ያራዳ ልጆች ወግ፣ በኦሮሙማ ወኦነግ ቁ 1
ሴኮ: “ማርሽል መሆን አማረኝ!”
ሰያው: “ም’ ነካህ?!ሃምሳ አለቃ !”
“ምን ያንሰኛል?እ!”
“ክራይቴርያውን አታሟላማ!”
“እኔም ምርኮኛ ነበርኩ!”
“እሺ! “
እኔም ሲጋራ በላዩ በላዩ እለኩሳለሁ! በአለባበሴም አንተ እግዚአብሔር ይስጥህ እንጅ ‘ሱሪው ጅል ‘ ‘ማእረጉ ተንጠልጥሎ ሊወድቅ ነው ብሎ እግረኛ የሚከተለው’ አስብለሕ እያዘበትክበኝ ነው።”
“ሌላስ?”
“ሌላማ? አዎ ሌላማ ትህነግ ለጭፍጨፋ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት ከአዛዥ እየተቀበልኩ በሬድዮ ሳስተላልፍ ስለነበር ሰሚ እንዳልተገኘ ሳውቅ እቃየን ጠቅልዬ ተዘጋጀሁ።ወዲያው ክዋ ስትል ወደ ኤርትራ ተሸበለልኩ።”
“ይህ ሁሉ ትረካ ክራይተሪያውን እንድታሟል አያደርግህም።”
“ምን ጎደለኝ ? አወ! አሁን ገባኝ! ኦሮሞ አይደለህም ልትል ነው? !”
“አንተ ከጭፍጨፋ የተረፍክ እንጅ አንድ ዕዝ ሙሉ ያስጨፈጨፍክ፣ዞረህ ደግሞ ከጨፈጨፉት ጋር በፍቅርን ሲጋራ እየተወጋጋህ ውስኪ የማትራጭ ስለሆንክ በእኔ በኩል የቀድሞ ምርኮኛ መሆንህን ጠቅሰህ ፊልድማርሻልነት ይገባኛል ያልክበት ማመልከቻ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመልሷል!!”
“እንዴ የይግባኝ መብተሳ!”
“እሱን ሌላ የሚጨፈጨፍ ዕዝ ሲዘጋጅ ድጋሚ የሚታይ ይሆናል! አብይ እስካለ ተስፋ አለህ!!! ”