Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42771
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 16 May 2023, 01:45

ይህን ማወቅ ግዴታችሁ ስለሆነ ይህን ሳትመልሱ ግዕዝ ተናጋሪ ነኝ ማለት የሚያሳፍር ይሆናል! መልሳችሁን ከታች አኑሩ !

ለምሳሌ፣
ይህ ግዕዝ ምንድን ነው? ለሚለው የተሰጠ መልስ ስልሆነ ትክክለኛ አይደለም " ግዕዝ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋ ነው" ፣ ይህ የግዕዝ ትርጉም ስላይደለ መልስ አይሆንም ።
Last edited by Horus on 16 May 2023, 16:06, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42771
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 16 May 2023, 02:44

ሃላፊ መንገዲና አሱማኢዛና የት ነው ያሉት?

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Abe Abraham » 16 May 2023, 15:25


ድሮ ዲያቆን ተስፋይ ዘዓደርዓዳ ዘሓማሴን ዘኤርትራ በየኣራት ዓመት ህጻንነቴ ፡ በእረፍት ጊዜ ኢዞላ ቨርደን ወጥቼ በማዶ እየተመለከትኩ ፡ ሒሳብና ፊደሎችን ሲያስተምረን " ሀ -ግዕዝ ሁ-ካዕብ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሓምስ ህ-ሳድስ ሆ-ሳብዕ " ስንል ኣስታውሳለሁ ።

ያን ጊዜ " ግዕዝ " ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው ብየ ባልጠይቅም ኣሁን ባገኘሁት መልስ ጠለቅ ያለ ባይሆንም ትርጉሙ " መጀመርያ " ነው ይላል ።





Abere
Senior Member
Posts: 15426
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Abere » 16 May 2023, 16:22

ሆረስ፥

እስመ ግዕዝ ያግእዘነ እምኩሉ ጻማዌ ( ግዕዝ ከድንቁርና ሁሉ ነጻ ያወጣል)

"ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል፡፡ ፍጥረታት በሐሊዎ በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ፡፡እነዚህ ሊቃውንት ቅዱስ ገብርኤል ንቁም በበህላዌነ ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፡፡ አዳምም ለ7ዓመታት በገነት ሲኖር በፀሎት ሲተጋ የነበረው በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል፡፡" አስተዳላዊ ዲ/ን የሽጥላ ው/ጻድቅ


መጽሀፉ እንድህ ካለ እነ አቶ አካለ ወልድ የወረሙማ ሃይማኖት ምን ሊያደርጉት ይሆን? :mrgreen:

https://www.academia.edu/49194596/The_n ... aguage_new



Horus wrote:
16 May 2023, 01:45
ይህን ማወቅ ግዴታችሁ ስለሆነ ይህን ሳትመልሱ ግዕዝ ተናጋሪ ነኝ ማለት የሚያሳፍር ይሆናል! መልሳችሁን ከታች አኑሩ !

ለምሳሌ፣
ይህ ግዕዝ ምንድን ነው? ለሚለው የተሰጠ መልስ ስልሆነ ትክክለኛ አይደለም " ግዕዝ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋ ነው" ፣ ይህ የግዕዝ ትርጉም ስላይደለ መልስ አይሆንም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42771
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 16 May 2023, 16:24

አቤ፣
እንደ ተለመደው ጥሩ ጅማሮ ንው። እኔም ያልከውን ለብዙ ግዜ አስቤው ነበር ። ከዚያ ግዝ (ግዕዝ) መጀመሪያ ወይም አንደኛ ማለት ከሆነ ሌላ ቦታ በዚያ ትርጉሙ ጥቅም ላይ ሲውል ማየት አለብን ።

ለምሳሌ አሃዝ ስንል ቁጥር ማለታችን ነው (አሃዝ በድምጽ ሺፍት ግዕዝ ሊሆን ስለሚችል) ። ሌላው ትልቁ ጥያቄ ግዕዝ መጀመሪያ ወይም ቁጥር ምለት ቢሆን ለምን የቋንቋ ወይም የፊደል ስም ይሆናል? ይህ ነው የሚቀትለው ቻሌንጅ!

