Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 09:56

Yayesew Shimelis

·
ከሞት የማምለጥ ሽሽት
----
ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ካለቀበትና ሞት መንግሥታዊ አዋጅ ሆኖ በየደቂቃው ከሚከሰትበት አገር መውጣት መታደል ሊመስል ይችላል፡፡ ሰዎቹ የጭካኔያቸውን አጽናፍ ለማሳየት ሁሉንም ዓይነት ክፋት አሳይተዋል፡፡ የፈፀሙት ክፉ ነገር ዕልፍ ነው፤ የተነገረው ግን ጥቂት ነው፡፡ በጣም ጥቂት!
ለምሳሌ ሌሊት የቤቴን በር ሰብረው ገብተው በጭምብል ሸፍነው የሆነ የማላውቀው ቦታ ውስጥ ወስደው ከአስከሬን ጋር እስኪያስሩኝ ድረስ እንዲህ እንደሚያደርጉ አላውቅም ነበር፡፡ እባብ ገድለው በማስገባት፣ ዓይጦችና እንሽላሊቶች በሚርመሰመሱበት፣ የምንጭ ውሃ በሚፈልቅበት ቀዝቃዛ ቤት ውስጥ አስገብተው እስከሚዘጉብኝ ድረስ እንዲህ ያሉ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ ከእኔ የሚፈልጉትን ለማግኘት አጠገቤ አምጥተው የሰው አካል እያጎደሉ ሲመረምሩ እስከማይ ድረስ እንዲህ ያለውን ታሪክ የማውቀው በመፃሕፍት ብቻ ነበር ፡፡ ይህንን ሁሉ አድርገው ‹‹ያደረግንህን አንዷን እንኳን ብትናገር ገድለን ለጅብ እንሰጥሃለን›› ብለው በሌሊት ጫካ ውስጥ ጥለውኝ ሲሄዱም አውሬነታቸውን አላውቅም ነበር፡፡
በርግጥ እንዲህ ብሎ ማውራት ቅንጦት ነው፡፡ ሰዎችን ከተራራ አናት ላይ ሆኖ እየገደለ ወደ ሸለቆ የሚጨምር ሠራዊት በተሰማራበት፣ ሰዎችን ከነነፍሳቸው አቃጥሎ ቪዲዮ የሚቀርጽ መንግሥታዊ ጦር ባለበት፣ ንፁሃንን ገድሎ በግሬደር የሚቀብር አገዛዝ ባለበት፣በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሴቶች እንዲደፈሩ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ‹‹በወንድ አካል እኮ ነው የተደፈሩት›› የሚል ጠቅላይሚኒስትር ባለበት፣ ‹‹ኧረ ሕዝብ አለቀ፤አትግደለን›› ተብሎ ሲጠየቅ፣‹‹ሞት አታዳንቁ፤ሞት የሌለበት አገር የለም›› የሚል ደመቀዝቃዛ መሪ ባለበት፣ ሚሊዮኖችን ለመጨፍጨፍ ‹‹ወጣቶች ያልቃሉ፣እናቶች ያለቅሳሉ›› ብሎ የጦርነት ነጋሪት የሚጎስም ጠቅላይሚኒስትር ባለበት አገር… በግል ይሄን ተበደልሁ፣እንዲህ ተደረግሁ ማለት ነውርም፤ቅንጦትም ነው፡፡
ከአስከሬን ጋር ያሰሩኝ ሰዎች እኔንም ሬሳ ማድረግ እንደሚችሉ እየነገሩኝ ነበር፤አካል እያጎደሉ ሲመረምሩኝ እኔንም እንደዛው እንደሚያደርጉኝ እየጠቆሙኝ ነበር፡፡ ስለዚህ እኔ አስከሬንም ሳልሆን፣ አካሌም ሳይጎድል፣ ከነተሟላ ጤንነቴ ነው የወጣሁት፡፡ የእኔ ነፍስ የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ከጨፈጨፋቸውና ካስጨፈጨፋቸው ሚሊዮኖች አይበልጥም፡፡ ዜጎችን የእምነት ቤታቸውንም የመኖሪያ ጎጇቸውንም አፍርሶ ‹‹ሕጋዊ ድሃ አደረግኋችሁ›› እያለ በመመፃደቅ የራሱን ቤተመንግሥት ግን በትሪሊዮን ብር ለመገንባት ዓይኑን የማያሽ፣ የሙያ አጋሮቼን በሥራቸው ምክንያት አጉሮ ሰበር ዜና የሚያስነግር፣ ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከት እያፈነ የሚሰውር፣ ሚሊዮኖችን ከሚሊየነርነት ወደ ለማኝነት ቀይሮ ኑሮን ሰማይ ጠቀስ ያደረገ አገዛዝ 120 ሚሊዮኖችን አስሮ ባለበት ሁኔታ በግሌ የደረሰብኝን ሁሉ መዘርዘር አልፈልግም፡፡ ከሞቱትና አካላቸውን ካጡት፣ ደብዛቸው ከጠፋና ታግተው ከተሰወሩት፣ ከተገደሉትና ለአእምሮ ሕመም ከተዳረጉት አንፃር እኔ ምን ሆንኩና!
