Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
wazzupdog
- Member
- Posts: 2009
- Joined: 16 Jun 2018, 22:10
Post
by wazzupdog » 15 May 2023, 17:41
እስካሁን ድረስ የማልረሳው አንድ ያነበብኩት ነገር ነበር። በዘመነ መለስ ሳጥናዊ ጊዜ ነው። የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የውይይት ግብዣ ይልካል። በዛን ጊዜ እነገብሩ አስራት አረና የሚባል ፓርቲ አቋቁመው ከፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር የሆነ ጥምረት ፈጥረው ነበር። ይሄ የኤምባሲ ግብዣ ክህደቱ አያሌውንም ይጨምር ነበር። ገብሩ አስራት አሻፈረኝ አለ። ክህደቱ አያሌው ከተጋበዘ እኛ አንሄድም አለ። የዛን ጊዜ ነገሩ ገባኝ። ገብሩ አስራት ክህድቱ አያሌውን የሚያውቀው እሱ የወያኔ ቁንጮ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ነው። ክህደቱ አያሌው ከወያኔ ጋር ያለውን ግንኙነት በጥልቀት ስለሚያውቅ አብሮ ውይይቱን መካፈል አልፈለገም።
