Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 4809
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

TPLF denounces the decision of Ethio Elections Board, report

Post by Right » 16 May 2023, 23:48

· የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
May be a graphic of text
Tigrai Television

· የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

—–

የኢትዮዽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሀይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሳትፏል በሚል ምክንያት የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ፤ የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ሥም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እንዲሁም የፓርቲው ንብረት ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሽፈኛ እንዲውል ቀሪው ገንዝብና ንብረት ደግሞ ለሰነ ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ሲል ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም መወሰኑ ይታወቃል።

ሆኖም ህወሓት፤ ጦርነትን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሕዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ ከኢፌዴሪ መንግስት ጋር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ግጭትን የማቆም ስምምነት ፈርመዋል። በዚሁ ስምምነት መሰረትም ህወሓት በሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ጥያቄዎቹን ለመመለስ ወደሚይስችለው ምዕራፍ ገበቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

በዚህም ምክንያት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ከአሸባሪነት መዝገብ ተሰርዞ በትግራይ አካታች ጊዚያዊ አስተዳደር ገብቶ መሪ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የሰላም ተስፋ ከመደገፍ ይልቅ የሰላም ስምምነቱ ዋናው ባለቤት የሆነውን ህወሓት ህልውና እንዳይኖረው ለማድረግ ያስተላለፈውን ውሳኔ በሕግም በፖልቲካም ተቀባይነት የለውም።

ምክንያቱም ውሳኔው የሰላም ስምምነቱ ባለቤት አልባ የሚያደርግ፣ ህወሓትን ወክለው በትግራይ አካታች ጊዚያዊ አስተዳደር እየተሳተፉ ያሉት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች እውቅናን በመንፈግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ህልውና አደጋ ላይ ይሚጥል እንዲሁም አጠቃላይ የሰላም ስምምነቱን የሚፈታተን ነው።

ስለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገራችን የተጀመረውን ተስፋ ሰጭ የሰላም መንገድ ለመደገፍ ሕግን በአወንታዊ የትርጉም ስርዓት ከመረዳት ይልቅ፤ ቴክኒካዊ በሆነ አረዳድ ሰላማዊ ፖለቲካዊ መግባባትን ማደናቀፍ አይኖርብትም። ይህ አካሄድ እንደ ህወሓት ወደ ሰላማዊ ትግል ለመመለስ ለሚዘጋጁ ሀይሎችም ተስፋ የሚያስቆርጥ ተግባር ነው።

ስለሆነም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን ውሳኔ የትግራይ አካታች ጊዚያዊ አስተዳደር ህልውና አደጋ ላይ ይሚጥል እና አጠቃላይ የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፍ ተግባር በመሆኑ ቦርዱ ውሳኔውን መርምሮ እንዲያስተካክል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የትግራይ አካታች ጊዚያዊ አስተዳደር

ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

መቐለ

Right
Member
Posts: 4809
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: TPLF denounces the decision of Ethio Elections Board, report

Post by Right » 17 May 2023, 00:09

The criminal TPLF should know that a rule is a rule. The election board is an institution that should follow and implement the law as tabled by the legislature.
There is not such thing called “a political law”. The board is not a political party or a political organization that takes a political decision.

Down and out. TPLF is dead. The leadership would have been killed or arrested. They have to thank Mamo kilo their step child for saving them.
.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: TPLF denounces the decision of Ethio Elections Board, report

Post by kibramlak » 17 May 2023, 12:43

Tplf ለራሱ የማይጥመውን ሁለ ለመቃወም የተፈጠረ ካንሰር
Right wrote:
17 May 2023, 00:09

Post Reply