ስደት እንዳያጋጥመኝ ስፀልይባቸው ከነበሩት የሕይወት ምዕራፎች አንዱ ነው፡፡
በአገሬ ሰርቼ ኑሮዬን ማሸነፍ እንደምችል አውቃለሁ፡፡ተሳክቶልኝም ለራሴ ሳላንስ አይቼዋለሁ፡፡ መንግስትን ግን ማሸነፍ አቃተኝ። እናም በምወዳት አገሬ ከምወዳቸው ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር መኖርን እንጂ መሰደድን ተመኝቼ አላውቅም፡፡ ሌላው ቀርቶ ስድስት ጊዜ እየታሰርሁ ስፈታ አንድም ጊዜ ስለመሰደድ አስቤ አላውቅም፡፡ በሰባተኛው ግን ወሰንሁ፡፡ ያንን ሁሉ ነገር እያደረጉ ሲያሳዩኝ ከርመው ጫካ ውስጥ አምጥተው ሲጥሉኝ ‹‹ካየኸው ሁሉ አንዷን ብትናገር ገድለን ለጅብ እንሰጥሃለን›› ሲሉኝ ወሰንኩ! በናዚ መፃሕፍት ላይ እንኳን ያላነበብሁትን ግፍ ሲፈጽሙ ካየሁ በኋላ መሰደድን መረጥሁ፡፡ ሰዎቹ በድለውህም በደልህን እንድትናገር አይፈቅዱልህም!
ሚሊዮኖችን በሁሉም ዓይነት የአገዳደል ዓይነት እያረገፈ ያለ መንግሥት፣የራሱ አልበቃ ብሎት በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች የአገርን ሕዝብ ያስጨረሰና እያሰጨረሰ ያለ አገዛዝ ካለበት አገር መውጣት ከአንድ ግዙፍ እስር ቤት ወይም የግድያ ማዕከል አምልጦ እንደመውጣት ነው፡፡
በርግጥም አምልጦ መውጣት ነው፡፡ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደየትኛውም የዓለምም ሆነ የኢትዮጵያ ክፍል እንዳልጓዝ ሲከለክሉኝ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠሩትን የዐቢይ አሕመድ አጋቾች አምልጩ ሞምባሳ ለመግባት ሰኔ 4/2015 ተነሳሁ፡፡ የመጣው ይምጣ ብዬ ኤርፖርት ደረስሁ፡፡ የፈራሁት አልቀረም፡፡ ‹‹ሞምባሳ ለመሄድ የተነሳኸው ለዘገባ ነው፤አትሔድም›› አሉኝ፡፡ ‹‹የምሔደው ለሰርግ ነው፤ሥራ ካስቆማችሁኝ አንድ ዓመት ሆነኝኮ፤እንዴት ለዘገባ እሄዳለሁ›› ብዬ ድርቅ አልኩ፡፡ አልተሳካም፡፡ ፓስፖርቴንም፣ሞባይሌንም፣በጠቅላላ የጉዞ ሰነዴን ነጠቁኝ፡፡ ሞምባሳን የመረጥሁት ለሰርግ እሄዳለሁ ብዬ ለመሸወድ እንዲያግዘኝና እነሱን ለማሳመን ነበር፡፡
ከረዥም ቆይታ በኋላ እንደገና ተመልሰው መጥተው፣የምሄደበት ሰርግ የማን እንደሆነ፣ሙሽሮቹን የማውቃቸው የትና መቼ እንደነበር፣ መቼ እንደምመለስ፣ የሰርግ ጥሪ ካርድ ስለመያዜ ወዘተ ጠይቀው ከአድካሚ ጭቅጭቅ በኋላ ‹‹ባትመለስ ግን ወዮልህ›› ብለው ሸኙኝ፡፡
አውሮፕላኑ ሞምባሳ እስከሚያርፍ ድረስ አላመንኩም ነበር፡፡ ሆነ! ከኬኒያ ሞምባሳ በናይሮቢ አድርጌ በየብስና በአየር ተጉዤ ቢያንስ የዐቢይ አሕመድና ታዛዦቹ ጥርሶች ከማይደርሱበት ቦታ ደርሻለሁ፡፡ አሁንም ጉዞው ይቀጥላል፡፡
ከምወዳቸው ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ የነጠሉኝ ጉዶች አሁን የማፈቅረውን ሥራዬን መንጠቅ አይችሉም፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ካያለንበት ቦታ ሆነን ጣቢያችን ኢትዮፎረምን ወደ ሥራ እናስመልሳለን፡፡ ምናልባትም በመጪዎቹ ቀናት ወደምንወደው ሥራችን እንመለሳለን፡፡
ከኬኒያ አስወጥታችሁ አሁን ወዳለሁበትና ነገም ወደምጓዝበት አገር እንድሄድ የተባበራችሁኝ ዓለማቀፍ ተቋማት፣ ቪዛ እንዳገኝ ያደረጋችሁልኝ መንግሥታት፣ከብልጽግናው አገዛዝ የግድያ ማዕከል ወጥቼ እዚህ እንድደርስ የተባበራችሁ ግለሰቦች ውለታችሁ አለብኝ፡፡ እጅግ አመሰግናችኋለሁ!🙏🙏

Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 11:06

This tragedy will come to an end very soon. Abiye Ahmed Ali just like the one before him will try to stop the tide by Torture and killings, but it won’t work.

The suffering will not end with the departure of the PP government, unless Ethiopians are organized and work on the alternatives.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Sam Ebalalehu » 22 Jun 2023, 11:45

ጋዜጠኛ ከካድሬ የተለየ መሆን አለበት። ፅሁፉ እውነት ማሽተት አለበት። ከስሜታዊነት የፀዳ መሆን አለበት። ይህ ፅሁፍ በካድሬ የተፃፈ ነው የሚመስለው። ያውም ያልተገራ ካድሪ። አንዱ አረፍተነገሩ እንዲህ ይላል -- " ሚሊዮኖችን ከ ሚሊየነርነት ወደ ለማኝነት ቀይሮ"
አቢይ መሆኑ ነው ቀያሪው። እንኳን መናጢ ደሀ አገር ኢትዮጵያ አሜሪካም ሚሊዮኖች ሚሊየነር የላትም።
በአጠቃላይ ፅሁፉ የማጋነን በሽታ አለበት።

Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 13:03

Unfortunately you may have probably been conditioned to value everything in US dollars. As many Ethiopians including the PM do you compare USA with Ethiopia in many things. I have no idea, why the US is a measuring stick for Ethiopians.

A million Birr is not a lot of money in today’s Ethiopia. All those houses demolished in Addis, thy are all valued over a million Birr. It is extremely hard to buy a sub standard condo under 3 million Birr in today’s Ethiopia.
The thousands of houses and assets burned by the PP invading army in the Amahara region and the many houses demolished by the Tigray war are estimated in billions of birrs.

