Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ፋኖ የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን አስተዳደር ተረክቧል! አስታ ላቪስታ ኦሮሙማ!

Post by Revelations » 03 Aug 2023, 13:48

ወደ ላሊበላ እና ጎንደር ከተሞች የሚደረገው የአየር በረራ መቋረጡ ተገለጸ




ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ወደ ላሊበላ የሚደረግ የአየር በረራ መቋረጡን የላሊበላ ኤርፖርት ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ምክንያት በዛሬው ዕለት ወደ ጎንደር የሚደረግ የአየር በረራ አለመኖሩን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

ዛሬ ረፋድ ላይም በጎንደር አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ነው መረዳት የተቻለው።

የላሊበላ አየር ማረፊያ ሠራተኞች ወደ ላሊበላ በቀን ከሚደረጉ ኹለት በረራዎች የመጀመሪያው ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 ጠዋት ላይ መደረጉን ገልጸው፤ “ተጨማሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላሊበላ አየር ማረፊያ ሊገቡ ነው” የሚል ወሬ የሰሙ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ሥፍራው አቅንተው ጥበቃ ላይ ከነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ይህን ተከትሎም በኹለተኛው በረራ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ50 ላይ ላሊበላ ኤርፖርት ማረፍ የነበረበት የመንገደኞች አውሮፕላን ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር ሳያርፍ መመለሱን ገልጸዋል።

በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ከማክሰኞ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የበረራ አገልግሎት አለመኖሩ ነው የተቀሰው።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች በከተማዋና አካባቢው ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር የአየር ማረፊያው የተለያዩ መገልገያ ቅሳቁሶችን ማሸሸታቸውንም ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ጽሑፎች:



አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ለማግኘት ለተቋሙ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ብትደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር የባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማንደፍሮ ታደሰ ወደ ላሊበላ የሚደረገው የአየር በረራ መቋረጡን ገልጸው፤ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ከሰሜኑ ጦርነት እና ከኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ በኋላ እየተሻሻለ የነበረ ቢሆንም፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በ“ፋኖ” ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ምክንያት ተመልሶ መቆሙን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የቱሪዝም እንቅሳቃሴውን ወደነበረበት ለመመለስም ረዥም ጊዜ ይወስዳል ያሉት ኃላፊው፣ “አሁን ያለው የጸጥታ ችግር ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ከቱሪዝም በሚያገኘው ገቢ ራሱን ለሚያስተዳድር የላሊበላ ሕዝብ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሯል” ሲሉ ተደምጠዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ፤ ንጹሃንን ጨምሮ ከኹለቱም ተፋላሚ ኃይሎች የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊት ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 በሰጠው መግለጫ፤ በአማራ ክልል በፋኖ ሥም በሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አስታውቋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እንዲሁ ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ “ኹሉም ልዩነት ያለው አካል ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ሰላማዊ ውይይት በመመለስ፣ በየደረጃው ወደ ተቋቋመው የአገር ሽማግሌ፣ የኃይማኖት አባት፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ችግሩ እንዲፈታ መረባረብ አለበት” ብለዋል።


Horus
Senior Member+
Posts: 44063
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፋኖ የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን አስተዳደር ተረክቧል! አስታ ላቪስታ ኦሮሙማ!

Post by Horus » 03 Aug 2023, 13:56

ምን አለ በሉ?

ባህር ዳርና ደሴ ጥይት ሳይተኮስ ነው ወደ ፋኖ ሚገቡት! አቢይ አሁን ባህር ዳርን ፣ ደሴን ለመቆጣጠር ተሟሟተ እንበል! ለምን እስትራተጂክ ጥቅም? ወፍ የለም! አማራ በቀረው አገር መንግስት ሆኖ ጦር ካቆመ አቢይ 2 እና 3 ከተሞች በግዙፍ ጦር መያዙ ከንቱ ነው ። ቀድሞ ነገር በዚህ ሰዓት የከተማ ፋኖ የድርጅት መረብ ዘርግቶ ነው የሚጠብቀው !

አቢይ መካሪ ይፈልጋል?!




Right
Member+
Posts: 5110
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ፋኖ የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን አስተዳደር ተረክቧል! አስታ ላቪስታ ኦሮሙማ!

Post by Right » 03 Aug 2023, 16:35

Amhara cities are falling one by one. Bahir Dar is about to fall. There is tension and jubilation in Addis.
Honestly, I am shocked by this breathtaking and speedy transition.
Who is behind all this coordination? I was told there is even an all inclusive blue print of a transitional government.
What a turn of events. Dramatic.

eden
Senior Member
Posts: 10245
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

w

Post by eden » 09 Jul 2026, 22:31

where’s revelations these days

Misraq
Senior Member
Posts: 18397
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ፋኖ የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን አስተዳደር ተረክቧል! አስታ ላቪስታ ኦሮሙማ!

Post by Misraq » 10 Jul 2026, 17:30

ሆሩስ ይህን አላለም። ይህ AI ነው።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7771
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፋኖ የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን አስተዳደር ተረክቧል! አስታ ላቪስታ ኦሮሙማ!

Post by Naga Tuma » 11 Jul 2026, 19:51

Did you find a ቃሉ in your town who told you the Almighty works in mysterious ways.

That would be unlike the imposter from your town who tried to lecture that to think an Almighty exists is a mental disorder.

Hasn’t the knucklehead driven the island under and the Almighty resurrected the ቃሉ higher?
Right wrote:
03 Aug 2023, 16:35
Amhara cities are falling one by one. Bahir Dar is about to fall. There is tension and jubilation in Addis.
Honestly, I am shocked by this breathtaking and speedy transition.
Who is behind all this coordination? I was told there is even an all inclusive blue print of a transitional government.
What a turn of events. Dramatic.

Post Reply