Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Abe Abraham
- Senior Member
- Posts: 14414
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
Post
by Abe Abraham » 14 May 2023, 01:32
ኣንድ ሱዳናዊ ምሁር በኣንድ የሃሳብ መለዋወጥ ስብሰባ ፥
ምዕራባዊ ዓለም እኛን የሚጠላበትና የሚፈራበት ምክንያት ኣለው ። እኛ እስልምናን በመላ ኣፍሪቃ የመዘርጋት ፍላጎት ኣለን ። እሱ ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት ስሜታችን ከመንጥቕ/ሎጂክ/ስነ-መጎት የወጣ ሊሆን ይችላል ። ለምሳሌ ኣ(ል)-ታዓይሺን / የማህዲዎች መሪ / ዮሃንስ " እኛ የጣልያን ወራር ችግር እናንተ ደሞ የእንግሊዞቹ የወራር ችግር ስላላችሁ ብንተባበር ኣይበጀንም ወይ ? " ብሎ ሲጠይቀው ኣ(ል)-ታዕይሺ ለዮሃንስ " ኣንተ በኔ ነቢ ታምናለህ ወይስ ...? " ብሎ ጥያቄን በጥያቄ መልሶ ውግያ ኣንስቶ የምስኪኑ ኣበሻውን/ኣል-ሓበሺ ኣል-ሚስኪን/ ኣንገት ቆርጦ ወደ ኡምዱርማን ወሰደው ።
---
ባሁኑ ጊዜ የሱዳን ወታደሮችና ደጋፊዎቻቸው የህዝቡን ስሜት ቀስቅሰው የሕሜድቲን ፈጥኖ ደራሽ/ኣል-ዳዕም ኣል-ሰሪዕ በህዝብ ዘንድ እንደሚጠላ ለማድረግ ከተጠቀሙት ኣንድ ዘዴ " የሕሜድቲ ኣማጽያን/ሙተመሪዲን ሴቶች ይደፍራሉ " የሚል ወሬ ማስራጨት ነው ። ( ሌላው ዘዴ ፥ ከሰራዊቱ ብዙዎቹ ቻዳውያን ኒጀርያውያንና ካሜሩናውያን እንጂ ሱዳናውያን ኣይደሉም ። /ሱዳናዊ ማን ነው የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሱ ገዢው የሰሜኑ ቡድን ይሆናል ማለት ነው ። በትምክህተኞች ኣይን ማንኛውም የዙርቕ/ኒገር ኣፍሪቃዊ ብሄረ-ሰብ ኣባል እንደ ኣንደኛ ደረጃ ሱዳናዊ ኣይቆጠርም ። ሓሰን ኣል-ቱራቢ እንደ ተረከው ዑመር ኣል-በሺር ስለ የዳርፉር የሴቶች መድፈር ጉዳይ ከጓዶቹ ጋር ሲነጋገር " ለዳርፉር ሴትን ኣንድ የሰሜን ወንድ ቢጫንባት/የርከብሃ/if he were to mount her ምን ይከፋታል " ኣለ ። ይህ የ" superior " እና የ " inferior " ጉዳይ በኢስላሚስቶች/ብራዘርሁድ/ - ሃይማኖተኞች ነን የሚሉ - ጉዳይ ይወስደናል ። )
በተጨማሪ የሱዳን ወታደሮች ደጋፉዎች መድፈር የሚለውን ክስ ሲያነሱ በታሪክ ወደ ጓላ ተመልሰው ኣ(ል)-ታዓይሺን ይጠቅሳሉ ። እንደሚባለው ከዳርፉር የመነጩ የኣ(ል)-ታዓይሺ ሰራዊት ኣባሎች ድሮ በካርቱም በነበሩበት ጊዜ ብዙ ሴቶች ስለ ደፈሩ የናይል ውሃ በብዙ ኢንቲሓር/suicide የፈጸሙ ሴቶች ሞልቶ ነበር ።
እዚ ማስተዋል ያለብህ ፥ ኣ(ል)-ታዓይሺ ባንድ በኩል የሃይማኖት ተቆርቋሪና ጀግና እየተቆጠረ በሌላው በኩል ደሞ ከዳርፉር በመሆኑ የዳርፉሩ ሕሜድቲ ከነሰራዊቱ ሲወነጀል የኣ(ል)-ታዓይሺ ስም ይነሳል !!
/ በኣረብኛ " ቸ " የሚባል ፊደል ስለሌለ ሱዳናውያን ሕሜድቲን ቻዳዊ ነው ለማለት " ሕሜድቲ ትሻዲ " ይላሉ !! ስርዓተ-ፊደላችን "ቸ" ና " ጨ " ስላለው ሃያል ነው ። ቻዳውያን የኣገራቸው ስም በኣፍሪቃዊ ቋንቋቸው እንዴት እንደሚያደምጡት ባላውቅም በትግርኛ " ጫድ " የሚል ኣጻጻፍ ኣንብቤ ኣለሁ ። ቻዳዉያን " ጨ " የሚባል ፊደል እንዳላቸው ሲናገሩ ስምቼኣለሁ ።/
-