If you want to defend Abiye Ahmed at the expense of the victims of torture and killings that is your prerogative but the writer is absolutely correct in his assessment of the situation in Ethiopia. Being a victim of Abiye Ahmed Ali himself, I believe he described it well.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Sam Ebalalehu » 22 Jun 2023, 13:24

ለነገሩ ለአንተ ፅሁፉ ይጥምሀል። የ ህወሓትን አላማ በተዘዋዋሪ መንገድ ይረዳል። ጋዜጠኝነት የተከበረ ሙያ ነው። ሙያው ክብረቱን የሚሸምተው ሙያውን የሚተግብሩት ሰዎች ለ እውነት ትልቅ ዋጋ ስለሚከፉሉ ነው። ይህ ጋዜጠኛ አንተ እዚህ ER ላይ ተጥደህ ከምትፅፈው አሉባልታ የተለየ ምን ነገር ነገረን። በማጋነን ከአንተም የላቀ ነው።
የማይያያዝ ነገር አንድ ለማድረግ አትሞክር። እኔ ስለ አቢይ አይደለም የፃፉኩት። የ ፃፉኩት ስለጋዜጠኛው አሉባልታ ነው። ስለዛ አንድ የማይረባ አሳብ ሰንዘርሀል። በገዛ ስልጣንህ መላ ኢትዮጵያን ሚሊየነር ልታረግ የተነሳህ ትመስላለህ። በአንተ ሂሳብ መሰረት የ ኢትዮጵያ ገንዘብ ባሽቆለቆለ ቁጥር ብዙ ኢትዮጵያኖች ሚሊዪነሮች ይወለዳሉ። ዘይገርም ነው ሊባል የሚችለው።

Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 14:32

You are stepping out of line. You are accusing me of being an ER regular, ok what about you? Remember I am capable of giving it to you.
You are trying to demean a respected writer for what he has gone through in order to defend a naked criminal. If you don’t like to read it and don’t want to believe it then stop reading it. Whining is not going to help you.

Back to the point, explain why the US (the most powerful and richest country in the world) is your measuring stick to dysfunctional Ethiopia? How do you know that the US doesn’t have one million millionaires in terms Ethiopian Birr? Dedeb.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Sam Ebalalehu » 22 Jun 2023, 15:35

የተከበረ ጋዜጠኛ አልክ። እኔ እንዳልከው አላላቅስም። ለመጀመሪያ ግዜ ነው የ " ጋዜጠኛውን" ፅሁፍ ሳነብ ምናልባትም የመጨረሻየ ነው የሚሆነው።
እኔ አሜሪካ የ ኢትዮጵያን ሁኔታ ለመመዘን መለኪያ ነው አላልኩም። እንደአብዛኛው ካድሪ ያልተፃፈ ማንበብ ትችልበታለህ። በነገራችን ላይ ሚሊየነሮችና ሚሊየነር ልዩነት አለው።
አውቃለሁ አማርኛ የአፍ መፉቻህ አይደለም። ልዩነት እንዳለው መጠቆም አስፈላጊ ነው።
እኔ የአቢይ አገዛዝ እንደ አጎቶችህ እስረኛ አላሰቃየም አላልኩም። ስለዛ ያልኩት ነገር የለም። በፅሁፊ ለመግለፅ የሞከርኩት ፅሁፉ የተጻፈው እንደ አንተ አይነቱን ካድሪ እሳቤ አርጎ ነው። ለአስተዋዩ ፣ ማመዛዘን የሚችለውን የኢትዮጵያ ህዝብ እሳቤ አድርጎ አይደለም ነው። ካድሪ እንደዛ ቢፅፉ አይገርምም። ጋዜጠኛ ግን በጣም።
ደጋግመህ እንደፃፉከው ዛሪ ያንን ፅሁፍ በማንበብ አንድ ደጋፊ አቢይ ያጣል ብለህ ካሰብክ ከገመትኩት በላይ ደንቆሮ ነህ ማለት ነው።
ከ ዘጠና ፐርሰንት በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ፓለቲከኛ አይደለም። የእለት ኑሮውን ለመምራት ሌተቀን የሚለፋ ህዝብ ነው። ለእንደዚህ አይነት ፅሁፉ ዋጋ ይሰጣል ብለህ ካመንክ አወ የለየህ ... ነህ።