ሌላ አንድ ክሉ ልስጥህ ። እሱም ግስ የሚለው የሰዋስው ቃል ነው ። እስካሁን ለእኔ ጠንከር ያለው ካንዲዴት ነው ። ግስ ቨርብ ማለት ነው ። ቨርብ የጥንት ግብጽ ቃል ሲሆን ዛሬ ላቲን ውስጥ ነው ያለው ። ቨርብ በቀምጥ አፍ ማለት ነበር፣ ኋላ መናገር ሆነ ። ኢቲሚሎጂውና ፊሎሎጂው ላይ እዚህ አላሰለችህም ።

ነገር ግን ያም ቢሆን ግዝ (ግስ) መናገር ፣ ማውራት በሚለው ትርጉሙ ጥቅም ላይ ሲውል ማየት አለብን (ኤቪደንሱ ያ ስለሆነ) ።

ሌላው ትልቁ ቻሌንጅ ግዕዝ ቅዱስ ቋንቋ ነው ይባላል! ልክ እንደ ህንድ ሳንስክሪት (ቅዱስ ጽሁፍ ማለት ነው) ። ታዲያ ግዕዝ እንደ ልሳነ መለኮት እንዴት ነው ከግስ ጋር ወይም ከመጀምሪያ ጋር ሚጣጣመው?

ኬር!

Horus
Senior Member+
Posts: 42771
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 16 May 2023, 16:47

አበረ፣
ድንቅ ነው! በቀጥታ መልሱ ወዳለበት ሰፈር ነው የሄድከው ። (this is called Findability Principle ማለትም አንድ ነገር የሚገኘው ሊኖር በሚችልበት ቦታ ሲፈለግ ነው) በመጀምሪያ ቃል ነበረ ይላል ኦሪት ዘ ፍጥረት! ቋንቋ የፍጥረት ሕላዌ፣ ገቢርና ነቢብ መግለጫ ነው ። ፈጣሪም ቢሆን አለምን ይሁን ብሎ በቃሉ ነው የፈጠረው ይባል የለ! ዛሬ በኮግኒቲቭ ሳይንስ ውስጥ "በቋንቋ ማንኛውም ነገር መፍጠር ይቻላል" የሚባል መርህ አለ። አው የግዕዝ ትርጉም በፍጥረት ኦሪት ውስጥ ነው ያለው ። ነገር ግን እራሱ ቃሉን ፈልቅቀን ማውጣት ይኖርብናል

ይቀጥላል !

Abere
Senior Member
Posts: 15426
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Abere » 16 May 2023, 17:09

ሆረስ

በነገሩ ዕውቀት የለኝም። ግን ከፍተኛ የማወቅ ጉጉት አለኝ። በግዕዝ ውስጥ አንድ የተደበቀ ምስጢር አለ። ለምሳሌ ዳዊት ወይም ውዳሴ በግዕዝ ስትደግም እና ስትተረጉምመው ሃይሉ የተለየ ነገር ነው።

አንተ ደግሞ እጅግ በሚገባ መልኩ ገለጽከው። ሎጅካዊ (ተጠየቃዊ) ትንታኔ ድንቅ ነው።

ሰውን በመልካችን በአርዓያችን እንፍጠር (ንግበር ሰብዓ በአርዓያነ ወበአምሳሊነ -ዘፍ. ፩፥፳፮) ሲል ለሰው ልጅ እግዚአብሄር የተለየ ፍቅር አለው ማለት ነው። ይህ ማለት ለሰው ልጅ ቋንቋን ሰጠው።

ከፍጥረታት ሁሉ የሰው ልጅ ብቻ ነው ቋንቋ ያለው። ሊሎች እንሰሳት ቋንቋ የሌላቸው እንደ ፊዚካል አንትሮፓሎጅስቶች አተያይ በአእምሯቸው ውስጥ ረቂቅ ነገሮችን ይሁን ቁሳዊ ሁኔታወችን ምልክት እያደረጉ የመሰየም ጸጋ ስላልተሣጣቸው ነው።ይህ እንዳልከው መለኮታዊ ስጦታ እና ቃና አለው። እግዚአብሄር አዳም እና ሄዋን በገነት በነበሩበት ዘመን ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር። ይህ እንዳልከው መለኮታዊ ስጦታ እና ቃና አለው። እግዚአብሄር አዳም እና ሄዋን በገነት በነበሩበት ዘመን ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር።


