Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 28 Jun 2023, 01:41

ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረ ሰቦች ለምርቃት የሚሰጡት ጥርት ያለ፣ ቀላልና ተግባራዊ ትርጉም ምን እንደ ሆነ አላውቅም ። የቋንቋና ባህል ሊቃውንት ቁም ነገር ብለው ያጠኑት ጉዳይ አይደለም። የምርቃት ስነምግባር የሌለው ማህበረሰብ ያለ አይመስለኝ ።

በጉራጌ ባህልና የኑሮ ዘይቤ ምርቃት መሙላት ማለት ነው። ምሩቅ ነገር ሙሉ ነገር ነው ። የተመረቀ ሰው የተሟላ፣ የሞላው ሙሉ ሰው ነው። ለምሳሌ ገበያ ሄደን ወይም ሱቅ ሄደን ምንም ነገር ስንገዛ ግብይቱን ከመፈጸማችን በፊት 'መርቅ' ሻጩን መርቅ እንለዋለን! የእቃው ልክ ገና ስለአልሞላ ጨምር፣ አክል ፣ ድበል ወይም ሙላ ማለታችን ነው ።

ይህ እጅግ ጥልቅ ፍልስፍና ነው ። ማንኛውም ነገር ይፈጸም ዘንድ ሙሉ መሆን አለበት ። ሳይሞላ የተደረገ ነገር ሁሉ ጎደሎ ስለሆነ አይሳካም ፣ ፍጹም አይሆንም። ቁንጽል ይሆናል፣ ቀጫጫና የደሀየ ይሆናል ።

ችግር ለምፍትሄ የሚደርሰው እንደ ችግር ሙሉ ችግር ሲሆን ነው ። መፍትሄ እንደ መፍትሄ የሚሳካው ሙሉ መፍትሄ ሲሆን ነው ። ጠቢቡ ሰለሞን ለሁሉም ግዜ አለው ሲል ሁሉም ነገር ሙሉ የሚሆንበት ወቅት ወራት አለው ማለት ነበር።

ስለዚህ መመረቅ መሙላት፣ ሙሉ ማድረግ ፣ ፍጹም ማድረግ ማለት ነው ። ባህሉን በሚኖር የጉራጌ ቤተሰብ ሆነ ማህበር ማንኛውም ነገር ለማድረግ በምርቃት ተጀምሮ በምርቃት ይዘጋል ። መራቂው ሰው መርቆ መርቆ ከማብቃቱ በፊት እኔ ያጎደልኩት እግዚአብሄር ይሙላበት ብሎ ነው ዝም የሚለው!

ስለዚህ የሰው ልጅ መሙላት የማይችለውን ሁሉ ፈጣሪ እንዲሞላው እንሂላው እንማለዳለን ማለት ነው!!! (ወሂላ ምህላ መለመን ማለት ነው፤ ጉራጌ ሲተርት ባለነ ንበላው በሌለነ ትንሂላ ይላል። ካለን እንበላለን ከሌለን አንለምንም ማለት ነው ። )

ዛሬ ለዚህ እኩለ ሰሞን (የሳምንት እኩል) ይህን የምርቃት ትርጉም ጉራጌ በሰርግ ባህላቸው ላይ እንዴት እንደ ሚከወን ቪዲዮችን ጀባ እላችኋለሁ !!

እናንተም ምርቃት በባህላችሁ እንዴት እንደ ሚተረጎም ጀባ በሉን ! ኬር ።
Last edited by Horus on 28 Jun 2023, 03:34, edited 4 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 28 Jun 2023, 02:00

ሴት ልጅ ከሰርጓ 3 ቀን ቀድሞ እንሶስል ይታሰርላታል ። በዚያ የቤተሰብ በዓል ላይ እንስራው በጠላ ጢም ብሎ ሳይሞላ ምርቃት አይደረግም ። ያን ሞላ ወይ ወይስ አልሞላም እያሉ ጓደኞቿ የሚዘፍኑት !

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 28 Jun 2023, 02:18

በአንዲት ልጅ እንሾሽላ ለት መላ ዘመዶቿን የምታሳይበት የምሰናበትበት ምሽት እጅግ ስሜታዊ በዓል ነው !! እንሾሽላ ሲታሰረሽ የእከሌ ልጅ ነኝ በይ እየተባለ የዘመዶችውን ዝርዝር የምትጠራበት ዋናው ዘፈን ነው ።

Last edited by Horus on 28 Jun 2023, 03:19, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 28 Jun 2023, 03:12

የእንሾሽላ ዘፈን በተመለከተ ጠቅላላ ኦክሲጂኑን የሳበው የናቲ ኬር ነጠላ ነው !! እጅግ ውብ ነው!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 30 Jun 2023, 03:17

በዘመናችን አንዲት ልጃገረድ ያለ ፍቃዷ መንጠቅ፣ መጥለፍ የሚባል ባህል በመላ ጉራጌ ሴራ ተወግዞ በህግ በቅጫ የሚያስቀጣ ከፍተኛ ወንጀል ነው። ይልቅስ ዛሬ ጥንታዊው የልጅቱብ ቤተሰ ፍቃድ ለማግኘትና በጋብቻ ሁለቱን ቤተሰቦች ለማሰር ሽማግሌዎችን የመላክና የመለመን ባህል በሙሉ ክብሩ እንደ ገና ተመልፏል !!

