sarcasm wrote: ↑16 Jul 2023, 19:01
Hi Brother Assegid, hope you had a great weekend. It seems that you have been misinformed. The Aba did not ask for protection. He said "my aim is to go to Tigray and I should go to Tigray." He refused the offer of going to Addis as he has no business going to Addis. He did not intend to visit Addis.
fast forward to 49:35
Another misinformation here again. He did
not say
ወደ መጣሁበት እመለሳለሁ. He actually said "ወደ ኣውስትራልያ ኣልመለስም". They forced him enter the plane. If you call that በደስታ ተሸኙ, then listen till the end and you will learn how he felt. Actually it was really interesting interview.
fast forward to 51:15
ሰላም ወንድም Sarcasm; የእኔ ሰንበት መልካም ነበር፤ አንተም ጥሩ የሳምንት መጨረሻ ነበርህ የሚል እምነት አለኝ።
Sarcasm ... ስለ ቪዲዮው አመሰግናለሁ።
ላለመዋሸት ግን የኣንተ recommendation ስለሆነ እንጂ የተመለከትኩት እውነትን አገኝበታለሁ ብዬ በማሰብ አይደለም። የኢትዮጵያ በተለይም የኣማራ ጥላቻን እንደ after-shave እለት ተእለት ገና ከእንቅልፉ እንደተነሳ ተቀብቶ የሚወጣን ብቻ ሳይሆን የኋላ ታሪኩ በእርግማንና ውሸት የወየበን ሰው እንዴት ማመን ይቻላል?
እኔ በግሌ እነዚህን መሳይ ሰዎች መንገድ ላይ ስሜን እስከ ቅድመ አያቴ ቢጠሩት እንኳ … ሦስት ጊዜ ካልደገሙትና ሁለት ጊዜ ካላሰብኩ በስተቀር እውነት ስሜ ነው ብዬ "አቤት" ለማለት እቸገራለሁ። አባም የሚያስተምሩት መፅሓፍ እኮ “
ተመዝኖ የቀለለ፣ ለትንሹ ያልታመነ ... ለትልቁ አይሾምም” ይላል። በነገራችን ላይ ... በተለጠፉት ቪዲዮዎች ላይ... ኣባ በተደጋጋሚ ለመዋሸት (ለማጋነን) ፈልገው ሓቅ ጉሮሯቸውን ኣንቆ ሲታገላቸው ተመልክቻለሁ።
ይሁንና ግን “’
እንኳን ደህና መጣችሁ!’ ላሉን የበረራ አስተናጋጆች የታፈንኩኝ የታሰርኩኝ የሓይማኖት መሪ
ኢትዮጵያዊ ነኝ” ብዬ ተናገርኩኝ ማለታቸው አስገርሞኛል። ከዚህ ቀደም “ማንም የትግራይ ተወላጅ ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ እንዳይል” ብለው ሲያወግዙ የሰማሁ መስሎኝ ነበር። ዛሬ እንዴትና ለምን ኢትዮጵያዊ ሆነው እራሳቸውን ለመስደብ እንደፈለጉ አልገባኝም። ሰውየው’ኮ ኢትዮጵያን “ዝሙተኛ ነች” ብለው ሲሉ … ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን ኢትዮጵያዊ የሆነውን ግለሰብ በሙሉ ነው "የኣመንዝራ ልጅ" ብለው የተሳደቡት። በራሳቸው ኣንደበት “አየር መንገዱ ውስጥ የፃም ምግብ ጠፍቶ '
የእኛን ምሳ ብሉ' ብለው መልካምነታቸውን አሳዩኝ” ያሏቸውን ሰራተኞች ጭምር ማለት ነው።
በአጠቃላይ ... ቪዲዮውን ብመለከተውም እኔ ጋር ያለውን አመለካከት ለመቀየር ግን ታማኝነት ይጎድለዋል። ይህን በልዩነት እንለፈውና፤ የትግራይ ጊዜያዊ ክልላዊ መንግስት …. በኣንተ አገላለፅ ደግሞ The Government of Tigray የፃፈው ደብዳቤ የተቀባይ አድራሻ የለውም እንዴ? ነው ወይንስ እንደ መንደር የንግድ ማስታወቂያ በየስልክ እንጨቱና በየግድግዳው ላይ የሚለጠፍ ነው? እንዲሁ ብቻ ለሚዲያ አካላት ጩኽት በጅምላ "
ሻሞ!" ተብሎ የተወረወረ በራሪ ወረቀት? ምናልባት ትግርኛ ስለሆነ ይዘቱን ስቼው ከሆነም ይቅርታ እጠይቃለሁ።
Have a great weekdays, Brother Sarcasm.