Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

ጥሩ ቀውስን በጭራሽ እንዲባክን አትፍቀድ

Post by TGAA » 28 Jun 2023, 00:46

Never let a good crisis go to waste

አብይ ቀውስ እየፈጠረ ያለው በእቅድ ነው ፤ ኢትዮጵያን እርሱና የርሱ አባጃግሬዎች ወደሚፈልጉት የኦሮሙማ መንግስት ለመቀየር ቀውስ እንዲጨምር እንጂ እንዲቀንስ አይፈልግም ፤ አብይ እንደውሻ የሚያክለፈልፈው በአጭር ግዜ ዘመናት የሚሻገር ለውጥ ማምጣት እችላለሁ ብሎ ነው ፡፡ አብይ ቀጥሮ ከሚያሰራቸው ዩቲዩበሮች ፤ በትንሽ ቦታና ከሚሸነግላቸው ሆዳሞች ፤ ጨምሮ ተላላ " የብልጽግና ወንጌል ሰባኪዎች ፤ አእምሯቸውን ሸጠው የእልፍኝ አሽከር የሆኑ ፖለቲከኞች ሁሉ የአብይ የቀውስ ማራብያ መሳሪያዎች ናቸው ፤ እነዚህ የቀውስ አጫፋሪዎች ሌላው ህዝብ ቆርጦ እንዳይታገል ለአብይ ምክንያት ሰጪዎች ፤ =እድሜ አራዛሚዎች ናቸው ፤ ከፊታቸው መታረደን ፤ ከ700 ሺህ በላይ ጎረቤቶቻቸው ቤት ሲደረመስባችው አሁንም ተስፋ እንዳለ እያስመሰሉ አብይ የበለጠ ጊዚ እየሰጡ የዚህን አረመኔ ዘመን ያራዝማሉ ፤ ግን አብይ ከመዝረክረኩ የተነሳ የማይነኩ ነግሮችን ነካከቶ አሁን በአንድ እግሩ ቆሟል ፤ የዛሬ አመት አብይ አይኖርም ፡
የማይነኩ የነካቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን
የኢትዮጵያን ሙስሊም አማኞችን
አማራ ጭፍጨፋን እያጠነከረ መሄዱ
አሁን ጭራሹንም ጦሩን ሰብቆ አማራን የማጥፋት ዘመቻ ጀመረ
አሁን አብይ መታጠፍያ ጊዜም ቦታም የለውም ስለዚህ ይህ ቀውስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘለቄታ ሰላም ፤ ዲሞክራሲ ፤ ፍትህ ፤ነጻነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ማምጣት መቻል አለበት ፤
አማራ ይህንን ቀውስ ተጠቅሞ በአጭር ግዜ ውስጥ የአማራ ጥያቄ እንዲመለስ ማድረግ የሚያስችል ቁመና መድረስ አለበት
ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በማቀረብ ምን አይነት ኢትዮጵያ መመስረት እንዳለበት መመካከርና አንድ የሆነ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ አለበት
አብይ ከስልጣን መውረድ እንጂ ተደራድሮ ስልጣኑ ላይ መኖር የለበትም: የአብይ ቀውስ በጭራሽ መባከን የለበትም፡፡
Time is of the essence"

Horus
Senior Member+
Posts: 42741
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጥሩ ቀውስን በጭራሽ እንዲባክን አትፍቀድ

Post by Horus » 28 Jun 2023, 01:16

TGAA
የተጨቋኝ ንቃተ ህሊና የሚያድገው በሁለት ደረጃ ነው ፤ መጀመሪያ መጨቆኑን መበደሉን ያውቃል፣ ይመረዋል ። ዛሬ ላይ ዘይትና ቲማቲም መግዛት ካቃታት እናት በክልል አትኖርም እስከ ተባለ ጳጳስ በደሉን እያወቀ ነው ።

አሁን ላይ ገና ያልበሰለው ንቃተ አለም የዚህ ሁሉ መከራ ምንጭ የሆነውን ስርዓት ለማሻሻል ወይም ለማስወገድ አንድ ነገር መደረግ አለበት የሚለው ንቃት ነው ገና ያልገነነው ።

ስለዚህ ከላይ ያልከው ቀውስ ወይም የክራይሲስ ዋንጫ ገና አልሞላም ። አንድ ትልቅ ሾክ ነውጥ ርዕደ ሕይወት ሲከሰት ነው ሕዝብ ነቅሎ የሚወጣው !

Post Reply