የዚህ ፍጥምጥም ባህል ቸግ ይባላል! ጀባ ብልያችኋለሁ ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17840
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Selam/ » 30 Jun 2023, 07:27

ሆረስ - ልብ የሚያርስ ርዕስ እኮ ነው የምታመጣው።

እንደ ኢትዮጵያ እኮ በዖሪት ስርዐት የታረቀ ህዝብ የትም የለም። እግዚአብሄር ዓለምን በፈጠረ በአምስተኛው ቀን፣ አዕዋፋቱንና የውሃ ውስጥ ፍጥረቶችን ባረከ። በዚህም ተያያዥነት እኛ የእርሱ ልጆች፣ ሰው ሲፀነስ ጀምሮ እንባርካለን፣ ከሌሎች ህዝቦች በተለየ ሁኔታም እንመርቃለን። ሁለቱም ቃላቶች ተመሳሳይ ፅንሰ ሀሳብ ቢይዙም ፣ ምርቃት በየዕለቱ ከምናደርገው ኑሮ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል። መባረክ ማለት ከእግዚአብሄር ፀጋን ፣ ደግነት፣ ምኅረት መጠየቅና ማግኘት ማለት ነው። ለዚህም ሰዎች አዘውትረው እግዚአብሄር ይባርክሽ / ይባርክህ ይላሉ።

መመረቅ ማለት እንዳልከው መጨመርና መሙላት ማለት ነው። የሚገርመው እኮ፣ ምርቃት ጠያቂውና አግኝው ብቻ ሳይሆን መሞላትን የሚሻው፣ መራቂውም በመመረቁ የመሞላት በረከትን እንደሚያገኝ ያምናል። የማይመርቅ ባለሱቅ እንደ ንፉግ ይቅጠራል፣ ሲያጣና ሲነጣ እንጂ ሲበለፅግም አይታይም። ልጆች አዛውንቶችን መርቁኝ ሲሉ፣ ጎዶሎ ነኝና ሙሉኝ ማለታቸው ነው። ይኼ አንተ እንዳልከው ነፍሴን የሚያነዝር ዩኒክ የኢትዮጵያ ባህል ነው።

ውሻው አብይ እንኳን ፣ ጎዶሎ ነኝና መርቁኝ እያለ በየመንደሩ ይዞር ነበር። ግን ዞሮ ዞሮ ማታ ቤቱ ሲገባ ምርቃቱ ተሟጦ አልቆበት የአዛውኝቶቹን ቤት ማፍረስ ይጀምራል። በረከትና ምርቃት የሌለው ሰው ደግሞ የትም ቦታ ክብር የለውም፣ ሰላምም አያገኝም። እንደ አበደ ውሻ በዮኤስ ኤይድና ብሬክስ ቂጥ ስር እያለከለከ ይኖራል።

Horus wrote:
28 Jun 2023, 01:41
ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረ ሰቦች ለምርቃት የሚሰጡት ጥርት ያለ፣ ቀላልና ተግባራዊ ትርጉም ምን እንደ ሆነ አላውቅም ። የቋንቋና ባህል ሊቃውንት ቁም ነገር ብለው ያጠኑት ጉዳይ አይደለም። የምርቃት ስነምግባር የሌለው ማህበረሰብ ያለ አይመስለኝ ።

በጉራጌ ባህልና የኑሮ ዘይቤ ምርቃት መሙላት ማለት ነው። ምሩቅ ነገር ሙሉ ነገር ነው ። የተመረቀ ሰው የተሟላ፣ የሞላው ሙሉ ሰው ነው። ለምሳሌ ገበያ ሄደን ወይም ሱቅ ሄደን ምንም ነገር ስንገዛ ግብይቱን ከመፈጸማችን በፊት 'መርቅ' ሻጩን መርቅ እንለዋለን! የእቃው ልክ ገና ስለአልሞላ ጨምር፣ አክል ፣ ድበል ወይም ሙላ ማለታችን ነው ።