ZEMEN
Member
Posts: 2635
Joined: 27 Jun 2011, 14:37

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by ZEMEN » 22 Jun 2023, 16:27

Sam Ebalalehu wrote:
22 Jun 2023, 13:24
ለነገሩ ለአንተ ፅሁፉ ይጥምሀል። የ ህወሓትን አላማ በተዘዋዋሪ መንገድ ይረዳል። ጋዜጠኝነት የተከበረ ሙያ ነው። ሙያው ክብረቱን የሚሸምተው ሙያውን የሚተግብሩት ሰዎች ለ እውነት ትልቅ ዋጋ ስለሚከፉሉ ነው። ይህ ጋዜጠኛ አንተ እዚህ ER ላይ ተጥደህ ከምትፅፈው አሉባልታ የተለየ ምን ነገር ነገረን። በማጋነን ከአንተም የላቀ ነው።
የማይያያዝ ነገር አንድ ለማድረግ አትሞክር። እኔ ስለ አቢይ አይደለም የፃፉኩት። የ ፃፉኩት ስለጋዜጠኛው አሉባልታ ነው። ስለዛ አንድ የማይረባ አሳብ ሰንዘርሀል። በገዛ ስልጣንህ መላ ኢትዮጵያን ሚሊየነር ልታረግ የተነሳህ ትመስላለህ። በአንተ ሂሳብ መሰረት የ ኢትዮጵያ ገንዘብ ባሽቆለቆለ ቁጥር ብዙ ኢትዮጵያኖች ሚሊዪነሮች ይወለዳሉ። ዘይገርም ነው ሊባል የሚችለው።
The guy is disgraceful and shameful so-called journalist. He sucked so hard TPLF's D!!ck, his mouth hurts. He was getting paid 130 thousands of Birr in a month while in Tigray and reporting from Tigray in behalf of TPLF. Whatever, the Abiy government did to him, he deserves it. They should have finished him while they got him. He is morally disgraceful. What is worst, he thinks people will give a hoot about him. No, one cares and go kill yourself. A-hole.

Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 16:29

Dedeb Askari. If you have respect to yourself you won’t have wasted your time in Ethiopian affairs.
Who cares if you have read the article one time or several times. Cadre? You are spitting all over the place in defending a tribal goon behalf of the Eris community and yet you have no shame calling others cadre.

What the journalist described is exactly what is happening in Ethiopia. And shove that statistics of “the US doesn’t have one million millionaires” in your [deleted]. Next time think before you comment.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Sam Ebalalehu » 22 Jun 2023, 16:47

አሁን ደሞ ኤርትራዊ ሆንኩ። የህወሓት ካድሬዎች በደንብ የሚያቃችሁ ሰው ስታገኙ የኤርትራን ካርድ ትመዛላችሁ። የተበላ ቁማር።

Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Right » 22 Jun 2023, 16:53

Eritrea is broke and unable to pay Ethiopian Airlines in hard currency.
You have a cash cow in Abiye Ahmed Ali. Kiss his [deleted] until the border is closed and start kidney selling.

Long live the Republic of Afar.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Journalist Yayesew Shimelese, Torture Chamber, in his own words.

Post by Sam Ebalalehu » 22 Jun 2023, 17:11

kissing a.. is the very and probably sole property of TPLF and its cadres. The Eritreans, especially their leader, are the very opposite of that.
You are still sucking up to the Americans. Aratkilo is a faded dream, but not Welkayet. For that dream to exist you keep sucking up for no use because it is the residents of Welkayet who will have the final say on the matter.

Post Reply