Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 4808
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

EZEMA blasted the PP government for stealing food aid. Report.

Post by Right » 16 Jun 2023, 07:51

መንግሥት ከታረዙ ዜጎች ጉሮሮ የሚነጥቀው ሰብዓዊ እርዳታ ሃገራችን ያለችበትን የከፋ የሌብነት፣ ሙስና እና ኢ-ሰብዓዊነት ደረጃ የሚያሳይ ነው!!
June 16, 2023

መንግሥት ከታረዙ ዜጎች ጉሮሮ የሚነጥቀው ሰብዓዊ እርዳታ ሃገራችን ያለችበትን የከፋ የሌብነት፣ ሙስና እና ኢ-ሰብዓዊነት ደረጃ የሚያሳይ ነው!!

ፓርቲያችን ኢዜማ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያላስከበረች ሀገር በዚህ ተደጋጋፊ (interdependent) ዓለም ሌሎች ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ያለተጽዕኖ መወሠን እንደማትችል ጠንቅቆ ይረዳል። ይህን መቅረፍ የሚቻለውም ያለውን ትክክለኛ ችግር ለይቶ ዘላቂ የሆነ የፖሊሲ አቅጣጫ ሲቀመጥ እና ተግባራዊ ሲሆን ብቻ እንደሆነ መንግሥት እስካልተረዳ ድረስ ችግሩን መራራ እና ረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንደሚያደርገው ቅንጣት ጥርጥር የለውም፡፡

ሀገራችን እራሷን መሠረታዊ የሆነውን የምግብ ፍጆታ በበቂ ሁኔታ መሸፈን አቅቷት በውጪ ሃገራት ድጋፍ የዜጎቿን ጉርስ ማሟላት ከጀመረች ቆየት ብላለች፡፡ ይህ የተረጂነት መንፈስ የሚፈጥረው የመንፈስ ስብራት እንዳለ ሆኖ በባሰ መልኩ ለዜጎች መዋል የነበረበትን ፍጆታ ለግል ጥቅም ማዋል ባስ ሲልም በአደባባይ ለሽያጭ ማቅረብ፣ የተጋነነ የተረጂዎችን ቁጥር በማቅረብ በሌሉ ሰዎች ስም እርዳታን መቀበል እና የእርዳታው ተጠቃሚዎችን ከተተመነላቸው ድጋፍ በታች በመስጠት ትርፍን መውሰድ አይነት አሳፋሪ ተግባሮች ሲፈጸሙ ይስተዋላል፡፡

ሌላው በተደጋጋሚ እንደታዘብነው መንግሥታዊ ተቋማት ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እና ድጋፎችን እርዳታ የሚደረሳቸውን ዜጎች ነፃነት በሚነጥቅ ሁኔታ ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚኾነው ብልፅግና ፓርቲ ከኢሕአዴግ በወረሰው መጥፎ ጠባይ፤ ባለፈው ሃገራዊ ምርጫ የገጠር እና የከተማ ሴፍቲኔት መርኃግብሮችን ለምርጫ ድምፅ መግዣ አድርጎ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡ “ብልፅግናን ካልመረጣችሁ የሴፍቲኔት ድጋፉን እናቋርጣለን” በሚል ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማስፈራሪያ እንዲሁም ለሴፍቲኔት ፕግራም የተመደቡ በጀቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ ጥቅም ላይ የማዋል ተግባራት ሲፈጸሙ እንደነበር የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

ከሰሞኑ ይህ የመንግስት የሞራል ማጣት ልጓም እጅጉኑ በመክፋቱ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የሚያቀርቧቸው ሰብዓዊ ዕርዳታዎች በመንግሥት ኃይሎች እየተዘረፉ ለችግሩ ተጠቂዎች ከመድረስ ይልቅ ለሌላ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የዕርዳታ መርኃ ግብር ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

መንግሥት በቂ የሆነ ምርት እንዲኖር የማስቻል ስራውን በተገቢው ሁኔታ አለመወጣቱ ሃገሪቱን ለእርዳታ መዳረጉ እና በዜጎች ላይ የተረጂነት እና ጥገኝነት መንፈስ እንዲሰፍን ማድረጉ ሳያንስ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ህይወታቸውን ማቆያ የሚሆንን የእርዳታ እህል መዝረፍ እና እንደ ሃገር መከላከያ ያሉ ተቋማትን ስም በሚያጠለሽ ሁኔታ እንዲነሳ ማድረግ የመንግሥት የሞራል ዝቅጠትን ጥግ ያሳያል።

በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ሞራል ካለው ሃገሪቱ የምታመርታቸውን ምርቶች ዋጋ ሆነ ብሎ እንዲያጋሽብ የማያደርግበት፣ ፍጆታዎች ሆነ ተብለው በየማከማቸው የማይደበቁበት፣ ለአርሷደሮች የሚመጣ ማዳበሪያ ሆነ ተብሎ እንዲነፈግ የማይደረግበት እና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ በየትኛውም መልኩ የሚፈጠር ትርምስ አትራፊ ያደርገኛል ብሎ ካመነ ምንም አይነት ነገር ከማድረግ እንደማያቆም ማሳያ ግልጽ ተግባር ነው።

እንዲህ አይነት መልካም አስተዳደር የጎደለበት ሥርዓት በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ዝቅጠት እና ወንጀል የማኅበረሠባችንን እሴት እጅጉን የሚፈታተን አፀያፊ ተግባር እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።

መንግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ የፌደራል መንግሥቱ ሊኖረው የሚገባውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው ለህወሓት ያልተገደበ ነፃነት ሰጥቶ ትንፋሽ እንዲዘራ እና ትግራይ ክልልን መልሶ እንዲቆጣጠር በማድረጉ ምክንያት ከአንድ ወር በፊት በክልሉ ሰብዓዊ ዕርዳታዎች ላልተገባ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን በመጥቀስ የዕርዳታ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡ የትግራይ ህዝብ አሁንም ተመልሶ ለከፋ ርሃብና እጦት ሲጋለጥና ህወሓት በተመቻቸለት ነፍስ የመዝራት ዕድል ተጠቅሞ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እየደረሱበት ያሉ ተቃውሞዎችን ለመከላከል በጦርነቱ ለማገዳቸው ታጣቂዎች አሳልፎ በመስጠት የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያስጠብቅ ለማድረጉ ዋነኛ ተጠያቂው የፌደራል መንግሥት መኾኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

በመኾኑም፤ መንግሥት በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚቀርብ ድጋፍን ከብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ እንዲያከናውን የተጣለበትን ግዴታን እንዲሁም በረዥም ጊዜ ሂደት ሃገሪቱን ከተመጽዋችነት የምትላቀቅበትን ምርታማነትን የማሳደግ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡ በየትኛውም ደረጃ የሚደረግን ሰብዓዊ ዕርዳታ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለምርጫ ቅስቀሳ እና ለገፅታ ግንባታ የመጠቀም አባዜም በአስቸኳይ እንዲያቆም እናሳስባለን፡፡

ዓለምአቀፍ የተራድዖ ድርጅቶችም በስግብግብ መንታፊ መንግሥታዊ አሠራር ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን የሚጎዳ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተገንዝበው ከመንግሥት ጋር በጋራ የጀመሩትን እነዚህን ወንጀለኞች ሕግ ፊት የማቅረብ ጥረት ማጠናከር እና የእርዳታው ተደራሽነት ላይ ቀደም ካለው ጊዜ በበለጠ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ከእርዛት እና መከራ እንዲያወጡ እንጠይቃለን።

መንግሥት ይህን አሳፋሪ እና አፀያፊ ተግባር ከዚህ ቀደም ተድበስብሰው እንደቀሩ ሌብነቶች በአንድ ሰሞን ግርግር እንዳያልፍ ይልቁንም ከምንም ነገር አስቀድሞ መንግሥት በይፋ ወጥቶ ይህንን ቆሻሻ ተግባር ከማመን በተጨማሪ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የድርጊቱ ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ገለልተኛ አካል ታክሎበት እንዲታይ፣ ሂደቱም በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እና በመጨረሻም ፍትህ ሲሰፍን በግልጽ ሊያሳይ ይገባል ስንል እናሳስባለን።

የኢትዮጵ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
ሰኔ 09/2015 ዓ.ም.

Abere
Senior Member
Posts: 15423
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: EZEMA blasted the PP government for stealing food aid. Report.

Post by Abere » 16 Jun 2023, 08:03

How did you get the appetite to post about EZEMA :mrgreen: PP is the head and EZEMA is the tail of the destruction politics of Ethiopia.

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: EZEMA blasted the PP government for stealing food aid. Report.

Post by TGAA » 16 Jun 2023, 11:42

Ezema except helping oromuma criminals ravage the country more by giving cover as a party it has died in the heart and minds of Ethiopians long time a go. Wither away.


Nauseating!
Last edited by TGAA on 16 Jun 2023, 13:41, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42761
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: EZEMA blasted the PP government for stealing food aid. Report.

Post by Horus » 16 Jun 2023, 13:01

ኢዜማ፣ የመግለጫ ፓርቲ! እኔ ሆረስ ስለዚህ ፓርቲ ሁለተኛ መስማትም ማንበብም የምችለው ከወረሙማ ወጥቶ ነጻ ፓርቲ ሆኖ ይህን አረመኔ መንግስት መታገሉን የሚያሳይ መረጃ ሳገኝ ብቻ ነው ። ነጻነት ለኢትዮጵያ!

Post Reply