ይህ እጅግ ጥልቅ ፍልስፍና ነው ። ማንኛውም ነገር ይፈጸም ዘንድ ሙሉ መሆን አለበት ። ሳይሞላ የተደረገ ነገር ሁሉ ጎደሎ ስለሆነ አይሳካም ፣ ፍጹም አይሆንም። ቁንጽል ይሆናል፣ ቀጫጫና የደሀየ ይሆናል ።

ችግር ለምፍትሄ የሚደርሰው እንደ ችግር ሙሉ ችግር ሲሆን ነው ። መፍትሄ እንደ መፍትሄ የሚሳካው ሙሉ መፍትሄ ሲሆን ነው ። ጠቢቡ ሰለሞን ለሁሉም ግዜ አለው ሲል ሁሉም ነገር ሙሉ የሚሆንበት ወቅት ወራት አለው ማለት ነበር።

ስለዚህ መመረቅ መሙላት፣ ሙሉ ማድረግ ፣ ፍጹም ማድረግ ማለት ነው ። ባህሉን በሚኖር የጉራጌ ቤተሰብ ሆነ ማህበር ማንኛውም ነገር ለማድረግ በምርቃት ተጀምሮ በምርቃት ይዘጋል ። መራቂው ሰው መርቆ መርቆ ከማብቃቱ በፊት እኔ ያጎደልኩት እግዚአብሄር ይሙላበት ብሎ ነው ዝም የሚለው!

ስለዚህ የሰው ልጅ መሙላት የማይችለውን ሁሉ ፈጣሪ እንዲሞላው እንሂላው እንማለዳለን ማለት ነው!!! (ወሂላ ምህላ መለመን ማለት ነው፤ ጉራጌ ሲተርት ባለነ ንበላው በሌለነ ትንሂላ ይላል። ካለን እንበላለን ከሌለን አንለምንም ማለት ነው ። )

ዛሬ ለዚህ እኩለ ሰሞን (የሳምንት እኩል) ይህን የምርቃት ትርጉም ጉራጌ በሰርግ ባህላቸው ላይ እንዴት እንደ ሚከወን ቪዲዮችን ጀባ እላችኋለሁ !!

እናንተም ምርቃት በባህላችሁ እንዴት እንደ ሚተረጎም ጀባ በሉን ! ኬር ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሞላም? አልሞላ ፤ አሁ ሞላም! የሙሊተ ነገር ምስጢር !!

Post by Horus » 30 Jun 2023, 14:20

Selam/ wrote:
30 Jun 2023, 07:27

Selam,
እንዲያውም ምርቃትና ባርኮት አንድ መሆን ብቻ ሳይሆን በእኔ እምነት ባርኮት ከምርቃት ይጠነክራል ። ባርኮት (መባረክ) በቃሉ ፊሎሎጂና ስረ ቃል ደረጃ አንድ ናቸው ። በ/መ +ረ/ረ + ከ/ቅ!! ባረከ እጅግ ጥንታዊና ግአዝ ነው ። መረቀ አገውኛ (ቀ) የገባበት አማርኛ ነው ። ይህ ብቻ ነው ልዩነቱ ።

ባርኮት የበለጠ ጠንካራ ያልኩበት ምክኛት ምርቃት ሙሉነት (ሆልነስ) ሲሆን በረከት ሞላ ብቻ ሳሆን በዛ የማያልቅ ፕሌንቲ ሆነ ማለት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም ፤ለብዙ ግዜ የለበስነው ልብስ በረከተልኝ ይባላል። ረጅም እድሜ ያለው ነገር ብሩክ ነገር ነው ። ስለዚህ በማደግና በማበብ ደረጃ ሙሉ መሆን ብቻ ሳይሆን መባረክ የማያልቅ መሆን ፣ ነዋሪ መሆን ፣ ከራሚ መሆን ስለሚጨምር ነው ። ባርኮት ከምርቃት ይልቃል ብዬ የማስበው ።

ሁለቱም የህዝባችንን ድንቅ፣ ጥልቅና ታሪካዊ መንፈሳዊነት እና የፈጣሪ ሕዝብነት ምስክሮች ናቸው። የዛሬ መሪዎች ይህን ዘላለማዊ ካልቸር የሰጡንን ወላጆች በማጣጣል የራሳቸውን ያልበሰለ ኢመንፈሳዊ የተረገመ፣ ያልተመረቀ፣ ያልተባረከ ባህሪያቸው በታላቁ ሕዝባችን ላይ በማጨማለቅ ግዜያዊ መከራ ቢፈጥሩም ይህም ያልፋል ። ያልተባረከ ነገር ሁሉ አይበረክትም፣ ያልቃል፣ በቶሎ ይጠፋል ይሞታል ።

ኬር!

Post Reply