖስቶች ሲኖሯቸው፣ እነዚህንም በበላይነት የሚያስተባብረው ጀግናው አርበኛ ሉቴናንት ኮረኔል ፉንታሁን ሙሃባ ነው።
የኮማንድ ፖስቱ ዓላማዎች፡-
ክልሉን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ለማፅዳት የተባበረና የተቀነባበረ ትግል እንዲካሄድ ማድረግ፤
ነፃ የወጡ ከተሞችን ጥበቃ እንዲኖራቸውና ሕዝባዊ አስተዳደር በማዋቀር የአገልግሎት ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ፤
ትግሉን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ኃይሎችን ማሰልጠን፣ ማስታጠቅና ለትግል ማሰማራት፤
የሎጅስቲክስ አቅርቦትን ለማሳለጥና፣ ጉዳት የደረሰባቸውን በመንከባከብ እርዳታ እንዲያገኙ ማመቻቸት፤
የጠላት ምርኮኞችንም ዓለም ዓቀፍ ህግ በሚፈቅደው መሠረት መጠብቅ፣ ተጸጽትውና ይቅርታ ጠይቀው ከወገን ጦር እንዲቀላቀሉ መሞከር፣ ወይም ወደፊት ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ።
ይህንንም ሕዝባዊ ዓላማ ለማሳካት የተቋቋሙት ኮማንድ ፖስቶችና ብርጌዶች የሚከተሉት ናቸው፡
ኮረኔል ፉንታሁን ሙሃባ አጠቃላይ የኮማንድ ፖስቶቹ የበላይ አስተባባሪ ከመሆኑም በተጨማሪ የወሎን ብርጌዶች ኮማንድ ፖስት ይመራል፡፡
ብርጌዶቹ:-
አንደኛ ብርጌድ
ሁለተኛ ብርጌድ
አሳምነው ብርጌድ-ላሊበላ
Re: የአማራ ጠቅላይ ማዘዣ! ኮማንድ ፖስት ሚያቆም መሬት ላይ የቆመ ነው!
ኢትዮጵያ የኦሮሙማ /ወያኔ ቆሻሻ ዘረኛ የድንጋይ ዘመን ስርዐት በመገላገል ላይ ነች። ትግሉ ከማይቀለበስበት ደረጃ ድርሷል። ትንሽ ትንሽ ቅንጣት የሰው ልጅ ህሌና ያላቸው በአብይ አህመድ ዙሪያ ካሉ ከዚህ በላይ ወንጀል ሳይ ፈጽም ከስልጣን እንድ ወርድ፤ፓርላማው እንድበተን ( ወንጀለኛ ፓርላማ ነው)፤ የወያኔ/ኦነግ ህገ መንግስት እንድታገድ ማድረግ ብቻ ነው።