Horus wrote:
16 May 2023, 16:47
አበረ፣
ድንቅ ነው! በቀጥታ መልሱ ወዳለበት ሰፈር ነው የሄድከው ። (this is called Findability Principle ማለትም አንድ ነገር የሚገኘው ሊኖር በሚችልበት ቦታ ሲፈለግ ነው) በመጀምሪያ ቃል ነበረ ይላል ኦሪት ዘ ፍጥረት! ቋንቋ የፍጥረት ሕላዌ፣ ገቢርና ነቢብ መግለጫ ነው ። ፈጣሪም ቢሆን አለምን ይሁን ብሎ በቃሉ ነው የፈጠረው ይባል የለ! ዛሬ በኮግኒቲቭ ሳይንስ ውስጥ "በቋንቋ ማንኛውም ነገር መፍጠር ይቻላል" የሚባል መርህ አለ። አው የግዕዝ ትርጉም በፍጥረት ኦሪት ውስጥ ነው ያለው ። ነገር ግን እራሱ ቃሉን ፈልቅቀን ማውጣት ይኖርብናል

ይቀጥላል !

Naga Tuma
Member+
Posts: 7376
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Naga Tuma » 17 May 2023, 01:39

ሆረስ፥

እኔ ግዕዝ ተናጋሪ ነኝ ማለት ኣልችልም። ብኮላተፍም አማርኛ ተናጋሪ ነኝ ማለት የምችል ይመስለኛል። ከግዴታህ መዉጫ ይሆነኛል።

እባክህ የኢትዮጵያዉ ቶማስ ጀፈርሰን ኣትሁንብን እና ግዕዝ እና እንግሊዝን የምያገናኛቸዉ ኣለ? ቶማስ ጀፈርሰን ስለ አቴና ሰምቶ ፈንድቆ ስለ አክናተን ሳይሰማ ያረፈ ነዉ።

አቤ አብረሃም፥

ባዶ ብርጭቆ ኣስጨለጥከኝ። እዉነቴን ነዉ። ስለ ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብ የፃፍከዉን ሳነብ በደስታ አጠገቤ የነበረዉን ብርጭቆ ኣነሳሁ። ባዶዉን ጨለጥኩት። ኣሳቀኝ።

ቁም ነገሩ እንዲህ ነዉ። በቅርቡ አፋን ኦሮሞን በፊደል መፃፍ ስለማመድ ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብን ኣስታወሰኝ። ኣንድ ቃል የተላያየ ዳይለክት ይመስለኝ የነበረዉ ሁለት የተለያዩ ቃላት መሆናቸዉን ለመጀመርያ ግዜ ኣስተዋልኩኝ።

ሁለቱ ቃላት ኮሜ እና ኮሚ ናቸዉ። የሚላያቸዉ ሜ እና ሚ ብቻ ናቸዉ። ይህ ልዩነት ብቻ ለቃላቱ የተለያየ ትርግም መስጠታቸዉ ስለ ግዕዝ ካዕብ ምንጭ እንዳሰላስል ኣደረጉኝ። ከዛ በኋላ ነዉ ስለሚቀጥለዉ ኬኛ ኣብዮት እዚህ መድረክ ላይ ያፃፈኝ።

በዚሁ ኣጋጣሚ አምቼ ወንድሞቻችን ቀን ወጣልን ብለዉ መፈንጨት እንዴት ይዞሃል? አምቼ ያደረገን የድሮዉ ኣጼኣችን ቻይናን ከጎበኘ ሃምሳ ሁለት ዓመታት በኋላ አምቼ ያስባለን የዘንድሮዉ ኣጼኣችን ቻይናን ከጎበኘ ምን ኣጠፋን ብለዉ ኣልፈነጩብህም? የድሮው አማርኛ ተናጋሪ የዘንስሮዉ ትግርኛ ተናጋሪ ናቸዉ። ዛት እዝ ዘ ፖትንት ኣልካቸዉ? ይህም ለፈገግታ ከሆነ ነዉ። እዉነቱ አምቼ ኣልላቸዉም።

Horus
Senior Member+
Posts: 42771
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴም ቋንቋ ለምትናገሩ ሁሉ፤ ግዕዝ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 17 May 2023, 02:35

አበረ፣
የግዕዝን ዘርፈ ብዙ አመጣጥ፣ ታሪክና አጠቃቀም መጻፍ ስጀምር ሃሳቦቹ እንደ ጎርፍ ያጣብቡኝና መጻፉን አቆማለሁ ። ግዕዝን መግለጽ የምንችልባቸው መስኮች ብዙ ብዙ ናቸው ። እምነት፣ ሃይማኖት (ነገረ መለኮት) ፣ ሚቶሎጂ፣ ትርክት፣ ካልቸር፣ ቋንቋ፣ ኮኚቲቭ ሳይንስ (ስነ እውቀት)፣ ስነ ተግባር (ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን) ወዘተ!

ለዛሬ አንዲት ነገር ብቻ ብዬ ልውጣ ።
ልክ እንዳልከው ቋንቋ ተአምር ነው ። እንሰሳ ስለሆንን በአፍና ጉሮሮአችን ድምጽ ማውጣታችን አይደለም ተአምሩ፤ ድምጽን ወደ ቋንቋ ማሳደጋችን ነው እጅግ ግዙፉ ፍልስፍናችን ። የሰውን ልጅ እዚህ ካደረሱት ጥቂት ፍልሰፋዎች ለምሳሌ ወርቅን ማወቅ፣ መስተዋት መስራት፣ ዉሃን ማጽዳት፣ ግዜን መቁጠር፣ ሰው ሰራሽ ብርሃን መፍጠርን ጨምሮ ድምጽን ወደ ቴክኖሎጂ መፈልሰፍ የሰው ልጅ ታላቅ ስራ ነው ። ድምቶችን ከታትፎ ለይቶ እነዚን የድምጾች ቁርጭራጭ እንደ ድርና ማግ ፈትሎ ንግግር ወይም የአፍ ቋንቋ መፍተር እራሱ የቻለ የዘመናት እድገት ሆኖ ሳለ ድምጾችን በምስል (በስዕል) ቀርጾ ፊደል (ጭረት ወይም ጽሁፍ) የሰራ ቀን ነው የሰው ልጅ በፈጣሪነቱ ወደ እግዚአብሄር ጠጋ ያለው !!!

ፊደል ምስል ነው ። ሲጀመር ካንጎላችን ውጭ ያለው አለም ሁሉ አንጎላችን ውስጥ የሚገባው ምስል ሆኖ ነው ። ምስል የሪያሊቲ ኮፒ ቅጂ ነው ። ሃስብ ባይምሮአችን ውስጥ ያለ ምስል ነው ፣ ማንኛውም ሃስብ ትልቁም ትንሹም ! ይህ ምስል በፊደል ሲቀረጽ የሚሰማ ድምጽ ብቻ ሳይሆን የሚታይ ምልክት ሆነ ። ስለዚህ ቃል ከሌለ፣ ቋንቋ ከሌላ ምንም ነገር ማወቅ ስለማንችል ለሰው ልጅ አለም የሚፈጠረው በቃል አማካይነት ፍጥረትን ሲያውቅ ነው ።

መጀምሪያ ቃል ነበረ! ፈጣሪ ቃል ነው! ቃል ምስል ነው ። ፈጣሪም ባምሳሉ ሰውን ፈጠረ! አንድ ነገር ምስሉን አይቶ ነው ብሎ መቀበል ማመን ነው ። በአንድ ቃል አይምሮ የተፈጠረው በቃል ነው፣ በቋንቋ ነው ። ሃሳብ ያለ ቋንቋ ሊኖር አይችልም፣ ነፋስ ሆኖ ይጠፋል ። ሃሳብን በፊደል ቀርጾ በምስል መልክ ማኖር የጀመረ ቀን የሰው ልጅ እጅግ እጅግ የመጠቀው።

ይቀጥላል

Post Reply